SUBSCRIBE

Search This Blog

Jul 27, 2020

አስተዳደራዊ ስልጣን ደንብና መመሪያ አወጣጥ

አስተዳደራዊ ስልጣን

ደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያከናውኗቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋነኛ ስልጣንና ተግባር ህግ ማውጣት አሊያም ዳኝነት መስጠት ሳይሆን ማስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደራዊ ስልጣን ከህግ ማውጣት እና ዳኝነት መስጠት ውጪ ያሉትን ተግባራት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ የአስተዳደር /ቤቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ይህን የእለት ተእለት የአስተዳደር ስራ በማከናወን ነው፡፡
በዚህ ስልጣን ስር ከሚወድቁ በርካታ ምሳሌዎችን መካከል ሪፖርት ማቅረብ፣ ፓስፖርት መስጠት፣ ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ፀጥታ ማስከበር፣ ክስ መመስረት፣ እድገትና ሹመት መስጠት፣ ምርመራ፤ ቁጥጥርና ክትትል ማካሄድ የምክር ሀሳብ መስጠት ወዘተ ሁሉም የአስተዳደር /ቤቶች አስተዳደራዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ስራዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ተግባራት የህግ መጣስ መኖርን አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የመረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ስርዓት የንግድ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱ በአካል ተገኝቶ ቀጥተኛ እና የአካባቢ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና የማጣራት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡
የመርማሪነት ስራ ህጉ ልዩ ስልጣን በሰጣቸው መርማሪዎች የሚከናወን ሲሆን የምርመራ ሂደቱም በህግ ማእቀፍ ውስጥ ይመራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የፖሊስ የምርመራ ተግባር ነው፡፡ ፖሊስ ወንጀል ሲፈጸም ወይም ተፈጽሟል የሚል መረጃ ከደረሰው አሊያም ተገቢ ጥርጣሬ ካደረበት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል በመገኘት ተጨባጭ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ እና ተጠርጣሪውን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ስልጣናት አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአስተዳደር /ቤቶች የመርማሪነት፣ የቁጥጥርና ክትትል ስልጣን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ለፖሊስ ከተሰጠው ስልጣን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡
በአስረጂነት በተወሰኑ ህጎች ለተቆጣጠሪዎች የተሰጣቸው መጠነ ሰፊ ስልጣን በማጣቀሻነት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንa
ሳያሳውቁ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባት
ማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት የመጠየቅ
ከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት፣ ማህደር ወይም ሌላ ሰነድ መፈተሽ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳት
የማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በህይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመር
የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 300/1995 ወይም ሌላ ህግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፍቶግራፍ ማንሳት፣ መለካት፣ መሳል ወይም መፈተሽ
አዋጁን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ህግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሳሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝ
የዱር እንስሳት ቁጥጥር ሠራተኛb
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶች ተደብቀዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ወደ ማንኛውም ሰው መሬት፣ ህንጻ፣ ድንኳን፣ ተሸከርካሪ፣ የአየር መንኮራኩር ወይም ጀልባ ውስጥ የመግባትና የመፈተሸ እንዲሁም ሻንጣ ወይም እሽግ የመፈተሸ
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶችን እንዲሁም ጥፋቱ የተፈጸመባቸውን መሳሪያዎች እንዲወረሱ ለማድረግ እንዲቻል በቁጥጥር ስር የማድረግና የሚመለከተው አካል ባወጣው የመመዝገቢያ ቅፅ መሰረት ተገቢውን ደረሰኝ ሰጥቶ የመረከብ
የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 541/1999 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በመተላለፍ ጥፋት ሲፈጽም የተገኘን ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ማስረከብ
የደን ውጤት ተቆጣጣሪc
የደን ውጤቶችን የጫነ ወይም ለመጫኑ የሚጠረጠርን ማናቸውንም ማጓጓዣ በደን መግቢያና መውጫዎች እንደአስፈላጊነቱ በሚመረጡ የሀገር ውስጥ እና የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አስቁሞ መፈተሸ
የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 542/1999 በመተላለፍ ተዘጋጅተው ሲጓጓዙ ወይም ተከማችተው የተገኙ የደን ውጤቶችን ከድርጊቱ ተጠያቂዎች ጋር የመያዝ
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርd
የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁ. 602/2000 ለማስፈጸም የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ቡና ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚገመትን መጋዘን፣ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድርጅት፣ ማጓጓዣ ወይም ማናቸውም ሌላ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የመፈተሽ፣ህገ ወጥ ቡና ሲያዝ የማሸግ፣ ምርቱን የማገድ፣ የመያዝ፣ ህገ ወጥነታቸው የማያጠራጥር ሲሆን የቡናው ባለቤት ለፍርድ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመውረስና የመሸጥ.

muhajersemanlaw7.wordpress.com

የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርህ እና ስርዓትአስተዳደራዊ ውሳኔ ምንድነው?‘

የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርህ እና ስርዓት
አስተዳደራዊ ውሳኔ ምንድነው?
‘አስተዳደራዊ ውሳኔ’ በአስተዳር ህግ ውስጥ ከቃል አጠቃቀም፣ ከይዘትና ከወሰን አንጻር ቁርጥ ያለ መደብ ከሌላቸው ፅንሰ ሀሳቦች መካከል ጎልቶ ይወጣል፡፡ ውስብስብነቱ ከፅንሰ ሀሳቡ ወካይ ስያሜ ይጀምራል፡፡ ‘አስተዳደራዊ ውሳኔ’ በሚል እዚህ ላይ መጠቀሱም በአገራችን የአስተዳደር ህግ ውስጥ መደበኛ መጠሪያው ቢሆን ይበጃል በሚል ብቻ ነው፡፡ ጀርመኖች እንኳን የራሳቸውን ወካይ ቃል መፍጠር ተስኗቸው አሁን ላይ በአስተዳደር ህጋቸው ዐቢይ ስፍራ ይዞ የሚገኘውን 'Administrative act' (Verwaltungsaktበሚል የሚጠሩትን ፅንሰ ሀሳብ ለማዳበር ከፈረንሳዮች acte administrative ለመዋስ ተገደዋል፡፡
'Administrative act' (Verwaltungsakt) is a core concept of the German administrative law. It covers most of the actions of the administrative authorities through which they affect the legal interests of an individual. The origin of this concept is traced from the French concept of acte administratif from which it was borrowed by the German jurists and developed into a German concept since 1826 onwards.a
በእንግሊዝኛው ፍቺ ከወሰድነው Administrative Decision በይዘቱ Administrative Act ውስጥ የሚጠቃለል ሲሆን ዘርፈ ብዙ መልክ ካላቸው አስተዳደራዊ ተግባራት መካከል አንድ ነጠላ ተግባርን ብቻ ይወክላል፡፡ ሆኖም ለአገራችን የአስተዳደር ህግ ‘አስተዳደራዊ ተግባር’ ወይም ‘አስተዳደራዊ ድርጊት’ የሚለውን ቃል ብንጠቀም ገላጭነቱ አይጎላም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደራዊ ድንጋጌ ማውጣት እንዲሁም ምርመራ፣ ቁጥጥርና ክትትል ሁሉም የአስተዳደር ተግባራት እንደመሆናቸው ዳኝነታዊ ባህርይ ያላቸውን ተግባራት ለይቶ ለማመልከት ውስን ይዘት ያለውን ቃል መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንጻር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ‘የአስተዳደር ውሳኔ’ ወይም ‘አስተዳደራዊ’ ውሳኔ የሚለው ቃል ዳኝነታዊ ባህርይ ያላቸውን ተግባራት ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ሆኖም በመደበኛ ትርጓሜው አደናጋሪ መልዕክት ስለሚፈጥር ይዘቱንና ፍቺውን በቅድሚያ መወሰን ያስፈልጋል፡፡
..1976 .በወጣው የጀርመን የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ የአስተዳደር ተግባር (Administrative act) የሚከተለው ፍቺ ተሰጥቶታል፡፡
Administrative act is every order, decision or other sovereign measure taken by an authority for the regulation of a particular case in the sphere of public law and directed at immediate external legal consequences.b
ወደ አማርኛ ስንመልሰው፤
የአስተዳደር ተግባር ማለት ቅርብና ውጫዊ የህግ ውጤት የሚያስከትል በህዝብ አስተዳደር ህግ ማዕቀፍ ውስጥ አንድን ልዩ ሁኔታ ለመቆጣጠር ሲባል ስልጣን ያለው አካል የሚሰጠው ትዕዛዝ፣ ውሳኔ ወይም ሌላ ማናቸውም ሌላ ሉዓላዊ እርምጃ ነው፡፡
በትርጓሜው ውስጥ ተጨማሪ ሰፊ ማብራሪያ የሚሹ ንዑስ ሀሳቦች ታጭቀዋል፡፡ ሆኖም በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል በጀርመን የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር ተግባር ማለት ህግ ለማስፈጸምና የአስተዳደር ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት ይህን ህዝባዊ ስልጣናቸውን (public functions) በመገልገል የሚሰጡትን ትዕዛዝ፣ ውሳኔ ወይም ማናቸውም በማድረግ፣ ባለማድረግ የሚገለጽ እርምጃ ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ይህም ማለት በውል ወይም ከውል ውጪ ኃላፊነት ህጎች ስር የሚሸፈኑ ግላዊ ድርጊቶች፣ ውሳኔዎች፣ እርምጃዎች ወዘተበአስተዳደር ተግባር ስር አይሸፈኑም፡፡
በትርጓሜው ላይ ‘ልዩ ሁኔታ ለመቆጣጠር’ ሲባል ተግባሩ ህጋዊ ውጤት እንደሚያስከትል ወሰኑም በአንድ ልዩ ሁኔታ ላይ ያነጣጠረ እንጂ ጠቅላላ ተፈጻሚነት እንደሌለው ያመለክታል፡፡ ስለሆነም የበታች ሠራተኛ ለበላይ ኃላፊ የሚያቀርበው የውሳኔ ሀሳብ፣ ሪፖርት ወይም የምርመራ ውጤት ራሱን ችሎ ህጋዊ ውጤት የማይከተለው በመሆኑ እንደ አስተዳደራዊ ተግባር አይቆጠርም፡፡ በአንድ ዘርፍ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ (ለምሳሌ ስጋ ሻጮች ማሟላት ያለባቸው የጥራት ደረጃከላይ በተቀመጠው ትርጓሜ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም ተፈጻሚነቱ ሁሉንም የዘርፍ ነጋዴዎች ስለሚያቅፍ ጠቅላላነት ይታይበታል፡፡ በመጨረሻም ህጋዊ ውጤቱ በአስተዳደሩ ውስጣዊ መዋቅር ተወስኖ የሚቀር (ለምሳሌ በአንድ ነጋዴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የበላይ ኃላፊው ለበታች ሠራተኛ የሚያስተላልፈው ማሳሰቢያከሆነ በአስተዳደራዊ ተግባር ውስጥ አይመደብም፡፡
የአሜሪካው የፌደራል አስተዳር ስነ ስርዓት ህግ ተፈጻሚነቱ አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (rule making) እና አስተዳደራዊ ዳኝነት (adjudication) የመስጠት ሂደቶች ላይ ነው፡፡ በህጉ ላይ በተሰጠው ፍቺ አስተዳደራዊ ዳኝነት ማለት በውጤቱ ‘ትዕዛዝ’ የሚያቋቁም የአስተዳደር ሂደት (agency process for the formulation of an order) ነው፡፡ ትዕዛዝ የሚለው ቃል በአስተዳደር ስነ ስርዓት ህጉ ላይ ፍቺ የተሰጠው ሲሆን ይዘቱ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
order means the whole or a part of a final disposition, whether affirmative, negative, injunctive, or declaratory in form, of an agency in a matter other than rule making but including licensing.c
ትዕዛዝ’ ከጀርመኑ ‘የአስተዳደር ተግባር’ ጋር ሲነጻጸር መሰረታዊ ልዩነት አይታይበትም፡፡ ጉዳዩን የሚቋጭ የመጨረሻ መሆኑ ህጋዊ ውጤት እንደሚከተለው ይጠቁመናል፡፡ በይዘቱ አንድ ድርጊት እንዳይፈጸም፣ እንዲፈጸም ወይም የአንድ ሁኔታ (መብትመኖር/አለመኖር የሚያረጋግጥ መግለጫ ወይም ከአስተዳደራዊ ድንጋጌ ማውጣት ውጪ ያለ ማንኛውም የመጨረሻ እልባት የሚሰጥ ነው፡፡
በመቀጠል የአገራችን የፌደራል ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ (1993) የተጠቀመውን ቃል እና አፈታቱን እናያለን፡፡ በረቂቅ አዋጁ የትርጓሜ ክፍል አንቀጽ 2 /2/ እንደተመለከተው አስተዳደራዊ ውሳኔ ማለት፤
ማናቸውም አስተዳደራዊ ባህርይ ያለውን ተግባር ወይም ነገር ከመፈጸም ጋር የተያያዘ ውሳኔ ወይም ውሳኔ አለመስጠትን ጨምሮ ቅጣትን ለመጣል፣ ወይም መፍትሔ ለመስጠት ወይም የመከላከል ዓላማ ወይም ውጤት ያለው በአስተዳደር ተቋማት የሚሰጥ ማናቸውም ውሳኔ፣ ትዕዛዝ ወይም ብይን [ነው፡፡]
የትርጓሜውን ይዘት ይበልጥ ለመረዳት የእንግሊዝኛውን ቅጂ መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡
Administrative Decision means any decision, order or award of an agency having as its object or effect the imposition of a sanction or the grant or refusal of relief, including a decision relating to doing or refusing to do any other act or thing of an administrative nature, or failure to take a decision
በቀጣይ 2001 .በተዘጋጀው ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ አዋጅ አርቃቂዎቹ የተለየ አገላለጽ መጠቀም መርጠዋል፡፡ በረቂቁ አንቀጽ 2/2/ ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡፡
አስተዳደራዊ ውሳኔ ማለት ተጨባጭ ሕጋዊ ግንኙነቶችን ለመመስረት፣ ለማሻሻል፣ በምርመራ ለማረጋገጥ ወይም የተሟላ ለማድረግ ለአንድ ጉዳይ የተወሰነ መፍትሔ የመስጠት ዓላማ ያለውና በግለሰብ ወይም በተወሰኑ ሰዎች ላይ ተፈጻሚነት ያለው በተቋሙ የሚሰጥ ሕጋዊ ውሳኔ ሲሆን፣ አስተዳደራዊ ባህርይ ባለው ተግባር ወይም ጉዳይ ላይ ውሳኔ አለመስጠትንም ይጨምራል፡፡
በሁለቱም ረቂቆች ላይ የሚታየው ገላጭነት የጎደለው የቋንቋ አጠቃቀም አብዛኛው ሰው በቀላሉ አይረዳውም፡፡ ከዚህም አልፎ የህግ ባለሞያዎች፣ ዳኞች እና አስተዳዳሪዎች በጋራ የሚያግባባ አገላለጽ አልያዘም፡፡ ለምሳሌ በተለምዶ ሰርኩላር በሚል ስያሜ ጠቅላላ ተፈጻሚነት ኖሯቸው የሚተላፉ ትዕዛዞች የአስተዳደራዊ ውሳኔና የአስተዳደራዊ ድንጋጌ ከፊል ባህርያት ይጋራሉ፡፡ ሆኖም በአንደኛው ስር ለመፈረጅ ሁለቱም ትርጓሜዎች ግልጽ መለያ መስፈርት አላካተቱም፡፡ ለአስተዳደራዊ ውሳኔ ትርጓሜ ለማበጀት ጥሩ መነሻ የሚሆነው የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው፡፡ ሁለቱን የሚያመሳስላቸው ብዙ ነጥቦች አሉ፡፡ አስተዳደራዊ ሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሁለቱም ምንጫቸው ዳኝነታዊ ስልጣን ነው፡፡ በዳኝነት ፍሬ ነገሩን የማረጋገጥና በተረጋገጠው ፍሬ ነገር ላይ ህጉን ተፈጻሚ የማድረግ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ ዓላማው አከራካሪ የሆነ አንድ ተለይቶ የታወቀ ጉዳይ (particular case) መቋጨት ነው፡፡ ጉዳዩን በመቋጨት የሚነገረው ትዕዛዝ፣ ብይን ወይም ውሳኔ በባለጉዳዮች ወይም ሶስተኛ ወገኖች ላይ ህጋዊ ውጤት ያስከትላል፡፡ እነዚህ ወሳኝ ባህርያት በጀርመኑ እና የአሜሪካው የአስተዳደር ህጎች ላይ በግልጽ ተለይተዋል፡፡
በአንድ የአስተዳደር /ቤት የተፈጸመ ተግባር የአስተዳደር ውሳኔ ነው ወይስ አይደለምየሚለው ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ መሰረታዊ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ጥያቄው ተቋሙ ካሉት ጠቅላላ የማስተዳደር (ህግ ማስፈጸም) ከፊል የህግ አውጭነት እና ከፊል የዳኝነት ስልጣናት መካከል የትኛውን እየተገለገለ እንደሆነ የሚለይበት ነው፡፡ የጥያቄው ሌላ መልክ ሲታይ ተቋሙ የፈጸመው ተግባር በባህርዩ ዳኝነታዊ ነው ወይስ አይደለምየሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ የውሳኔ ሰጭውን የስልጣን እና የተግባር ዓይነት መለየት በህጉ የአፈጻጸም ወሰን ላይ የራሱ ጉልህ እንደምታዎች አሉት፡፡ ጠቅለል ባለ አነጋገር የአስተዳደር /ቤቶች ዳኝነታዊ ወይም የህግ አውጭነት ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ጊዜ ካልሆነ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በአስተዳደር ስልጣን ውስጥ የሚወድቁት ድርጊቶች በመደበኛ /ቤቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸው አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር አስተዳደራዊ ውሳኔ ወይም ድንጋጌ ባልሆነ ጉዳይ ላይ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አይኖራቸውም፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች ዳኝነታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሰጡ መሰረታዊ የውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች ተፈጻሚ መሆን ይጀምራሉ፡፡

Jul 26, 2020

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር ____2012

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር___2012 አዋጅ
ቁጥር 25/1988 እና አዋጁን ለማሻሻል የወጡ ቁጥራቸው 138/1991፣254/1993፣321/1995 እና 454/1997 የሆኑ አዋጆች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡፡ 2) ይህን አዋጅ የሚቃረን ወይም በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን የሚመለከት ማናቸውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ የፌዴራል ፍርድቤቶችአዋጅቁጥር 25/1988 እናአዋጁንለማሻሻል የወጡ ቁጥራቸው 138/1991፣254/1993፣321/1995 እና 454/1997 የሆኑ አዋጆች

የመንስዔው መንስዔ የውጤቱ መንስዔ ነው። እያደገ ከሆነ ዛፍ እንለዋለን፡፡ ካልሆነ እንጨት ነው።

የመንስዔው መንስዔ የውጤቱ መንስዔ ነው።    

እያደገ ከሆነ ዛፍ እንለዋለን፡፡ 
ካልሆነ እንጨት ነው።   

Jul 23, 2020

የህጉ ምንጮች

የህጉ ምንጮች

የአስተዳደር ህግ የሚመራባቸው መርሆዎች እና ደንቦች ከተለያዩ ምንጮች ይገኛሉ፡፡ 

የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ የዛችን አገር ፖለቲካዊና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትና አወቃቀር የሚያንጸባርቅና ከዚሁ አንጻር የተቀረጸ እንደመሆኑ እነዚህን ምንጮች ወጥ በሆነ መልኩ ማስቀመጥ ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከአጠቀላይ ምልከታ በመነሳት ምንጮቹን እንደሚከተለው መዘርዘር ይቻላል፡፡
ህገ መንግሰት
የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ መልክና ቅርጽ ምን እንደሚመስል ለመረዳት መነሻችን የዛች አገር ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ነው፡፡ ብዙዎቹ የአስተዳደር ህግ መርሆዎች መሰረታቸው የተተከለው በህገ መንግስት ላይ ከመሆኑም በላይ ወሰንና አፈጻጸማቸው እንዲሁ ለብቻው ተነጥሎ የቆመ አይደለም፡፡ የአስተዳደር ህግ ተፈጻሚነት የሚያገኘው በህገ መንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ነው፡፡a
ህግ
የመንግስት ስልጣን ዋነኛ ምንጩ በህግ አውጭው የሚወጣው ህግ ሲሆን በአስተዳደር ህግ ውስጥ በተለምዶ ‘ማቋቋሚያ አዋጅ’ ወይም ‘እናት ህግ’ እየተባለ ይጠራል፡፡ በአገራችን በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ በተዋቀረው ህግ አውጪ አካል የሚወጣው አዋጅb የአስተዳደር መስሪያ ቤቶችን ስልጣን በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ ስለሆነም ይህ አዋጅ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ በጥልቀት ሊመረምርና ሊተነተን ይገባዋል፡፡
ህግ አውጪው ስልጣን ከመስጠት በተጨማሪ ስልጣኑ ተግባር ላይ የሚውልበትን መንገድና ስርዓት ይደነግጋል፡፡ በስልጣን መገልገል ሂደት ተፈጻሚ የሚሆነው ስነ-ስርዓት አብዛኛውን ጊዜ ስልጣን በሚሰጠው አዋጅ ላይ ይካተታል፡፡ በሌላ መልኩ ህግ አውጪው በሁሉም ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ላይ በጠቅላላው ተፈጻሚ የሚሆን ወጥ ደንብ በማስቀመጥ ሁሉን አቀፍ ስርዓት ሊዘረጋ ይችላል፡፡
በዚህ ረገድ በአሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1946 ዓ.ም የወጣው የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ደንብ (Administrative Procedure Act) ተጠቃሽ ነው፡፡ በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦችና ስርዓቶች አስገዳጅነት ያላቸው እንደመሆኑ መጠን ስነ-ስርዓቱን የሚጥስ ውሳኔ ጸንቶ የሚቆምበት የህግ መሰረት አይኖርም፡፡ በአጠቃላይ የስልጣን ምንጭ የሚወሰንበት መንገድ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡

ደንብና መመሪያ

በአገራችን በተለይም በፌደራል መንግስቱ ደረጃ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የተለያዩ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በውክልና በሚተላለፍላቸው ስልጣን መሰረት ደንብና መመሪያ ያወጣሉ፡፡ የእነዚህ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች አወጣጥ ስርዓት እንዲሁም ህጋዊነታቸውና ህገ መንግስታዊነታቸው የሚረጋገጥበት መንገድ በህጉ አብይ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሆኗል፡፡
በእርግጥ የእያንዳንዱ ደንብና መመሪያ ይዘት ከአስተዳደር ህግ ጥናት ወሰን ውጭ ነው፡፡ ህጉ እንደ ስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያነቱ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ መውጣቱን ማረጋገጥ አይነተኛ ዓላማው ነው፡፡ በውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን በአስተዳደር ህግ ውስጥ ያለው ቦታ መቃኘት ያለበትም ከዚሁ ነጥብ አንፃር ነው፡፡ ለህጋዊነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ደንብና መመሪያው ላይ አስገዳጅ ውጤት ኖሯቸው የተደነገጉት ጉዳዮች ስልጣን በሰጠው አዋጅ ስር የተሸፈኑ መሆናቸውን መመርመርን ይጠይቃል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔዎች
መደበኛ ፍ/ቤቶች የስልጣን መገልገልን ህጋዊነትና ፍትሐዊነት በመቆጣጠር ለግለሰቦች መብትና ነፃነት መጠበቅ የሚያበረክቱ አስተዋጽኦ በአስተዳደር ህግ ጥናት ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ ፍ/ቤቶች አስተዳደሩ በህግ እንዲመራ እና ለህጋዊነት መርህ ተገዢ እንዲሆን በተጨማሪም በህግ የተሰጠውን ስልጣን በፍትሀዊ መንገድ እንዲገለገል የተለያዩ መለኪያዎችንና መስፈርቶችን በማስቀመጥ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ህገ-መንግስታዊ ሚናቸው የመልካም አስተዳደር እሴቶች ገንቢ ተቋማት ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር የፌደራል እና የክልል መደበኛ ፍርድ ቤቶች በአስተዳደራዊ ክርክር የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች ለአስተዳደር ህግ ጥናት ግብዓት ናቸው፡፡ በተለይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም በመላ አገሪቱ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅነት ያለው እንደመሆኑ የአስተዳደር ህግን ተግባራዊ አፈጻጸም ለመመዘን ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
ከመደበኛ ፍ/ቤቶች በተጨማሪ በአስተዳደር ተቋማት ውስጥ ወይም ለብቻቸው ገለልተኛ ሆነው የሚቋቋሙት በተለምዶ ‘የአስተዳደር ፍ/ቤት’ በሚል የሚታወቁት የአስተዳደር ጉባዔዎች (Administrative Tribunals) የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የአንዲት አገር የአስተዳደር ህግ እና የአስተዳደር ፍትህ ምን እንደሚመስልና ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት አጋዥ ምንጮች ናቸው፡፡
ያም ሆኖ የመደበኛ ፍ/ቤት ሆነ የአስተዳደር ጉባዔዎች ውሳኔዎች በአስተዳደር ህግ ውስጥ ያላቸው ቦታ ውስን ነው፡፡ በየአስተዳደር መስሪያ ቤቱ በየጊዜው በሚሰጡት ውሳኔዎችና በሚወጡት ደንብና መመሪያዎች አማካይነት በዜጋው ላይ የሚፈጸሙት በደሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቢሆንም የፍ/ቤትን ደጃፍ የሚረግጡት ግን በጣት የሚቆጠሩት ናቸው፡ ከሚቀርቡት አቤቱታዎች መካከልም በተለያዩ የስነ-ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች የተነሳ ዳኝነት ሳይታይ አብዛኛዎቹ ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ውሳኔዎቹ አጠቃላዩን የአስተዳደር ሂደት ባህርይ እና አካሄድ ገላጭ ወይም ወካይ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

ልዩ ዝግጅት በወቅታዌ የሀገራችን ጉዳይ ላይ

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!