SUBSCRIBE

Search This Blog

May 25, 2021

የተሻረው እና አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ድንጋጌዎች ንጽጽር በተለይም

የተሻረው እና አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ድንጋጌዎች ንጽጽር በተለይም  

መግቢያ

በሀገራችን የኤክሳይ
ዝ ታክስን በተመለከተ በሥራ ላይ የነበረው አዋጅ ቁጥር 307/2002 (እንደተሻሻለ) ተሽሮ በአዲስ የኤክሳይዝ አዋጅ ቁጥር 1186/2020 የተተካ ስለመሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህ ጽሁፍ ሁለቱ አዋጆች የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎችን፤ ታክሱን የመክፈል ግዴታን እና ታክሱ ስለሚሰላበት ስሌትን በተመለከተ ያስቀመጡትን ድንጋጌዎች ከጨው ምርት ጋር በተያያዘ በወፍ በረር ለማነጻጽር ነው፡፡

1. በተሻረው እና በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መሰረት ታክሱ የተጣለባቸው ዕቃዎች፤ ታክሱን የመክፈል ግዴታ እና ታክሱ የሚሰላበት ስሌት፤

1.1 የተሻረው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ፤

በቀድሞ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/2002 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 4 መሰረት የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎች በአገር ውስጥ ሲመረቱ (When produced locally) ወይም ከውጭ ወደሀገር ውስጥ ሲገቡ (When imported) የኤክሳይዝ ታክስ እንደሚከፈልባቸው የሚደነግግ ሲሆን፤ ታክሱን የመክፈል ግዴታ በተመለከተ በአዋጁ አንቀጽ 6 መሰረት በአገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለው በአምራቹ (by the Producer) ላይ ሲሆን ወደ አገር ውስጥ በገቡ ዕቃዎች ላይ ደግሞ የመክፈል ግዴታ የተጣለው በአስመጭው (by the importer) ነው፡፡

በተሻረው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የቃል ትርጉም ላይ ለአምራች የተሰጠው ትርጉም ባይኖርም ከአዋጁ ጠቅላላ ድንጋጌ አምራች ማለት የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸውን ዕቃዎችን የሚያመርት/Producer/ እንጂ፤ የሚፈበርክ/Manufacturer/ ማለት እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ Producer ተብሎ በተሻረው አዋጅ ለተጠቀሰውም ሆነ Manufacturer ተብሎ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ለተጠቀሰው የኢንግሊዘኛ ቃል የተሰጠው የአማረኛ አቻ ትርጉም አምራች ቢሆንም Producer and Manufacturer የተለያዩ ትርጉም ያለቸው ቃላቶች ናቸው፡፡ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2016 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 14 መሰረት “Manufacturing” includes any formulation, alteration, assembling or processing…or operation activity carried out by using industry ማለት ነው፡፡

ይህ የቃል ትርጉም በአዋጁ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 13 ለኢንዱስትሪ ከተሰጠው ትርጉም ጣምራ ንባብ መደራት የሚቻለው Manufacturing ማለት ኢንዱስትሪን በመጠቀም በሞተር ኃይል የመቀመም፤ የመለወጥ፤ የመገጣጠም፤ የማሰናዳት ወይም የማምረት ሥራን ማከናወን ማለት ነው፡፡  ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በተሻረው አዋጅ መሰረት በጨው ላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለው በአምራቹ (Producer) በመሆኑ በጨው መሸጫና መግዥ የዋጋ ግንባታ ላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ የተካተተው በጥሬ ጨው አምራች ገበሬዎች የመሸጫ ዋጋ ብር 257.95 ላይ እንጂ፤ ኢንዱስትሪን በመጠቀም ጥሬ-ጨው በማሰናዳትና በማቀነባበር /Processing/ ለምግብ ወይም ለሌላ ጥቅም በሚፈበርኩ /Manufacturer/ ፋብሪካዎች የመሸጫ ዋጋ ብር 529.68 ላይ የኤክሳይዝ ታክስ አልተካተተም፡፡  

በተሻረው አዋጅ አንቀጽ 5 መሰረት በአገር ውስጥ ለተመረቱ ዕቃዎች የኤክሳይዝ ታክስ ስሌት የሚሰላው ከማምረቻ ወጪ (cost of production) ዋጋ ላይ ሲሆን፤ በአዋጅ አንቀጽ 2(8) መሰረት የማምረቻ ወጪ ማለት፡-ለምርት ተግባር በቀጥታ የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችና የጉልበት ዋጋ፤ ቀጥተኛ ያልሆኑ ግብዓቶች ወጪ እና ኦቨር ሄድ ወጪ ያካትታል፡፡ ለምሳሌ የቀድሞ የንግድ ሚኒስቴር ህዳር/2009 ዓ.ም የጥሬ ጨው አምራቾች በማምረቻ ቦታ እና በፋብሪካ የተቀነባበረ አዮዲን ያለው ጨው እስከ ተጠቃሚው ድረስ የዋጋ ግንባታ እና የገበያ ሰንሰለት በሚል በማወጣውና ተግባራዊ በመሆን በሚገኘው ሰነድ ውስጥ በተራ ቁጥር 12 ላይ አንድ ኩንታል ጥሬ ጨው ለማምረት የተያዘው የማምረቻ ወጪ ብር 95.12 ነው፡፡ ይህ ማለት በተሻረው አዋጅ ጨው 30% የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ዕቃ/ምርት/ በመሆኑ የጨው አምራች የሆነ ገበሬ ኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት ሲሆን፤  ይህ አምራች ገበሬ የኤክሳይዝ ታክሱን የሚከፍለው ለማምረቻ ወጪ ተብሎ ከተያዘው ብር 95.12 በመሆኑ በኩንታል ሊከፍል የሚገደደው 30% × 95.12 = ብር 28.54 ነው፡፡

ማስታወሻ

የተሻረው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የኤክሳይዝ ታክስ ስሌት እንዲሰላ ግዴታ ሲጥል የነበረው ከማምረቻ ወጪ (cost of production) ዋጋ በመሆኑ፤ የቀድሞ የኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስቴር ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 011.36/7879 የጥሬ ጨው አምራቾች በማምረቻ ቦታ እና በፋብሪካ የተቀነባበረ አዮዲን ያለው ጨው እስከ ተጠቃሚው ድረስ የመግዥና መሸጫ ዋጋ እና የገበያ ሰንሰለት ተግባራዊ እንዲሆን ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ ተካቶ የሚገኘው በጥሬ ጨው አምራቾች የመሸጫ ዋጋ ብር 257.95 ላይ እንጂ በፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ ብር 529.68 ላይ የኤክሳይዝ ታክስ አልተካተተም፡፡

2. አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ፤

በሌላ በኩል በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2020 አንቀጽ 5 መሰረት የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለው በ3 ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ይህም፡- a) በተፈቀደለት አምራች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች (Manufactured in Ethiopia by a licensed manufacturer); b) ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎች; እና c) በተፈቀደለት አገልግሎት ሰጪ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጡ የአክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው አገልግሎቶች ናቸው፡፡

በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 6 መሰረት የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለው ከላይ ከa እስከ c በተጠቀሰው ቅደም ተከተል መሰረት የተፈቀደለት አምራች (Licensed manufacturer) አስመጪው እና አገልግሎቱን ለመስጠት የተመዘገበው ሰው ናቸው፡፡ የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ ከተጣለባቸው 3 አካላት መካከል ጸሃፊው በተፈቀደለት አምራች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጓል፡፡

በአዋጅ አንቀጽ 2(20) መሰረት የተፈቀደለት አምራች (Licensed manufacturer) ማለት የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎችን የሚያመርት በአዋጁ አንቀጽ 17 መሰረት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ማለት ነው፡፡ በአዋጁ በአንቀጽ 18(2) መሰረት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ዕቃዎች ለሚያመርት ሰው የሚሰጥ ፈቃድ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፡-

  1. አምራቹ አንዲያመርት የተፈቀደለት ዕቃ ምድብ እና
  2. አምራቹ ምርቶችን እንዲያመርት የተፈቀደለትን ፋብሪካ ናቸው፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 18/3ና4/ መሰረት ፈቃድ የተሰጠው አምራች፡ በተሰጠው ፈቃድ የተመለከተው ፋብሪካ ማምረት የሚችለው በፈቃዱ የተመለከተውን ዕቃ ምድብ ብቻ እንደሆነ እና በተሰጠው ፈቃድ የተመለከተው ፋብሪካ ማምረት የሚችለው በፈቃዱ ላይ አምራች በሚል የተመለከተው ሰው ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡

በፈቃድ የተመለከተ ዕቃ ምድብ ማለት የኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም ባሳተመው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደቦች መመሪያ መሰረት በንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ ላይ የተመለከተ የሥራ መደብ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ አምራች በፈቃዱ ላይ የተመለከተው ዕቃ ምደብ የምግብ ጨው ማምረት ከሆነ ይህ ባለፈቃድ በፋብሪካው ማምረት የሚችለው የምግብ ጨው ብቻ ሲሆን ባለፈቃዱ በፈቃዱ ላይ አምራች መባል አለበት፡፡ በሌላ አገላለጽ አምራች ተብሎ ባልተገለጸ ፈቃድ እና በፈቃዱ ላይ ያልተገለጸን ዕቃ ምድብ ማምረት ክልክል ነው፡፡

በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 2(20) መሰረት ፋብሪካ/Factory/:- ማለት ፈቃድ የተሰጠው አምራች የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸውን ዕቃዎች የሚያመርትበት ወይም የሚያከማችበት ሥፍራ ሲሆን፤ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸውን ዕቃዎች ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ለገበያ የሚቀርቡበትን ማናቸውንም የአምራቹን የሥራ ቦታ አይጨምርም፡፡ ይህ ማለት ባለፈቃዱ ያመረታቸውን ዕቃዎች ለምሳሌ የምግብ ጨው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል መጋዘን ወይም ሱቅ በማከማቸት ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብበት ቦታ እንደ ፋብሪካ ሊቆጠር አይችልም፡፡ 

በመሆኑም በጸሃፊው እምነት በተሻረው አዋጅ መሰረት በአገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክሱ የተጣለው በአምራቹ (Producer) በመሆኑ በጨው መሸጫና መግዥ የዋጋ ግንባታ ላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ የተካተተው በጥሬ ጨው አምራች ገበሬዎች የመሸጫ ዋጋ ብር 257.95 ላይ በመሆኑ፤ በተመሳሳይ በአዲሱ አዋጅ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች መካከል በጨው ላይ 25% የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለው በተፈቀደለት አምራች (Licensed manufacturer) በመሆኑ ታክሱ የሚመለከተው አምራች ፋብሪካዎችን እንጂ፤ ጨው አምራች (Producer) ገበሬዎችን  አይመለከትም፡፡

ከላይ እንደተመለከተው በተሻረው አዋጅ አንቀጽ 6 መሰረት በአገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለው በአምራቹ (by the Producer) በመሆኑ እና በአዋጁ አንቀጽ 5 መሰረት አምራቹ የሚከፍለው የኤክሳይዝ ታክስ ስሌት የሚሰላው ከማምረቻ ወጪ (cost of production) ዋጋ ላይ በመሆኑ፤ 30% የኤክሳይዝ ታክስ ተካቶ የሚገኘው በአምራች ገበሬዎች የመሸጫ ዋጋ ብር 257.95 ላይ እንጂ በፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ ብር 529.68 ላይ የኤክሳይዝ ታክስ አልተካተተም፡፡

3. ማጠቃለያ

የቀደም የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ በአዲስ አንዲተካ ከተደረገበት ምክንያቶች መካከል በዋናነት በአዋጅ ቁጥር 1186/2020 መግቢያ/Preamble/ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው በማምረቻ ወጪ ላይ ሲሰላ የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ፤ በፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ እንዲተካ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ በመሆኑ በጸሃፊው እምነት አዲሱ አዋጅ ሲሰራበት የቆየውን የኤክሳይዝ ታክስ ስሌት ከማምረቻ ወጪ ወደ ፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ እንዲተካ ያደረገ በመሆኑ በጨው ላይ የተጣለውን 25% የኤክሳይዝ ታክስ ክፍያ መካተት ያለበት በፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ ብር 529.68 እንጂ፤ በጨው አምራች ገበሬዎች የመሸጫ ዋጋ ላይ ባለመሆኑ፤ ቀደም ሲል በጨው አምራች ገበሬዎች የመሸጫ ዋጋ ላይ ብር 257.95 ተካቶ የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ በአዲሱ አዋጅ ተነስቷል፡፡  

Mar 2, 2021

TYPES OF GOVERNMENT

 Types of Government

Louis XIV, the King of France from 1643 until 1715, is the definition of an absolute monarch. His famous phrase, "I am the State," is an illustration of the power he wielded in France. Louis ruled through a mixture of fear and admiration, but in every case the law extended from himself.

"Off with his head!"
This is a favorite story line to show how cruel a king (or a sultan or emperor) can be. The rules in this type of government are pretty clear. Whatever the ruler says, goes. Of course, many people have had different ideas about how the ruler should govern, and those beliefs support totally different types of government. The rules shape the government's LEGITIMACY, or the degree to which the people accept the authority of the government.

Rule by Man

Countries whose CITIZENS are governed by the absolute decisions of the ruler have not necessarily been unhappy. A government whose king or queen rules justly and wisely may enjoy a great deal of legitimacy as long as the ruler's AUTHORITY is accepted. Sometimes people may accept their leader because they are afraid of the consequences if they don't. In the words of MACHIAVELLI, "It is better to be feared than loved." As long as the feared ruler is seen as bringing about prosperity or protecting the lives of his subjects, it is entirely possible that his people will be happy.

Niccolo Machiavelli wrote political works during the Renaissance. In The Prince, Machiavelli advised his audience that in a system of Rule by Man it was "better to be feared than loved."

An absolute ruler may be accepted because the people believe or accept the idea that God gave him/her the right to rule. This belief is known as divine right, which often has been associated with a MONARCHY, a form of government in which the power of the king or queen is hereditary. A similar idea legitimized the Chinese emperor, whose rule was threatened if his subjects perceived that he had lost the "mandate of heaven."
Rule by man can also take the shape of an OLIGARCHY, or rule by a few elites whose right to rule is based on possession of wealth, social status, military position or achievement. A little more broadly based rule is by ARISTOCRACY (literally, "rule of the highest"), but if the type of government is "rule by man", their decisions are still ARBITARY and absolute.

Rule by Law

RULE BY LAW exists in any political system in which those with power cannot make up all their own rules, but must follow an established CODE OF LAW. In ancient times a Byzantine emperor established JUSTINIAN'S CODE, a set of laws named after him that lived on long after he died. We still follow parts of that code today. The Romans were also known for codifying laws, as was NAPOLEON, Emperor of France, many centuries later.

Napoleon revised the French laws into a single unified code, known as the Code Napoleon. Under the French Empire, the code was implemented throughout Europe. Napoleon is seen in this painting standing next to a copy of the Code written on a scroll.

Today most governments at least claim to be ruled by law. The most common indication is the existence of a written constitution, but the most important question to ask is whether or not the constitution actually is the "blueprint" that determines how and what policies are made. For example, Nigeria officially is a democracy with a written constitution that one dictator after another has ignored. On the other hand, Great Britain has never had a constitution as a single written document, but has for centuries been governed by law. For much of their history, the English had a limited monarchy, or a king or queen who has followed rule of law.
So whether a king can order "off with his head!" depends on the type of government that is accepted in his country. If he sets the rules (rule by man), or if the accepted outside rules allow (rule by law), the victim doesn't have a chance.

Types of government

Feb 13, 2021

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የገቢዎች ሚኒስቴር የደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37 ሕገ-መንግስታዊነት ***********************************

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የገቢዎች ሚኒስቴር የደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37 ሕገ-መንግስታዊነት
***********************************

ደንብ ቁጥር 155/2000 የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች አስተዳደር የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ሲሆን ባሁኑ አደረጃጀት የፌዴራል አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀፅ 36(15) መሰረት የገቢዎች ሚኒስቴር ሰራተኞች አስተዳደር ደንብ ሆኗል። በዚህ ደንብ አንቀፅ 37(1) መሰረት ዳይሬክተሩ (በአሁኑ አወቃቀር ሚኒስቴሩ) በሙስና የተጠረጠረንና እምነት ያጣበትን ማንኛዉምን ሰራተኛ መደበኛዉን ዲሲፕሊን እርምጃ አፈፃፀም ሥረዓት ሳይከተል ከስራ ማሰናብት ይችላል። በደንቡ አንቀፅ 37(2) መሰረት ደሞ ከላይ በአንቀፅ 37(1) መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛዉም የፍርድ አካል ዉሳኔ ወደስራ የመመለስ መብት እንደሌለዉ ተመልክቷል። 

በዚህ ደንብ አንቀፅ 37(1) ድንጋጌ መሰረት ዳይሬክተሩ (በአሁኑ አወቃቀር ሚኒስቴሩ) በሙስና የተጠረጠረንና እምነት ያጣበትን ማንኛዉንም ሰራተኛ መደበኛዉን ዲሲፕሊን እርምጃ አፈፃፀም ሥረዓት ሳይከተል ከስራ ማሰናብት ይችላል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ዳይሬክቴሩ/ሚኒስቴሩ መደበኛዉን ሂደት ሳይከተል (summarily) ሰራተኛዉን ከስራ ለማሰናበት አንደኛ ሰራተኛዉ በሙስና መጠርጠር አለበት ሁለተኛ ዳይሬክተሩ/ሚኒስቴሩ በሙስና ከተጠረጠረዉ ሰራተኛ እምነት ማጣት ይኖርበታል። ሰራተኛዉ በሙስና ተጠርጥሯል ሊባል የሚችለዉ መቼና በምን አይነት ሁኔታ ነዉ? ጥርጣሬዉስ በቂ ጥርጣሬ ነዉ ወይስ ግምታዊ ጥርጣሬ ነዉ? የመጠርጠር ማሳያዎችና ማስረጃዎችስ በማን እይታ ይመዘናሉ? የሚሉ ጉዳዮች በትርጉምም ሆነ በዝርዝር አልተመለከቱም። ይህ መሆኑ ደሞ ከሰዉ ወደ ሰዉ የተለየ እይታ ከመፍጠሩና ወጥነት የጎደለዉ አሰራር እንዲኖር ከማድረግም አልፎ የሰራተኛዉን የስራ ዋስትና ይጎዳል። 

በደንቡ አንቀጽ 37(1) በሚሰጠዉ ዉሳኔ ወጥነት የጎደለዉ አሰራር መኖሩን ለማመላከትም በ2004 በግምገማ ዉጤት ከስራ የተሰናበቱ, በ2010 ጥቆማ ቀርቦባቸዉ የምርመራ ሂደት ተጠናቆ ከስራ የተሰናበቱ,  የዲሲፕሊን ዉሳኔ የተላለፈባቸው ፤ እንዲሁም በሰኔ 22/ 2001 የተፃፈ ደብዳቤ የገቢዉ ዘርፍ ሦስት ተቋማት በአንድ ላይ ተዋህደዉ ሐምሌ 7 ቀን በወጣዉ የኢትዮጵያ ገቢችዎና ጉመሩክ ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 587/2000 እና ይህን ተከትሎ በወጣዉ የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 155/2000 መሰረት አዲስ የሰራተኛ ምደባ ተከናዉኗል በማለት በተጠቀሰዉ ደንብ አንቀጽ 37 መሰረት ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ 
ሁለተኛዉ የድንጋጌዉ መስፈርት የዳይሬክተሩ/የሚኒስቴሩ በሙስና የተጠረጠረ ሰራተኛ ላይ እምነት ማጣት ነዉ። እምነት ማጣት ጥርጣሬን ተከትሎ የሚመጣ ጉዳይ ቢሆንም በሰራተኛዉ ላይ እምነት ማጣት በሚኒስቴሩ ግላዊ እይታ ብቻ የሚመዘን ነዉ፡፡ ይህ ደሞ ሚኒስቴሩ በህግ የተሰጣቸዉን ስልጣን መሰረት በማድረግ የዐይን ቀለሙ ያላማራቸዉን ሰራተኛ በዘፈቀደ እምነት ስላጣሁብህ ከስራ አሰናብቼሃለዉ ቢሉት የሚከለክላቸዉ አይደለም፡፡ በርግጥ ይህ ድንጋጌ ሰራተኛዉን ከሙስናና ብልሹ አሰራር ለመታደግ የተደረገ ጥረት ቢሆንም በግለሰብ እይታ ብቻ (በሚኒስቴሩ እይታ) የሚወሰነዉ ዉሳኔም ለሙስና ተጋላጭ መሆን እንደሚችል ያገናዘበ አይደለም፡፡ 

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ደንብ አንቀጽ 37(1) መሰረት የሚሰጠዉ ዉሳኔ በማኔጅመንት መሆኑንና የሚሰጠዉም ዉሳኔ መነሻዉን የቅ/ጽ ቤት የዲሲፕሊን ኮሚቴ የዉሳኔ ሀሳብ ሆኖ የስነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት የቅ/ጽ ቤቱን የዉሳኔ ሀሳብ እንደገና መርምሮ የዉሳኔ ሀሳቡን ለዳሬክተሩ (ለሚኒስቴሩ) የሚያቀርብና ሚኒስቴሩም እንዲጣራ ካደረገ በኋላ በማኔጅመንት የሚወሰን መሆኑን ከተቋሙ ያገኘነዉ መረጃ ቢያመላክትም ይህ አሰራር በህግ የተደገፈ አሰራር አይደለም፡፡ በህግ የተደገፈ አሰራር አለመሆኑ ደሞ ሀላፊ በተቀያየረ ቁጥር የተለያየ አሰራር ሊዘረጋ ከመቻሉም አልፎ በደንቡ መሰረት ያለምንም ሂደትና ምርመራ በሙስና ጠርጥሬሃለዉ ያለዉን ሰራተኛ ከስራ ለማሰናበት አያግደዉም፡፡ አሁን ባለዉ አሰራርም  ሚኒስቴሩ ከዚህ ልማዳዊ አሰራር በመዉጣት በሙስና ጠርጥሬሃለዉ ያሉትን ሰራተኛ ያለምንም ሂደት ከስራ ለማሰናበት የሚከለክላቸዉ የለም፡፡ ባጭሩ አንቀጽ 37(1) መሰረት ከ 2006 ዓ፣ም ወዲህ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ልማዳዊ አሰራር ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ከመቅረፍ አንፃር ጥሩ ቢሆንም በህግ የተደገፈ አይደለም፡፡ በሚኒስቴሩ የህግ አማካሪና የደንቡ አርቃቂ አንቀጽ 37(1) ተፈፃሚ ለማድረግ የተካተተ ነዉ የተባለዉ የደንቡ አንቀፅ 37(2) እንደሚያመለክተዉ ደሞ ከላይ በአንቀፅ 37(1) መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛዉም የፍርድ አካል ዉሳኔ ወደስራ የመመለስ መብት የለዉም። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለዉ በሚኒስቴሩ/በዳይሬክተሩ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ የሌለዉና የመጨረሻዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ማንኛዉም የፍርድ አካል ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አይኖረዉም ማለት ነዉ፡፡ 

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1) መሰረት ማንኛዉም ሰዉ በፍርድ ሊወሰን የሚገባዉን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠዉ አካል የማቅረብና ዉሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለዉ፡፡ ህገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን ያለዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢሆንም የደንቡ አንቀጽ 37(2) ከህገ መንግስቱ ጋር ማየቱ ተገቢ ነዉ፡፡ አንድ ሰራተኛ ከስራ ያላግባብ ተሰናብቻለዉ የሚል አቤቱታ ለፍርድ ሰጪ አካል የሚያቀርብ ከሆነ ጉዳዩ በፍርድ ሊወሰን የሚገባ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡ በደንብ ቁጥር 155 አንቀጽ 37(1) መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በማንኛዉም የፍርድ አካል ወደ ስራ ሊመለስ አይችልም ማለት ደሞ በፍርድ ሊወሰን የሚገባን ጉዳይ ለማንኛዉም የፍርድ አካል አቅርቦ ወደስራ የመመለስ ዉሳኔን ሊያገኝ አይችልም ማለት ነዉ፡፡ ይህ ድንጋጌ በህገ መንግስቱ የተመለከተዉን በፍርድ አካል የመዳኘት መብትን የሚገድብ ነዉ፡፡ የዚህ ደንብ ህገ መንግስታዊነት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ተብሎ በዚህ መልኩ የሰራተኞችን ይግባኝ የማለትና በማንኛዉም የፍርድ አካል የመዳኘት መብትን መገደቡ ተገቢ ባለመሆኑ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል ሌላ የተሻለ አማራጭ መጠቀሙ ተገቢ ነዉ፡፡ 

በደንቡ አንቀጽ 37(1) የተመለከተዉ ድንጋጌ ከተቋሙ የሥራ ባህሪይ አንጻር አስፈላጊ ነዉ ቢባል እንኳን ይግባኝ የማለት መብትንና በፍርድ አካል የመዳኘትን መብት ሳይገደብ የደንቡን አንቀጽ 37(2) በማዉጣት፤ ጉዳዩን ለሚያየዉ የፍርድ አካል ሰራተኛዉ በሙስና የተጠረጠረ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዳት የተሻለ አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ 
በአንቀጽ 37(1) የሚወሰነዉ ዉሳኔ ግልጽ እንዲሆንና ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም በአድሎ እንዳይወሰን ለማድረግ በተቋሙ ያለዉን የአሁን አሰራር በህግ መደገፍም እንደ ጥሩ አማራጭ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

Feb 10, 2021

ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን

ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን

ስልጣንአብዛኛውን ጊዜ ለመንግስት አካላት የሚደለደለው ስልጣን አሻሚ ባልሆነ አነጋገር ይገለጻል፡፡ ግልጽና ቀጥተኛ ስልጣን በአስተዳደሩ ውስጥ ህጋዊነትን ያሰፍናል፡፡ በተጨማሪም ስልጣንን በመገልገል ረገድ ጥርጣሬና ብዥታን ያስወግዳል፡፡ በተግባር ሲታይ ግን ለውጤታማ አስተዳደር አስፈላጊ የሆኑትን ስልጣናትና ተግባራት መዘርዘር ያዳግታል፡፡ ስለሆነም በግልጽ ስልጣን ውስጥ አስፈላጊ የሆነ በዝምታ የሚተላለፍ ተጓዳኝ ስልጣን ይኖራል፡፡ አንድን ድርጊት ለመፈፀም ግልጽ የሆነ ስልጣን ሲሰጥ የድርጊቱ አካል የሆኑና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በዝምታ የሚሰጥ ስልጣን ስለመኖሩ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የህጉን ዓላማና ግብ እንዲሁም የህጉን ድንጋጌዎች አነጋገር በጥልቀት መፈተሽ ይጠይቃል፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን መኖሩን ለመወሰን የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡የህጉ አነጋገርይህ የህግ አውጭውን ሀሳብ ለማወቅ ወሳኝነት አለው፡፡ ለምሳሌ የመንግስት እና የግል ድርጅት ሠራተኞች ኤጀንሲዎች በሚያስፈጽሟቸው አዋጆች መሰረት ለማናቸውም ዓይነት አበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥና የአበሉን ዓይነትና መጠን የመወሰን ስልጣን አላቸው፡፡ ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በአዋጅ ቁ. 714/2003 እና 715/2003 የተለያዩ ድንጋጌዎች በዝርዝር ተለይተዋል፡፡ ኤጀንሲዎቹ እነዚህን ሁኔታዎች መኖራቸውን የመወሰን ስልጣናቸው ክርክር አያስነሳም፡፡ ለምሳሌ በአዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 41 መሰረት ለሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈለው የጡረታ አበል ሟች ያገኝ ወይም ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 50 በመቶውን ነው፡፡ በዚሁ ድንጋጌ ላይ ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል በመቀበል ላይ እያሉ ጋብቻ ከፈጸሙ አበሉ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ተመልክተዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች መወሰን በኤጀንሲዎቹ ስልጣን ስር ቢሆንም የባልነት ወይም ሚስትነት ጥያቄ በተነሳ ጊዜ ይህንን ማረጋገጥ ከስልጣናቸው ክልል በላይ ነው፡፡ ይህን መወሰን በመደበኛ የዳኝነት አካላት ስልጣን ስር ይወድቃል፡፡ ስለሆነም ‘ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች’ የሚለው አነጋገር በሁለቱም አዋጆች ላይ መለኪያና መስፈርት የተቀመጠላቸውን ሁኔታዎች እንጂ በሌሎች ህጎች የሚወሰኑትን አያካትትም፡፡ የህግ አውጨው ሀሳብም ኤጀንሲዎቹ ለአበል ብቁ የሆኑ የሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈላቸውን መጠንና እና ክፍያውን የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎች እንዲወስኑ እንጂ ከመነሻው ባልነት ወይም ሚስትነትን በተመለከተ ማስረጃ አሰባስበው ውሳኔ እንዲሰጡ አይደለም፡፡በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ወሰንስልጣኑ በጠባቡ ከተሰጠ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ በአንጻሩ ሰፊ የሆነ ስልጣን በውስጡ አስፈላጊ የሆኑ ተጓዳኝ ስልጣናትን ያቅፋል፡፡ለምሳሌ በተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁ. 799/2005 አንቀጽ 13 ላይ እንደተመለከተው አንድ ተሽከርካሪ የመድን ተለጣፊ ምልክት ከሌለው የመድን ሽፋን እንደሌለው ስለሚያስቆጥረው የመድን ዋስትና ሰርተፊኬት እስኪመጣ ድረስ ፖሊስ ተሽከርካሪውን ይዞ የማቆየት ስልጣን አለው፡፡ በዚህ ድንጋጌ የፖሊስ የስልጣኑ ወሰን ጠባብ ነው፡፡ መኪናውን ከመያዝና ለማቆያ በተዘጋጀ ስፍራ ላይ ከማስቀመጥ ውጪ ሊወስድ የሚችለው ተጓዳኝ እርምጃ የለም፡፡ይህንን የፖሊስ ስልጣን አካባቢንና ብክለትን የመቆጣጠር ኃላፊነት ካለባቸው አካላት ስልጣን ጋር ብናነጻጽረው ልዩነቱ በግልጽ ይታያል፡፡ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ወይም የሚመለከተው የክልል ባለስልጣን በአካባቢ ላይ አደጋ እንዳያስከትል ከሚያሰጋ የስራ እንቅስቃሴ ሊመጣ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ድርጅትን እስከ መዝጋት ወይም ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይችላል፡፡ ድርጅትን እስከመዝጋትና ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ስልጣን ድርጅቱን የማሸግና ሠራተኞች እንዳይገቡ የመከልከል እንዲሁም ጉዳት ለመቀነስ የሚያስፈልጉ ተጓዳኝ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ጭምር ያካትታል፡፡
የህጉ ዓላማ የህጉ አጠቃላይ ዓላማና ግብ በግልጽ ከተቀመጠው ስልጣን በተጨማሪ የህጉን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ስልጣናት ስለመኖራቸው አመላካች ነው፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን ሳይኖር የህጉን ዓላማ በተግባር ማሳካት የማይቻል ከሆነ በዝምታ የተሰጠ ስልጣን ስለመኖሩ ግምት ይወሰድበታል፡፡የድርጊቱ ዓይነትና /ባህርይ/ ይዘት
በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ማዕቀብ የሚጥል ድርጊት ወይም እርምጃ ከሆነ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የመቆጣጠር ስልጣን በውስጠ ታዋቂነት የመከልከል ስልጣንን አይጨምርም፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች

የዜጎችን መብትና ጥቅም አስከብሮ ዘላቂ የሀገረ ሰላምና ዲሞክራሳዊ ስርአትን በመጠናከር እኮኖሚየዊ ና ማህበራዊ ዕድገትን ለመፋጠን ፍ/ቤቶች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸዉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኦሮምያ ጠቅለይ ፍ/ቤት ይህን የማይተካ ሚናቸዉን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የእ.ፌ.ዲሪ ሕግ መንግስትም በምዕራፍ 9 አንቀፅ 78-81 ባሉት ድንጋገም ሆነ ህገመንግስቱነን ተከትሎ የወጣዉ የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት መልሶ መቋቋም አወጅ ቁጥር 16/2011 መሰረት የደኝነት ስልጣን የተሰጣቸዉ መሆኑን ደንግጓል፡፡
ራዕይ
በ2012 በክልላችን የህግ የበላይነት ተረጋግጦ የህዝብ አማኔታ አግኝቶ መገኘት፤
እሴቶች
የዳኝነት ነጻነት እና ተጠያቂነት፤
የዳኝነት ግልጻኝነት፤
አድሎ አለማድረግ፤
የህዝብ አገልገይነት፤
ጽኑ አቋም፤
የተቋሙ አላማ
የዳኝንት አገልግሎት ለተገልገዩ ህብረተሰብ መስጠት፤
የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት
የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቋቋያ አዋጅ ቁጥር 16/2011 ባወጣዉ ህግ መሰረት የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አደረጎዋል፡፡
የኦሮምያ ፍርድ ቤቶች መዋቅር 3 ደረጃ አለዉ፡-
1. ወረዳ ፍ/ቤት፤
2. ከፍተኛ ፍ/ቤት፤
3. ጠቅላይ ፍ/ቤት፤
በኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በ 13 ዳሬክተሮች ተደራጅቶዋል፡፡
በከፍተኛ ፍ/ቤት በ 13 የስራ ሂደቶች ተደራጅቶዋል፡፡
በወረዳ ፍ/ቤት በ 12 የስራ ሂደቶች ተደራጅቶዋል፡፡
የወረዳ ፍርድ ቤት ሰልጣን
የወረዳ ፍ/ቤት ግምታቸዉ እስከ 500000 ብር የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ስልጣን አለዉ፤
በግለሰብ ለአለማቀፋዊ ጉዳዮች፤
የማይንቀሳቀስ ንብረት እስከ 1000000 ብር የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ስልጣን አለዉ፤

Fan oromo

Afaan Oromoo

Akka Baayisaa Fufaan qorannoo isaa keessatti ibseen Afaan Oromoo afaan baay’innaan Afrikaa keessatti dubbataman keessaa sadarkaa afraffaa irra jira. Kana jechuun afaan Arabaa, afaan kiSwahiliitiif, afaan Hawusaatti aana jechuudha. Afaan Arabaa fi afaan Kiswaahilii afaan biyya ormaa yoo ta’an, Afaan Oromoo afaan Afrikaa keessatti dubbatamu keessaa tokkoffaa ta’a; osoo mootummaa qabaatee immo addunyaa irraatti sadarkaa sadaffaa ta’u ni mala. Afaan Oromoo kutaa afaanii Afroo-Eshiyaatiik jedhamu jalatti ramadama. Afaan kun Afroo-Asiyaatiik keessaa gare afaanii Kuush jalatti qooddama. Afaanota Kuusha keessa Afaan Oromoo afaan sabni baayyeen dubbatu yoo ta’u, uummata miliyoona 60 ol ta’utu dubbata

Feb 9, 2021

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው ህግ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አድርጎታል። በመሆኑም ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሲሰራ ቆይቷል።

የዜጎችን መብትና ጥቅም አስከብሮ ዘላቂ የአገር ሠላምና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በማጠናር ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን ፍ/ቤቶች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ይህን የማይተካ ከሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የኢ.ፌ.ዲሪ ሕገ መንግስትም በምዕራፍ ዘጠኝ አንቀጽ 78 እስከ 81 ባሉት ድንጋጌዎችም ሆነ ሕገመንግስቱን ተከትሎ የወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው መሰረት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑን ደንግገዋል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው ህግ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አድርጎታል። በመሆኑም ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሲሰራ ቆይቷል።የፌደራል ስርዓቱ በህገ መንግስቱ ካወቀራቸው አደረጃጀቶች መካከል የፍርድ ቤቶች የስልጣን እርከን አንዱ ነው። በመሆኑም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዋጁ በተሰጡት ስልጣኖች መሰረት በፍታብሔር እና በወንጀል የዳኝነት ስልጣን ታውጆ እንዲዳኝባቸው ተሰቶታል። የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዓላማውን ለማሳካት ቀጥሎ የተገለፁት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡-

የፍታብሔር የዳኝነት ስልጣን፡-

1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግምታቸው እስከ 500,000 (አምሰትመቶ ሺ) ብር የሆኑ ጉዳዮችን የማዳኘት ስልጣን አለው ።
2. የፌደራል መንግስቱ ተከራካሪ አካል በሆነበት ጉዳዮች
3. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሆኑ ነዋሪዎች መካከል ክርክር ሲነሳ
4. የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖችና ሰራተኞች በስራቸው ወይም በሃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች
5. የውጭ ሀገር ዜጋ ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
6. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
7. በፌደራል መንግስት በተመዘገቡ ወይም በተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በተመለከቱ ክርክሮች
8. በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
9. በኢንሹራንስ ውል ላይ በሚነሱ ክርክሮች
10. ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን ለማጣራት በሚቀርብ አቤቱታ
11. በአዲስአበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ የፍታብሄር ጉዳዮች

በወንጀል የዳኝነት ስልጣን፡-

1. በፌደራል መንግስቱ የቀረጥና የግብር ገቢዎች በጠቅላላ የገንዘብ ጥቅሞች ላበሚፈጸም ወንጀል
2. የሀሰት ገንዘብን በሚመለከቱ ወንጀሎች
3. በፌደራል መንግስቱ ሰነዶች ላይ የሐሰት ሰራ በመስራት በሚፈጸሙ ወንጀሎች
4. ከአንድ ክልል በላይ ውይም በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በሚሰጡ መገናኛዎች ፀጥታና ነጻነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች
5. የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚመለከቱ ወንጀሎች
6. በአዲስ አበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ በስራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለአውራጃና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!