WELCOME TO MY BLOG WEBSITES! This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution.
Search This Blog
Feb 13, 2021
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የገቢዎች ሚኒስቴር የደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37 ሕገ-መንግስታዊነት ***********************************
Feb 12, 2021
Feb 10, 2021
ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን
ግልጽና ተጓዳኝ ስልጣን
ስልጣንአብዛኛውን ጊዜ ለመንግስት አካላት የሚደለደለው ስልጣን አሻሚ ባልሆነ አነጋገር ይገለጻል፡፡ ግልጽና ቀጥተኛ ስልጣን በአስተዳደሩ ውስጥ ህጋዊነትን ያሰፍናል፡፡ በተጨማሪም ስልጣንን በመገልገል ረገድ ጥርጣሬና ብዥታን ያስወግዳል፡፡ በተግባር ሲታይ ግን ለውጤታማ አስተዳደር አስፈላጊ የሆኑትን ስልጣናትና ተግባራት መዘርዘር ያዳግታል፡፡ ስለሆነም በግልጽ ስልጣን ውስጥ አስፈላጊ የሆነ በዝምታ የሚተላለፍ ተጓዳኝ ስልጣን ይኖራል፡፡ አንድን ድርጊት ለመፈፀም ግልጽ የሆነ ስልጣን ሲሰጥ የድርጊቱ አካል የሆኑና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በዝምታ የሚሰጥ ስልጣን ስለመኖሩ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የህጉን ዓላማና ግብ እንዲሁም የህጉን ድንጋጌዎች አነጋገር በጥልቀት መፈተሽ ይጠይቃል፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን መኖሩን ለመወሰን የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡የህጉ አነጋገርይህ የህግ አውጭውን ሀሳብ ለማወቅ ወሳኝነት አለው፡፡ ለምሳሌ የመንግስት እና የግል ድርጅት ሠራተኞች ኤጀንሲዎች በሚያስፈጽሟቸው አዋጆች መሰረት ለማናቸውም ዓይነት አበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥና የአበሉን ዓይነትና መጠን የመወሰን ስልጣን አላቸው፡፡ ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በአዋጅ ቁ. 714/2003 እና 715/2003 የተለያዩ ድንጋጌዎች በዝርዝር ተለይተዋል፡፡ ኤጀንሲዎቹ እነዚህን ሁኔታዎች መኖራቸውን የመወሰን ስልጣናቸው ክርክር አያስነሳም፡፡ ለምሳሌ በአዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 41 መሰረት ለሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈለው የጡረታ አበል ሟች ያገኝ ወይም ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 50 በመቶውን ነው፡፡ በዚሁ ድንጋጌ ላይ ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል በመቀበል ላይ እያሉ ጋብቻ ከፈጸሙ አበሉ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ተመልክተዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች መወሰን በኤጀንሲዎቹ ስልጣን ስር ቢሆንም የባልነት ወይም ሚስትነት ጥያቄ በተነሳ ጊዜ ይህንን ማረጋገጥ ከስልጣናቸው ክልል በላይ ነው፡፡ ይህን መወሰን በመደበኛ የዳኝነት አካላት ስልጣን ስር ይወድቃል፡፡ ስለሆነም ‘ለአበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች’ የሚለው አነጋገር በሁለቱም አዋጆች ላይ መለኪያና መስፈርት የተቀመጠላቸውን ሁኔታዎች እንጂ በሌሎች ህጎች የሚወሰኑትን አያካትትም፡፡ የህግ አውጨው ሀሳብም ኤጀንሲዎቹ ለአበል ብቁ የሆኑ የሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈላቸውን መጠንና እና ክፍያውን የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎች እንዲወስኑ እንጂ ከመነሻው ባልነት ወይም ሚስትነትን በተመለከተ ማስረጃ አሰባስበው ውሳኔ እንዲሰጡ አይደለም፡፡በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ወሰንስልጣኑ በጠባቡ ከተሰጠ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ በአንጻሩ ሰፊ የሆነ ስልጣን በውስጡ አስፈላጊ የሆኑ ተጓዳኝ ስልጣናትን ያቅፋል፡፡ለምሳሌ በተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁ. 799/2005 አንቀጽ 13 ላይ እንደተመለከተው አንድ ተሽከርካሪ የመድን ተለጣፊ ምልክት ከሌለው የመድን ሽፋን እንደሌለው ስለሚያስቆጥረው የመድን ዋስትና ሰርተፊኬት እስኪመጣ ድረስ ፖሊስ ተሽከርካሪውን ይዞ የማቆየት ስልጣን አለው፡፡ በዚህ ድንጋጌ የፖሊስ የስልጣኑ ወሰን ጠባብ ነው፡፡ መኪናውን ከመያዝና ለማቆያ በተዘጋጀ ስፍራ ላይ ከማስቀመጥ ውጪ ሊወስድ የሚችለው ተጓዳኝ እርምጃ የለም፡፡ይህንን የፖሊስ ስልጣን አካባቢንና ብክለትን የመቆጣጠር ኃላፊነት ካለባቸው አካላት ስልጣን ጋር ብናነጻጽረው ልዩነቱ በግልጽ ይታያል፡፡ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ወይም የሚመለከተው የክልል ባለስልጣን በአካባቢ ላይ አደጋ እንዳያስከትል ከሚያሰጋ የስራ እንቅስቃሴ ሊመጣ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ድርጅትን እስከ መዝጋት ወይም ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይችላል፡፡ ድርጅትን እስከመዝጋትና ወደ ሌላ ቦታ እስከማዛወር የሚደርስ ስልጣን ድርጅቱን የማሸግና ሠራተኞች እንዳይገቡ የመከልከል እንዲሁም ጉዳት ለመቀነስ የሚያስፈልጉ ተጓዳኝ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ጭምር ያካትታል፡፡
የህጉ ዓላማ የህጉ አጠቃላይ ዓላማና ግብ በግልጽ ከተቀመጠው ስልጣን በተጨማሪ የህጉን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ስልጣናት ስለመኖራቸው አመላካች ነው፡፡ ተጓዳኝ ስልጣን ሳይኖር የህጉን ዓላማ በተግባር ማሳካት የማይቻል ከሆነ በዝምታ የተሰጠ ስልጣን ስለመኖሩ ግምት ይወሰድበታል፡፡የድርጊቱ ዓይነትና /ባህርይ/ ይዘት
በግልጽ የተሰጠው ስልጣን ማዕቀብ የሚጥል ድርጊት ወይም እርምጃ ከሆነ ተጓዳኝ ስልጣን ስለመኖሩ በጠባቡ መተርጐም ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የመቆጣጠር ስልጣን በውስጠ ታዋቂነት የመከልከል ስልጣንን አይጨምርም፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች
የዜጎችን መብትና ጥቅም አስከብሮ ዘላቂ የሀገረ ሰላምና ዲሞክራሳዊ ስርአትን በመጠናከር እኮኖሚየዊ ና ማህበራዊ ዕድገትን ለመፋጠን ፍ/ቤቶች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸዉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኦሮምያ ጠቅለይ ፍ/ቤት ይህን የማይተካ ሚናቸዉን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የእ.ፌ.ዲሪ ሕግ መንግስትም በምዕራፍ 9 አንቀፅ 78-81 ባሉት ድንጋገም ሆነ ህገመንግስቱነን ተከትሎ የወጣዉ የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት መልሶ መቋቋም አወጅ ቁጥር 16/2011 መሰረት የደኝነት ስልጣን የተሰጣቸዉ መሆኑን ደንግጓል፡፡
ራዕይ
በ2012 በክልላችን የህግ የበላይነት ተረጋግጦ የህዝብ አማኔታ አግኝቶ መገኘት፤
እሴቶች
የዳኝነት ነጻነት እና ተጠያቂነት፤
የዳኝነት ግልጻኝነት፤
አድሎ አለማድረግ፤
የህዝብ አገልገይነት፤
ጽኑ አቋም፤
የተቋሙ አላማ
የዳኝንት አገልግሎት ለተገልገዩ ህብረተሰብ መስጠት፤
የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት
የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቋቋያ አዋጅ ቁጥር 16/2011 ባወጣዉ ህግ መሰረት የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አደረጎዋል፡፡
የኦሮምያ ፍርድ ቤቶች መዋቅር 3 ደረጃ አለዉ፡-
1. ወረዳ ፍ/ቤት፤
2. ከፍተኛ ፍ/ቤት፤
3. ጠቅላይ ፍ/ቤት፤
በኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በ 13 ዳሬክተሮች ተደራጅቶዋል፡፡
በከፍተኛ ፍ/ቤት በ 13 የስራ ሂደቶች ተደራጅቶዋል፡፡
በወረዳ ፍ/ቤት በ 12 የስራ ሂደቶች ተደራጅቶዋል፡፡
የወረዳ ፍርድ ቤት ሰልጣን
የወረዳ ፍ/ቤት ግምታቸዉ እስከ 500000 ብር የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ስልጣን አለዉ፤
በግለሰብ ለአለማቀፋዊ ጉዳዮች፤
የማይንቀሳቀስ ንብረት እስከ 1000000 ብር የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ስልጣን አለዉ፤
Fan oromo
Afaan Oromoo
Akka Baayisaa Fufaan qorannoo isaa keessatti ibseen Afaan Oromoo afaan baay’innaan Afrikaa keessatti dubbataman keessaa sadarkaa afraffaa irra jira. Kana jechuun afaan Arabaa, afaan kiSwahiliitiif, afaan Hawusaatti aana jechuudha. Afaan Arabaa fi afaan Kiswaahilii afaan biyya ormaa yoo ta’an, Afaan Oromoo afaan Afrikaa keessatti dubbatamu keessaa tokkoffaa ta’a; osoo mootummaa qabaatee immo addunyaa irraatti sadarkaa sadaffaa ta’u ni mala. Afaan Oromoo kutaa afaanii Afroo-Eshiyaatiik jedhamu jalatti ramadama. Afaan kun Afroo-Asiyaatiik keessaa gare afaanii Kuush jalatti qooddama. Afaanota Kuusha keessa Afaan Oromoo afaan sabni baayyeen dubbatu yoo ta’u, uummata miliyoona 60 ol ta’utu dubbata
Feb 9, 2021
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው ህግ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አድርጎታል። በመሆኑም ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሲሰራ ቆይቷል።
የዜጎችን መብትና ጥቅም አስከብሮ ዘላቂ የአገር ሠላምና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በማጠናር ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን ፍ/ቤቶች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ይህን የማይተካ ከሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የኢ.ፌ.ዲሪ ሕገ መንግስትም በምዕራፍ ዘጠኝ አንቀጽ 78 እስከ 81 ባሉት ድንጋጌዎችም ሆነ ሕገመንግስቱን ተከትሎ የወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው መሰረት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑን ደንግገዋል፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25 በ 1988 ባወጣው ህግ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንዱ የዳኝነት መስጫ ተቋም አድርጎታል። በመሆኑም ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሲሰራ ቆይቷል።የፌደራል ስርዓቱ በህገ መንግስቱ ካወቀራቸው አደረጃጀቶች መካከል የፍርድ ቤቶች የስልጣን እርከን አንዱ ነው። በመሆኑም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዋጁ በተሰጡት ስልጣኖች መሰረት በፍታብሔር እና በወንጀል የዳኝነት ስልጣን ታውጆ እንዲዳኝባቸው ተሰቶታል። የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዓላማውን ለማሳካት ቀጥሎ የተገለፁት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡-
የፍታብሔር የዳኝነት ስልጣን፡-
1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግምታቸው እስከ 500,000 (አምሰትመቶ ሺ) ብር የሆኑ ጉዳዮችን የማዳኘት ስልጣን አለው ።
2. የፌደራል መንግስቱ ተከራካሪ አካል በሆነበት ጉዳዮች
3. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሆኑ ነዋሪዎች መካከል ክርክር ሲነሳ
4. የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖችና ሰራተኞች በስራቸው ወይም በሃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች
5. የውጭ ሀገር ዜጋ ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
6. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
7. በፌደራል መንግስት በተመዘገቡ ወይም በተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በተመለከቱ ክርክሮች
8. በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ በሚነሱ ክርክሮች
9. በኢንሹራንስ ውል ላይ በሚነሱ ክርክሮች
10. ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን ለማጣራት በሚቀርብ አቤቱታ
11. በአዲስአበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ የፍታብሄር ጉዳዮች
በወንጀል የዳኝነት ስልጣን፡-
1. በፌደራል መንግስቱ የቀረጥና የግብር ገቢዎች በጠቅላላ የገንዘብ ጥቅሞች ላበሚፈጸም ወንጀል
2. የሀሰት ገንዘብን በሚመለከቱ ወንጀሎች
3. በፌደራል መንግስቱ ሰነዶች ላይ የሐሰት ሰራ በመስራት በሚፈጸሙ ወንጀሎች
4. ከአንድ ክልል በላይ ውይም በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በሚሰጡ መገናኛዎች ፀጥታና ነጻነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች
5. የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚመለከቱ ወንጀሎች
6. በአዲስ አበባና በድሬደዋ ውስጥ በሚነሱ በስራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለአውራጃና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
Feb 8, 2021
PDF DOCUMENTS AND FILE
WordPress
WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution



































































































































































































































