SUBSCRIBE

Search This Blog

Jun 28, 2020

የአስተዳደር ስልጣን

አስተዳደራዊ ስልጣን

አስተዳደራዊ ስልጣን

ደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያከናውኗቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋነኛ ስልጣንና ተግባር ህግ ማውጣት አሊያም ዳኝነት መስጠት ሳይሆን ማስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደራዊ ስልጣን ከህግ ማውጣት እና ዳኝነት መስጠት ውጪ ያሉትን ተግባራት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ የአስተዳደር /ቤቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ይህን የእለት ተእለት የአስተዳደር ስራ በማከናወን ነው፡፡
በዚህ ስልጣን ስር ከሚወድቁ በርካታ ምሳሌዎችን መካከል ሪፖርት ማቅረብ፣ ፓስፖርት መስጠት፣ ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ፀጥታ ማስከበር፣ ክስ መመስረት፣ እድገትና ሹመት መስጠት፣ ምርመራ፤ ቁጥጥርና ክትትል ማካሄድ የምክር ሀሳብ መስጠት ወዘተ ሁሉም የአስተዳደር /ቤቶች አስተዳደራዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ስራዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ተግባራት የህግ መጣስ መኖርን አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የመረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ስርዓት የንግድ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱ በአካል ተገኝቶ ቀጥተኛ እና የአካባቢ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና የማጣራት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡
የመርማሪነት ስራ ህጉ ልዩ ስልጣን በሰጣቸው መርማሪዎች የሚከናወን ሲሆን የምርመራ ሂደቱም በህግ ማእቀፍ ውስጥ ይመራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የፖሊስ የምርመራ ተግባር ነው፡፡ ፖሊስ ወንጀል ሲፈጸም ወይም ተፈጽሟል የሚል መረጃ ከደረሰው አሊያም ተገቢ ጥርጣሬ ካደረበት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል በመገኘት ተጨባጭ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ እና ተጠርጣሪውን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ስልጣናት አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአስተዳደር /ቤቶች የመርማሪነት፣ የቁጥጥርና ክትትል ስልጣን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ለፖሊስ ከተሰጠው ስልጣን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡
በአስረጂነት በተወሰኑ ህጎች ለተቆጣጠሪዎች የተሰጣቸው መጠነ ሰፊ ስልጣን በማጣቀሻነት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንa
ሳያሳውቁ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባት
ማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት የመጠየቅ
ከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት፣ ማህደር ወይም ሌላ ሰነድ መፈተሽ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳት
የማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በህይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመር
የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 300/1995 ወይም ሌላ ህግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፍቶግራፍ ማንሳት፣ መለካት፣ መሳል ወይም መፈተሽ
አዋጁን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ህግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሳሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝ
የዱር እንስሳት ቁጥጥር ሠራተኛb
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶች ተደብቀዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ወደ ማንኛውም ሰው መሬት፣ ህንጻ፣ ድንኳን፣ ተሸከርካሪ፣ የአየር መንኮራኩር ወይም ጀልባ ውስጥ የመግባትና የመፈተሸ እንዲሁም ሻንጣ ወይም እሽግ የመፈተሸ
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶችን እንዲሁም ጥፋቱ የተፈጸመባቸውን መሳሪያዎች እንዲወረሱ ለማድረግ እንዲቻል በቁጥጥር ስር የማድረግና የሚመለከተው አካል ባወጣው የመመዝገቢያ ቅፅ መሰረት ተገቢውን ደረሰኝ ሰጥቶ የመረከብ
የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 541/1999 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በመተላለፍ ጥፋት ሲፈጽም የተገኘን ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ማስረከብ
የደን ውጤት ተቆጣጣሪc
የደን ውጤቶችን የጫነ ወይም ለመጫኑ የሚጠረጠርን ማናቸውንም ማጓጓዣ በደን መግቢያና መውጫዎች እንደአስፈላጊነቱ በሚመረጡ የሀገር ውስጥ እና የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አስቁሞ መፈተሸ
የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 542/1999 በመተላለፍ ተዘጋጅተው ሲጓጓዙ ወይም ተከማችተው የተገኙ የደን ውጤቶችን ከድርጊቱ ተጠያቂዎች ጋር የመያዝ
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርd
የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁ. 602/2000 ለማስፈጸም የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ቡና ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚገመትን መጋዘን፣ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድርጅት፣ ማጓጓዣ ወይም ማናቸውም ሌላ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የመፈተሽ፣ህገ ወጥ ቡና ሲያዝ የማሸግ፣ ምርቱን የማገድ፣ የመያዝ፣ ህገ ወጥነታቸው የማያጠራጥር ሲሆን የቡናው ባለቤት ለፍርድ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመውረስና የመሸጥ.

Jun 18, 2020

አስተዳደራዊ ስልጣን

አስተዳደራዊ ስልጣን
ደንብና መመሪያ ማውጣት እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ እና እርምጃ መውሰድ ህግ አስፈፃሚ አካላት ህግና ፖሊሲን ለመተግበር የሚያከናውኗቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋነኛ ስልጣንና ተግባር ህግ ማውጣት አሊያም ዳኝነት መስጠት ሳይሆን ማስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደራዊ ስልጣን ከህግ ማውጣት እና ዳኝነት መስጠት ውጪ ያሉትን ተግባራት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ የአስተዳደር /ቤቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ይህን የእለት ተእለት የአስተዳደር ስራ በማከናወን ነው፡፡
በዚህ ስልጣን ስር ከሚወድቁ በርካታ ምሳሌዎችን መካከል ሪፖርት ማቅረብ፣ ፓስፖርት መስጠት፣ ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ፀጥታ ማስከበር፣ ክስ መመስረት፣ እድገትና ሹመት መስጠት፣ ምርመራ፤ ቁጥጥርና ክትትል ማካሄድ የምክር ሀሳብ መስጠት ወዘተ ሁሉም የአስተዳደር /ቤቶች አስተዳደራዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ስራዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ተግባራት የህግ መጣስ መኖርን አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የመረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ስርዓት የንግድ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱ በአካል ተገኝቶ ቀጥተኛ እና የአካባቢ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና የማጣራት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡
የመርማሪነት ስራ ህጉ ልዩ ስልጣን በሰጣቸው መርማሪዎች የሚከናወን ሲሆን የምርመራ ሂደቱም በህግ ማእቀፍ ውስጥ ይመራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የፖሊስ የምርመራ ተግባር ነው፡፡ ፖሊስ ወንጀል ሲፈጸም ወይም ተፈጽሟል የሚል መረጃ ከደረሰው አሊያም ተገቢ ጥርጣሬ ካደረበት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል በመገኘት ተጨባጭ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ እና ተጠርጣሪውን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ስልጣናት አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአስተዳደር /ቤቶች የመርማሪነት፣ የቁጥጥርና ክትትል ስልጣን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ለፖሊስ ከተሰጠው ስልጣን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡
በአስረጂነት በተወሰኑ ህጎች ለተቆጣጠሪዎች የተሰጣቸው መጠነ ሰፊ ስልጣን በማጣቀሻነት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንa
ሳያሳውቁ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባት
ማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት የመጠየቅ
ከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት፣ ማህደር ወይም ሌላ ሰነድ መፈተሽ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳት
የማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በህይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመር
የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 300/1995 ወይም ሌላ ህግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፍቶግራፍ ማንሳት፣ መለካት፣ መሳል ወይም መፈተሽ
አዋጁን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ህግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሳሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝ
የዱር እንስሳት ቁጥጥር ሠራተኛb
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶች ተደብቀዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ሲኖር ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ወደ ማንኛውም ሰው መሬት፣ ህንጻ፣ ድንኳን፣ ተሸከርካሪ፣ የአየር መንኮራኩር ወይም ጀልባ ውስጥ የመግባትና የመፈተሸ እንዲሁም ሻንጣ ወይም እሽግ የመፈተሸ
ሕግን በመተላለፍ በይዞታ ስር የተደረጉ የዱር እንስሳት ወይም የዱር እንስሳት ውጤቶችን እንዲሁም ጥፋቱ የተፈጸመባቸውን መሳሪያዎች እንዲወረሱ ለማድረግ እንዲቻል በቁጥጥር ስር የማድረግና የሚመለከተው አካል ባወጣው የመመዝገቢያ ቅፅ መሰረት ተገቢውን ደረሰኝ ሰጥቶ የመረከብ
የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ ቁ. 541/1999 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በመተላለፍ ጥፋት ሲፈጽም የተገኘን ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ማስረከብ
የደን ውጤት ተቆጣጣሪc
የደን ውጤቶችን የጫነ ወይም ለመጫኑ የሚጠረጠርን ማናቸውንም ማጓጓዣ በደን መግቢያና መውጫዎች እንደአስፈላጊነቱ በሚመረጡ የሀገር ውስጥ እና የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አስቁሞ መፈተሸ
የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 542/1999 በመተላለፍ ተዘጋጅተው ሲጓጓዙ ወይም ተከማችተው የተገኙ የደን ውጤቶችን ከድርጊቱ ተጠያቂዎች ጋር የመያዝ
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር
የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁ. 602/2000 ለማስፈጸም የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ቡና ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚገመትን መጋዘን፣ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድርጅት፣ ማጓጓዣ ወይም ማናቸውም ሌላ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የመፈተሽ፣ህገ ወጥ ቡና ሲያዝ የማሸግ፣ ምርቱን የማገድ፣ የመያዝ፣ ህገ ወጥነታቸው የማያጠራጥር ሲሆን የቡናው ባለቤት ለፍርድ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመውረስና የመሸጥ

Jun 15, 2020

የዕግድ ትዕዛዝ ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡

የዕግድ ትዕዛዝ

ዕግድ በፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ራሱን ችሎ እንደ ውሳኔ ወይም በክርክሩ መሀል እንደ ጊዜያዊ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ዕግድ በውጤቱ ተከሳሹ ወይም ተጠሪው አንድ 
ድርጊት ከመፈፀም እንዲታቀብ እንዲሁም የዕግዱ ትዕዛዝ አስገዳጅ ከሆነ አንድን ድርጊት በተወሰነ አይነት መንገድ እንዲፈጽም ያስገድደዋል፡፡

 በኢትዮጵያ ከውል ውጭ በሚደርስ ኃላፊነት ሕግ ውስጥ የእግድ ትዕዛዝ የተፈፃሚነት ወሰኑ ተከሳሹ ጉዳት የሚያመጣ ነገር እንዳይሰራ በመስራት ላይ ቢገኝ እንዳይቀጥል ወይም እንደገና እንዳይጀመር ማገጃ እንጂ አንድ ተግባር እንዲፈጸም ማስገደጃ እንዳልሆነ ከፍ// 2121(1) ድንጋጌ እንረዳለን፡፡ ዕግድ ማገጃ እና ማስገደጃ ትዕዛዛትን አጠቃሎ ሲይዝ ህገ ወጥ አስተዳደራዊ ተግባራትን ብቻ ሳይሆን በቸልተኝነት ግዴታን ባለመወጣት የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን ለመቅረፍ የሚያስችል ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡
ተፈፃሚነቱ ደረቅና ፍፁም ሳይሆን ተስማሚ ባልሆኑ ሁኔታዎች ሁሉ ዳኛው ትዕዛዙን ላለመስጠት ሰፊ ስልጣን አለው፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2021/2/ እንደተመለከተው በሁለት ሁኔታዎች ትዕዛዙ ላይሰጥ ይችላል፡፡ ይኸውም ጥያቄ የተነሳበት ድርጊት በከሳሹ ላይ ጉዳት እንደሚያመጣ አሳማኝ ምክንያት ከሌለና እንዲሁም ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ኪሳራውን በመክፈል ለመካስ ከተቻለ ፍርድ ቤት ዳኝነት ለመንፈግ ሰፊ ስልጣን አለው፡፡
የዕግድ ትዕዛዝ ራሱን የቻለ ውሳኔ እንደመሆኑ ክርክሩ ታይቶ /ቤቱ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ በፍ////. 154 መሰረት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህ በባህሪዩ ዘላቂ መፍትሄ ሳይሆን ውሳኔ እስከ ውሳኔ ቀን ሊደርስ የሚችልና የማይመለስ ጉዳት እንዳይደርስ በጊዜያዊነት የሚሰጥ ከለላ ነው፡፡ ትዕዛዙ የተላለፈለት ተከራካሪ ዕግዱን ባያከብር ድርጊቱ እንደ ፍርድ ቤት ንቀት ተቆጥሮ ቅጣት ይጣልበታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በፍ// 2121 መሰረት በቋሚነት የሚሰጥ የዕግድ ትዕዛዝ ተጨማሪ የአፈፃፀም ማመልከቻ ሳያስፈልግ ወዲያውኑ ተፈፃሚነት ሊኖረውና በተከሳሹ ሊከበር ይገባዋል፡፡ ይህ ባልሆነበት ጊዜ /ቤቱ በወንጀል ህጉ የተመለከተውን የፍርድ ቤት ንቀት ድንጋጌ በመጥቀስ ተገቢውን ቅጣት ይወስንበታል፡፡
የዕግድ ትዕዛዝ የሚጠይቅ አመልካች ወይም ከሳሽ በድርጊቱ ምክንያት በንብረቱ ወይም በመብቱ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት እንደሚደርስበትና በጉዳዩ ጥቅም ያለው መሆኑን ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ድርጊቱ ከስልጣን በላይ ወይም አላግባብ በስልጣን መገልገል መሆኑ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በሌሎች አገሮች ግን ይህን የጠበቀ የከሳሽነት ብቃት (standing) በማላላት የተለየ ልዩ ጉዳት በአመልካቹ ላይ ባይደርስም ከማንም ሰው ጋር በሚጋራው ህዝባዊ መብቱ ላይ ጠቅላላ ጉዳት ሲደርስበት የዕግድ አቤቱታ የማቅረብ መብት ይኖረዋል፡፡

የፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችን

የፅንሰ ሀሳቡ አፈጻጸም በአገራችን

ስለ አገራችን ፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን ከመወራቱ በፊት መጀመሪያ የጽንሰ ሀሳቡ ይዘትና አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ጥቂት  መንደርደሪያ  ነጥቦችን  መሰንዘር  ያስፈልጋል፡፡  አጣሪ  ዳኝነት  በአገራችን  የህግና  ህገ  መንግስታዊ  ስርዓት  ውስጥ  ያለውን  ቦታ፣  አሁን  የሚገኝበት  ሁኔታና  የወደፊት  አቅጣጫዎች  ጥርት  ያለ  ስዕል  እንዲኖረን  ለፅንሰ  ሀሳቡ  አገራዊ  ፍቺ  በመስጠት  መጀመር  ይኖርብናል፡፡  አጣሪ  ዳኝነት  ምንድነው?  ለሚለው  ጥያቄ  በእንግሊዝ፣  በአሜሪካ፣  በፈረንሳይ  ወይም  በሌላ  አገር  ያለው  ትርጓሜ  መነሻ  ሀሳብ  ከመፈንጠቅ  በስተቀር  በአገራችን  ነባራዊ  ሁኔታ  ለጥያቄው  ምትክ  ምላሽ  አይሆንም፡፡  ይህም  ከሁለት  ነገሮች  ይመነጫል፡፡  አንደኛ፤  የአስተዳደር  ህግ  ከሌሎች  አገራዊ  ህጎች (domestic laws)  በበለጠ  የአንዲት  አገር  የህዝብ  አስተዳደር፣  የፖለቲካና  የህገ  መንግስት  ስርዓትና  ታሪክ  ነፀብራቅ  ነው፡፡  በዚህም  የተነሳ  የአጣሪ  ዳኝነት  ሆነ  ሌሎች  የአስተዳደር  ህግ  መርሆዎችና  ፅንሰ  ሀሳቦች  ከአገር  አገር  የጎላ  ልዩነት  ይታይባቸዋል፡፡  የዚህ  ሀሳብ  ተጓዳኝ  የሆነው  ሁለተኛው  ነጥብ  ደግሞ  ለአጣሪ  ዳኝነት  የሚቀርብ  ማናቸውም  ትርጓሜ  በፅንሰ  ሀሳቡ  ይዘትና  አፈጻጸም  ለሚነሱ  መሰረታዊ  ጭብጦች  በከፊል  ምላሹን  ይሰጣል፡፡  ስለሆነም  ፍቺውን  ከእንግሊዝ  ሆነ  ከፈረንሳይ  በመቅዳት  በእኛ  አገር  በውሰት  ወይም  በተሞክሮ  ስም  ተፈጻሚ  ለማድረግ  ብንሞክር ‘ ላም  ባልዋለበት  ኩበት  ለቀማ’  ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ  ውስጥ  የአጣሪ  ዳኝነት  ምንነትና  አፈፃፀም  በተመለከተ  ከብዥታ  የጠራ  አመለካከት  የሌለ  ከመሆኑም  በላይ  ለፍ/ ቤት  የቀረቡ  በጣት  የሚቆጠሩ  ውሱን  ጉዳዮች  እንደሚያሳዩን  ብዥታው  በፍ/ ቤቶቻችንም  ላይ  በእጅጉ  ይንፀባረቃል፡፡  ይህም  ጽንሰ  ሀሳቡ  ወጥነት  እንዲያጣ  ምክንያት  ሆኗል፡፡
ከመነሻው  ብንጀምር ‘ ኢትዮጵያ  ውስጥ  አጣሪ  ዳኝነት  አለ?’  የሚለው  ጥያቄ  በብዙዎች  ዘንድ  ይነሳል፡፡  ለዚህ  ወሰኑን  ያልለየ  ጥቅል  ጥያቄ  በደፈናው  መልስ  መስጠት  አይቻልም፡፡  ቢሰጥም  ትክክለኛ  አይሆንም፡፡  የጥያቄውን  ድፍንነት  ገልጦ  በጥልቀት  ለመፈተሸ  ወደ  ንዑስ  ጥያቄዎች  መሰንጠቅና  አፈጻጸሙንም  በነጠላ  ማጤን  የሚያስማማ  ድምዳሜ  ላይ  ለመድረስ  ያስችላል፡፡  በዚህ  መልኩ  ህላዌነቱም  በተጨባጭ  እውነታ  ላይ  ተመስርቶ  ይወሰናል፡፡
መመለስ  ያለባቸው  ንዑስ  ጥያቄዎች  እነዚህ  ናቸው፡፡
  • የአገራችን ፍ/ቤቶች በአስተዳደሩ የተፈጸሙ ተግባራትን ህጋዊነት የማጣራትና የማረም የዳኝነት ስልጣን አላቸው? አላቸው ከተባለ የስልጣናቸው ህጋዊና ህገ መንግስታዊ መሰረቱ ምንድነው?
  • በአጣሪ ዳኝነት ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? በሌላ አነጋገር ፍ/ቤቶች የትኞቹን አስተዳደራዊ ተግባራት ነው ማጣራት የሚችሉት?
  • አስተዳደራዊ ውሳኔዎች (administrative acts) በፍ/ቤት ሊታዩ ወይም ሊመረመሩ የሚችሉት በየትኞቹ የምርመራ ምክንያቶች (grounds of judicial review) ነው?
  • አንድ ባለጉዳይ አቤቱታው በአጣሪ ዳኝነት እንዲታይለት ሲጠይቅ ከጥያቄ አቀራረብ ጀምሮ እስከ ‘ክስ መሰማትና’ ውሳኔ አሰጣጥ ድረስ ተፈፃሚ የሚሆነው ስነ-ስርዓት የትኛው ነው?
  • ፍርድ ቤቶች በአጣሪ ዳኝነት አቤቱታ ሲቀርብላቸው ምን ዓይነት ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላሉ? ማለትም በአስተዳደራዊ እርምጃ ጉዳት የደረሰበት ወገን ከፍ/ቤቱ ምን አይነት መፍትሄ ማግኘት ይችላል?
እንግዲህ  አጣሪ  ዳኝነት  በኢትዮጵያ  ውስጥ  አለ  ከተባለ  ከላይ  ለተዘረዘሩት  ጥያቄዎች  በሙሉ  ምላሽ  ማግኘት  ይገባል፡፡  አንዳንዴ  ለከፊል  ጥያቄ  መልስ  ቢኖርም  ለተቀሩት  ግን  ምላሽ  ማግኘት  ፈጽሞ  የማይቻል  ባይሆንም  ያስቸግራል፡፡  እነዚህን  ጥያቄዎች  በመመለስ  ሂደት  በመጨረሻ  ሊደረስበት  የሚችለው  ድምዳሜ  የአጣሪ  ዳኝነት  ጽንሰ  ሀሳብ  ሙሉ  በሙሉ  በኢትዮጵያ  ተፈጻሚነት  እንዲኖረው  የዳኞች  ጀብደኝነት (judicial activism)  እንኳን  ባይሆን  ብርታት  የሚጠይቅ  ጉዳይ  መሆኑን  ነው፡፡  በአንድ  በኩል  ዳኞች  ለግለሰቦች  መብትና  ነፃነት  ዘብ  በመቆም  በሌላ  በኩል  በስራ  አስፈፃሚው  ስራ  ጣልቃ  ከመግባት  በመቆጠብ  እነዚህን  ሁለት  መሰረታዊ  እሴቶች  በማመዛዘንና  በማጣጣም  ህጋዊነት የማስፈን ሚናቸውን በብቃትና በብርታት  መወጣት  ይኖርባቸዋል፡፡
የአጣሪ  ዳኝነት  ፅንሰ  ሀሳብ  በአጠቃላይ  ይዘቱና  ወሰኑ  በተለየ  መልኩ  ደግሞ  በኢትዮጵያ  ውስጥ  የያዘው  መልክ  በቀጣይ  ንዑስ  ምዕራፎች  በጥልቀት  የተዳሰሰ  ቢሆንም  እንደ  መነሻ  ያህል  አንድ  ቁልፍና  መሰረታዊ  ነጥብ  ሁሌ  መዘንጋት  የለበትም፡፡  ይኸውም፤  ኢትዮጵያ  ውስጥ  የአስተዳደር  ህግ  ገና  ከህገ  መንግስትና  ከፍትሐብሔር  ህግ  ጉያ  አልተላቀቀም፡፡  በአስተዳደሩ  የሚፈጸሙ  ተግባራት  ህጋዊነታቸው  የሚጣራው  ራሱን  ችሎ  በቆመ የአስተዳደር ህግ ወይም የአጣሪ ዳኝነት ስርዓት  አይደለም፡፡  ህግ  አውጭው  በህግ  ነጥብ  ላይ  ይግባኝ  ከፈቀደባቸው  ውስን  ጉዳዮች  በስተቀር  አስተዳደሩን  ለተግባራቱ  ተጠያቂ  የሚያደርግ  ከፍትሐብሔር  የተለየ  የአስተዳደር  ፍትሕ  ስርዓት ( የፍትሐብሔርና  የወንጀል  ፍትሕ  ስርዓት  እንደምንለው)  የለም፡፡

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!