ለጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ አካላትን ማቋቋሚያ ህጎች
አዋጅ ቁጥር 257/1994
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ
የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ባልተጠበቀ ሁኔታ ከሚከሰቱም ሆነ አመጣጣቸው ሊታይ ከሚችል አደጋዎችና ፈተናዎች በመጠበቅ ረገድ ተጨማሪ ዋስትና ሊያስገኝ የሚችል አሠራር መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
257/1994” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
መቋቋም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ከዚህ በኋላ (ምከር ቤቱ) እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል።
ምክር ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ሊኖሩት ይችላል።
የምክር ቤቱ አባላት
ምክር ቤቱ የሚከተሉት ቋሚ አባላት ይኖሩታል፣
ሀ/ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ................................ ሰብሳቢ ለ/ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ............... ም/ሰብሳቢ ሐ/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ .......................... አባል መ/ የመከላከያ ሚኒስትሩ .............................. „
ሠ/ የደህንነት፤ ኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ዋና ሥራ
አስኪያጅ.................................................... „
ረ/ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዠር ሹም ........... „ ሰ/ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ ………. አባልና ፀሐፊ።
የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፦ ሀ/ ተጨማሪ የምክር ቤት አባላትን ለመሰየም፣ እና
ለ/ ማንኛውም ሰው ሙያዊ ምክር ለመስጠት በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ
በአስረጅነት እንዲገኝ ለመፍቀድ ይችላል።
የምክር ቤቱ ተግባር
ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት የሚመለከቱ የውጭና የመከላከያ ፖሊሲዎች እንዲጣጣሙ በማድረግና በሚገባ ተግባራዊ መደረጋቸውን በመከ ታተል ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያማክራል።
የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ምክር ቤቱ፣ ሀ/ ለሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት የሥጋት ምንጭ የሆኑ ሁኔታዎችን በመገምገም ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ሃሣብ ያቀርባል፤
ለ/ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎችን
የሚመለከቱ የአፈጻጸም መመሪያዎች ያመነጫል፤
ሐ/ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት በሚነካ ማናቸውም ጉዳይ ላይ ይመከራል።
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲደነገግም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚወሰኑ ተግባሮችን ያከናውናል።
የምክር ቤቱ ስብሰባዎች
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲጠራ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል።
በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልአተ ጉባዔ ይኖራል።
ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መመሪያ ሊያወጣ ይችላል።
የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የሚቋቋሙ ኮሚቴዎች የሚኖሩዋቸው አባላትና ዝርዝር ተግባራቸው በምክር ቤቱ ይወሰናል።
WELCOME TO MY BLOG WEBSITES! This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution.
Search This Blog
Sep 20, 2020
ለጠቅላይ ሚንስትር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ ህጎች
PDF DOCUMENTS AND FILE
WordPress
WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution


















































































































































































































