SUBSCRIBE

Search This Blog

Oct 17, 2020

የሕግ የበላይነት ትርጉም

 


የሕግ የበላይነት ትርጉም“የሕግ የበላይነት ማለት የመንግስት አካላት፣ ባለስልጣናት(ሰራተኛውን ጭምሮ) እና ዜጎች በሕግ ጥላ ስር ሲወሰኑና ሲያክብሩ ነው “ የሚል ነው፡፡በአንድ ማህበረሰብ የመንግስት ባለስልጣናትና ዜጎች የእለት- ተለት ስራቸውን የሚፈፅሙት በህግ ጥላ ስር ሆነው ህግን በማክበር ከሆነ በህግ የበላይነት የሚመራ ማህበረሰብ ይባላል፡፡ በዚህ ትርጉም ውስጥ የተገለፀው ህግ ለውጥን ሊያስተናግድ በሚችል መልኩ በጠቅላላ አገላለፅ የተረቀቀና በቀላሉ የሚረዱት፣ ተደራሽ የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ ሁሉም በህግ ፊት እኩል የሆነበት እንዲሁም ህጉ በማይከበርበት ወቅት የማስፈፀሚያ ስርዓትና ተቋማት ሊኖረው ይገባል ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሕግ የበላይነት ሊኖር አይችልም ይላል ዊሊያም፡፡ ለምሳሌ ህጉን የማስፈፀሚያ ስርዓት እና ተቋማት ከሌሉ ወይም ስራቸውን በአግባቡ ካልተወጡ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ይቆጠራል፤ ባለስልጣኑም ሆነ ዜጋው ልጓም እንደሌለው ፈረስ እንዳሻው ይፈነጫል ማለት ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም በሰፋ መልኩ እንደሚከተለው ይተረጉመዋል:-“ የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ሁሉም ሰው፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በግልፅ በፀደቀ፣ ያለአድሎ በእኩል በሚፈፀም፣ በገለልተኛ ፍርድ ቤት በሚተረጎም እና ከአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች የቃል ኪዳን ሰነዶች ጋር በተጣጣመ ህግ ተጠያቂ መሆንን የሚያመለክት ሲሆን ተጠያቂነትን፣ ርትዕን፣ ተገማችነትን፣ የስልጣን ክፍፍልን፣ በውሳኔ ሰጪነት ተሳታፊነትን፣ የዘፈቀደ አሰራርን ለማስወገድ እና የህግና የሥነ ስርዓት ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሂደትና ጥረት ይጨምራል” በማለት ይተረጉመዋል፡፡ፅንሰ ሃሳቡን የሚያጠኑ የሕግ ሊሂቃኖች ከላይ ከተመለከቱት ትርጉሞች አንፃር እይታቸው በሁለት የሚከፈል ሲሆን ሕጋዊነትን መሰረት ያደረገ ዝቀተኛው (formal or procedural conception) እይታ እና መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያካተተ (substantive conception) የህግ የበላይነት በሚል ይከፈላል፡፡ ህጋዊነትን መሰረት ያደረገው ዝቅተኛው የሕግ የበላይነት እይታ ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ህግ መሰረታዊ የአስተዳደር መሳሪያ ሲሆን አግባብ ባለው ባለስልጣን ይመነጫል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ፣ ተገማች፣ የረጋ እና ወደ ፊት የሚፈፀም መሆን እንደሚገባው ይገልፃሉ፡፡ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረገው የህግ የበላይነት እይታ አንድ ህግ ቅቡል ለመሆን ከሥነ ስርዓታዊ መስፈርቶች በተጨማሪ የሞራል ቅቡልነት ያለው፣ ርትዕንና ሰብዓዊ መብቶችን እና ሌሎች ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ያከበረ መሆን ይገባዋል የሚል ነው፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደሌለው በመደንገግ በመንግስት ስልጣን ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው መንግስት ምንም እንኳ ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟላ ህግ ቢያወጣም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ካላከበረ ህጉ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ መንግስት አላማውን ለማስፈፀም ወይም ለአገዛዝ እንዲመቸው መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያላከበረና መደበኛ የሕግ አወጣጥ ሥነ ስርዓትን የተከተለ ህግ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ስርዓት በህግ የተደገፈ ነበር፡፡ በሃገራችንም ፀረ ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራት አዋጅ እና የምርጫ አዋጅ የገዥውን መንግስት ስልጣን ለማራዘም ሲባል የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚገድቡ በመሆናቸው መንግስት የህግ የባላይነትን በሚያስከብር መልኩ እያሻሻላቸው ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህግ የበላይነት ሲባል በህግ አውጪው አካል መደበኛ የህግ አወጣጥ ስነ ስርዓትን ተከትሎ በወጣ ህግ መተዳደር ብቻ ሳይሆን ህጉ ባስገዳጅ ሁኔታ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ባከበረ መልኩ ስለመፅደቁ ትኩረት ይሻል ማለት ነው።የህግ የባላይነት ፋይዳ እና አላባውያንየሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ለሰላም ግንባታ፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲሁም ውጤታማና ተአማኒነት ያለው የፍትህ አስተዳደር ተቋማት ለመገንባት በመሰረታዊነት የሚወሰድ ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ በዋነኛነት ግን ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሳካት የተወጠነ ሃሳብ ነው፡፡እነሱም፡-የመንግስትን የዘፈቀደ የስልጣን አጠቃቀምን ለመገደብ፣የዜጎችን የንብረት፣ የነፃነት እና የሕይወት መብት በሌሎች እንዳይጣስ ጥበቃ ማድረግ ነው፡፡በአንድ ሀገር መንግስት ውስጥ የህግ የበላይነት ስለመኖሩ ማረጋገጭ የሚሆኑ መገለጫ አላባውያን የተለያየ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነትን የሚያከብሩ ሃገራትን ደረጃ(rule of law index) የሚያወጣው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፕሮጅክት(world justice project) የሚጠቀምባቸውን መለኪያዎች ከህገ መንግስታችን አኳያ የሚከተሉትን አምስት አላባውያን እናያለን፡፡በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣህጋዊነትገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካልሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበርሰላምና ደህነትበሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣንየመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የህግ የበላይነት መለኪያ መስፈርት ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅኑት የነበረ ሲሆን ዋና አላማውም መንግስት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋጭና አምባገነነ ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግስት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን እና የዜጎችን ሰላም፣ ደህንነት እና መብት አክብሮ ለማስከበር በሚያስችል መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ መንግስት በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በሚፈፅምበት ወቅት በህግ በተቀመጡ አሰራሮች አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ከተቃረነ በህግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም ህጉን ለመቀየር ወይም ለማሻሻል ፍላጎት ቢያድርባቸው ህግ የማውጣት ስልጣንን የሚገድቡ ወሰኖችን(constraints) በመጣስ ሊሆን አይገባም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 ማንኛም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው ህግ አውጪው የሚያወጣው ህግ ወይም ሕግ አስፈፃሚው የሚወስነው ውሳኔ ወይም ህግ ተርጓሚው አካል ህግ ሲተረጉም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ማክበር እንዳለበት በስልጣናቸው ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ይህን ገደብ የጣሰ ህግ፣ ውሳኔ እና የህግ ትርጉም ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የመንግስት አካላት በህግ በተሰጣቸው ስልጣን( separation of power) ብቻ እየሰሩ ስለመሆኑ ግልፅነትና ተያቂነት የሚያሰፍን የቁጥጥር ማድረጊያ መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 12 ማንኛውም ሃላፊና የህዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ቁጥጥርና ተጠያቂ ከሚደረግባቸው መንገዶች መካከል የሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር መኖር( ለምሳሌ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(17-18) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚውን አካል የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ደንግጓል) ፣ ለሲቨል ማህበራትና ለሚዲያ ተጠያቂ በመሆን፣ የመንግስት ስልጣን በህግ አግባብ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ(ህገ መንግስት አንቀጽ 9(3) ይመለከቷል) ወ.ዘተረፈ ይገኝበታል፡፡ህጋዊነትየህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡ አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡ የንብረት ህግ ዜጎች ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አውጥተው ያፈሩትን ንብረት በነፃነት እንዲጠቀሙ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ የዚህ መርህ መስፈርቶች ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ ስለመንግስት አሰራር ግልፅነት እና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆን በተመለከተ በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 12(1) እና 25 እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል፡፡ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካልነጻ የሆነ ፍ/ቤት የሕግ በላይነት መሰረታዊ ገፅታና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መኖር ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዋነኛው ባሕሪ ደግሞ የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መረጋገጥ ነው፡፡ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግስት ወይም በሌላ ሕግ መደንገጋቸው ብቻ በራሱ ለመብቶች መረጋገጥ ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ መብቶች እውን ይሆኑ ዘንድ ነፃ ፍ/ቤት መኖር አለበት፡፡ ነፃነት የሌለው ፍ/ቤት የሰዎችን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እንዲረጋገጥ ሊያደርግ አይችልም፡፡በዜጎችና በመንግስት እንዲሁም በሰዎች መካከል ባሉ ግንኙነቶች ሳቢያ የሚነሱ የፍትሐብሔር ወይም ወንጀል ክርክሮችን ገለልተኛና ነፃ ሆኖ እልባት ሊሰጥ የሚችል ፍ/ቤት በሌለበት የሕግ በላይነት ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ የሕግ በላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና መልካም አስተዳደር እውን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰላምና ዘለቄታ ያለው ልማትም ዋስትና አይኖረውም፡፡ የዳኝነት ነፃነት ለኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ እድገት መሰረት ነው፡፡ ባለሃብቱ በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት እንዲኖረው በአንድ ሀገር ውሰጥ የዳኝነት ነፃነት መስፈንና መረጋገት ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ ስለዳኝነት ነፃነት አስፈላጊነት ላይ ምንም ክርክር የለውም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 78 እና 79 ነፃ የዳኝነት አካል እንደተቋቋመ እና በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት አካል፣ ከማንኛውም ባለስልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተፅእኖ ነፃ መሆናቸው እና ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት በህግ በመመራት እንደሚያከናውኑ ተደንግጓል፡፡ ጥያቄው ያለው የዳኝነት ነፃነት ስፋትና እና ተግባራዊ አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡ሠላም፣ ስርዓትና ደህንነትየአንድ ሃገር መንግስት፣ ህዝብና ነዋሪዎች ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት መብትና ጥቅም መከበረ እና መረጋገጥ የህግ የባለይነት ዋነኛ ገፅታ ነው፡፡ ዘላቂ ዋስትና ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻቻለው በአገራዊ ደህንነት፣ በመንግስትና በህዝብ ጥቅም፣ በግለሰቦች ደህንነትና መብት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊት ዝግጅቶችንና ሴራዎችን አስቀድሞ ለመከላከል ሲቻልና ወንጀሎቹ ከተፈፀሙ አጥፊዎችን በህግ ስርዓት ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብና ለማስቀጣት ሲቻል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፓለቲካ ድርጅቶች፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራትና ማንኛውም ሰው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በህገ መንግስቱና ሌሎች የህግ ማዕቀፎችና ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የማከናውን የዳበረ ባህል ሲዳብሩ የምርጫ ውድድሮች ጨምሮ ሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካውና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ መሆን ይገባቸዋል፡፡ መንግስት ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልበትን የመጠቀም(monopoly ofcoercive power) ብቸኛ መብት አለው፡፡ በመሆኑም ከህግ ከተፈቀደው ውጭ ዜጎች ወይም ሌሎች አካላት መብታቸውን ለማስከበር ሃይል የመጠቀም መብት የላቸውም፡፡ መንግሰት ሃገረ መንግስቱ የቆመበትን ሥርዓና ደህንነት ማስከበር አለበት ሲባል ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት የመከላከል ስራ መሰራት፣ ፓለቲካዊ ግጭቶችን(ሽብርተኝነት፣ አለመረጋጋትን፣ በታጠቁ ሃይሎች መካከል የሚደረግ ግጭትን) ውጤታማ በሆነ መልኩ መቀነስ እና የግል ችግርን ወይም በደልን ለመወጣት መደበኛውን የህግ ማስከበር ሥርዓት ከመከተል ይልቅ ሃይልን መጠቀም ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው አድርጎ አለመፈፀም(ለምሳሌ የደቦ ፍትህ) በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ሰብዓዊ መብትና ነፃነቶች መከበርሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የመነጩ የማጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡ ሃገራችን ህገ መንግስት የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩ ስለመሆኑ በመሰረታዊ መርህነት የተደነገገ ከመሆኑም በላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ የፌደራል መንግስት የክልል ህግ አውጭ፣ አስፈፃሚና የዳኝነት አካል በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት በተካተቱ የሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ በአንቀጽ 13(1) ተደንግጓል፡፡ መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ግዴታ የሚወጣው አስፈላጊውን የህግ፣ የአስተዳደርና ሌሎች እርምጃዎች በመዉሰድ ነው፡፡ መንግስት ከዜጎቹ ጋር ባለው የቀጥታ ግንኙነት እንዲሁም ዜጎች ባላቸው የእርስ በርስ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብት የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ በመሆኑም የመንግስት ባለስልጣናትና ሰራተኞች ስልጣንና ሃላፊነታቸውን አላግባብና ከህግ ውጭ በመጠቀም የሚፈፀሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቶችን እንዲሁም ሰዎች ባላቸው የጎንዮሽ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብትና ነፃነት የሚጥሱ ድርጊቶች የወንጀል ተጠያቂነትና ሃላፊነት የሚያስከትሉ ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ፣ በመከላከል እና ጥሰቱ ተፈፅሞ ሲገኝ በተሟላ ሁኔታ በወንጀል ፍትህ ስርዓቱ እንዲፈፀም በማድረግ መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበርና የማስከበር ግዴታውን በመወጣት የህግ የባለይነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡የሕግ የባለይነትን ለማረጋገጥ ምን ይደረግ ?በአንድ ሃገር ውስጥ የህግ የበላይነት መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በአንፃራዊነት ካልሆነ በስተቀረ ከላይ የተመለከቱት የህግ የበላይነት መገለጫዎች ሙሉ በሙሉ የተከበረበት ሃገር የለም፡፡ የህግ የበላይነት በጊዜ ሂደት የሚገነባ እና የጋራ ባሕል መገለጫ ይሆናል፡፡ መንግስት እና ዜጎች ሕጎች የእሴቶቻቸው መገለጫ እና ጥቅማቸውን ለማስከበር የወጡ መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ህጎች በማክበርም ሆነ በማስከበር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡

 

የሕግ የበላይነት ማለት የመንግስት አካላት፣ ባለስልጣናት(ሰራተኛውን ጭምሮ) እና ዜጎች በሕግ ጥላ ስር ሲወሰኑና ሲያክብሩ ነው “ የሚል ነው፡፡
በአንድ ማህበረሰብ የመንግስት ባለስልጣናትና ዜጎች የእለት- ተለት ስራቸውን የሚፈፅሙት በህግ ጥላ ስር ሆነው ህግን በማክበር ከሆነ በህግ የበላይነት የሚመራ ማህበረሰብ ይባላል፡፡ በዚህ ትርጉም ውስጥ የተገለፀው ህግ ለውጥን ሊያስተናግድ በሚችል መልኩ በጠቅላላ አገላለፅ የተረቀቀና በቀላሉ የሚረዱት፣ ተደራሽ የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ ሁሉም በህግ ፊት እኩል የሆነበት እንዲሁም ህጉ በማይከበርበት ወቅት የማስፈፀሚያ ስርዓትና ተቋማት ሊኖረው ይገባል ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሕግ የበላይነት ሊኖር አይችልም ይላል ዊሊያም፡፡ ለምሳሌ ህጉን የማስፈፀሚያ ስርዓት እና ተቋማት ከሌሉ ወይም ስራቸውን በአግባቡ ካልተወጡ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ይቆጠራል፤ ባለስልጣኑም ሆነ ዜጋው ልጓም እንደሌለው ፈረስ እንዳሻው ይፈነጫል ማለት ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም በሰፋ መልኩ እንደሚከተለው ይተረጉመዋል:-
“ የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ሁሉም ሰው፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በግልፅ በፀደቀ፣ ያለአድሎ በእኩል በሚፈፀም፣ በገለልተኛ ፍርድ ቤት በሚተረጎም እና ከአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች የቃል ኪዳን ሰነዶች ጋር በተጣጣመ ህግ ተጠያቂ መሆንን የሚያመለክት ሲሆን ተጠያቂነትን፣ ርትዕን፣ ተገማችነትን፣ የስልጣን ክፍፍልን፣ በውሳኔ ሰጪነት ተሳታፊነትን፣ የዘፈቀደ አሰራርን ለማስወገድ እና የህግና የሥነ ስርዓት ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሂደትና ጥረት ይጨምራል” በማለት ይተረጉመዋል፡፡
ፅንሰ ሃሳቡን የሚያጠኑ የሕግ ሊሂቃኖች ከላይ ከተመለከቱት ትርጉሞች አንፃር እይታቸው በሁለት የሚከፈል ሲሆን ሕጋዊነትን መሰረት ያደረገ ዝቀተኛው (formal or procedural conception) እይታ እና መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያካተተ (substantive conception) የህግ የበላይነት በሚል ይከፈላል፡፡ ህጋዊነትን መሰረት ያደረገው ዝቅተኛው የሕግ የበላይነት እይታ ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ህግ መሰረታዊ የአስተዳደር መሳሪያ ሲሆን አግባብ ባለው ባለስልጣን ይመነጫል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ፣ ተገማች፣ የረጋ እና ወደ ፊት የሚፈፀም መሆን እንደሚገባው ይገልፃሉ፡፡ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረገው የህግ የበላይነት እይታ አንድ ህግ ቅቡል ለመሆን ከሥነ ስርዓታዊ መስፈርቶች በተጨማሪ የሞራል ቅቡልነት ያለው፣ ርትዕንና ሰብዓዊ መብቶችን እና ሌሎች ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ያከበረ መሆን ይገባዋል የሚል ነው፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደሌለው በመደንገግ በመንግስት ስልጣን ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው መንግስት ምንም እንኳ ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟላ ህግ ቢያወጣም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ካላከበረ ህጉ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ መንግስት አላማውን ለማስፈፀም ወይም ለአገዛዝ እንዲመቸው መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያላከበረና መደበኛ የሕግ አወጣጥ ሥነ ስርዓትን የተከተለ ህግ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ስርዓት በህግ የተደገፈ ነበር፡፡ በሃገራችንም ፀረ ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራት አዋጅ እና የምርጫ አዋጅ የገዥውን መንግስት ስልጣን ለማራዘም ሲባል የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚገድቡ በመሆናቸው መንግስት የህግ የባላይነትን በሚያስከብር መልኩ እያሻሻላቸው ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህግ የበላይነት ሲባል በህግ አውጪው አካል መደበኛ የህግ አወጣጥ ስነ ስርዓትን ተከትሎ በወጣ ህግ መተዳደር ብቻ ሳይሆን ህጉ ባስገዳጅ ሁኔታ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ባከበረ መልኩ ስለመፅደቁ ትኩረት ይሻል ማለት ነው።
የህግ የባላይነት ፋይዳ እና አላባውያን
የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ለሰላም ግንባታ፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲሁም ውጤታማና ተአማኒነት ያለው የፍትህ አስተዳደር ተቋማት ለመገንባት በመሰረታዊነት የሚወሰድ ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ በዋነኛነት ግን ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሳካት የተወጠነ ሃሳብ ነው፡፡
እነሱም፡-

 

የመንግስትን የዘፈቀደ የስልጣን አጠቃቀምን ለመገደብ፣
የዜጎችን የንብረት፣ የነፃነት እና የሕይወት መብት በሌሎች እንዳይጣስ ጥበቃ ማድረግ ነው፡፡
በአንድ ሀገር መንግስት ውስጥ የህግ የበላይነት ስለመኖሩ ማረጋገጭ የሚሆኑ መገለጫ አላባውያን የተለያየ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነትን የሚያከብሩ ሃገራትን ደረጃ(rule of law index) የሚያወጣው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፕሮጅክት(world justice project) የሚጠቀምባቸውን መለኪያዎች ከህገ መንግስታችን አኳያ የሚከተሉትን አምስት አላባውያን እናያለን፡፡
በህግ የተገደበ የመንግስት
ህጋዊነት
ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል
ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር
ሰላምና ደህነት
በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን
የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የህግ የበላይነት መለኪያ መስፈርት ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅኑት የነበረ ሲሆን ዋና አላማውም መንግስት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋጭና አምባገነነ ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግስት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን እና የዜጎችን ሰላም፣ ደህንነት እና መብት አክብሮ ለማስከበር በሚያስችል መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ መንግስት በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በሚፈፅምበት ወቅት በህግ በተቀመጡ አሰራሮች አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ከተቃረነ በህግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም ህጉን ለመቀየር ወይም ለማሻሻል ፍላጎት ቢያድርባቸው ህግ የማውጣት ስልጣንን የሚገድቡ ወሰኖችን(constraints) በመጣስ ሊሆን አይገባም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 ማንኛም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው ህግ አውጪው የሚያወጣው ህግ ወይም ሕግ አስፈፃሚው የሚወስነው ውሳኔ ወይም ህግ ተርጓሚው አካል ህግ ሲተረጉም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ማክበር እንዳለበት በስልጣናቸው ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ይህን ገደብ የጣሰ ህግ፣ ውሳኔ እና የህግ ትርጉም ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የመንግስት አካላት በህግ በተሰጣቸው ስልጣን( separation of power) ብቻ እየሰሩ ስለመሆኑ ግልፅነትና ተያቂነት የሚያሰፍን የቁጥጥር ማድረጊያ መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 12 ማንኛውም ሃላፊና የህዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ቁጥጥርና ተጠያቂ ከሚደረግባቸው መንገዶች መካከል የሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር መኖር( ለምሳሌ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(17-18) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚውን አካል የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ደንግጓል) ፣ ለሲቨል ማህበራትና ለሚዲያ ተጠያቂ በመሆን፣ የመንግስት ስልጣን በህግ አግባብ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ(ህገ መንግስት አንቀጽ 9(3) ይመለከቷል) ወ.ዘተረፈ ይገኝበታል፡፡
ህጋዊነት
የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡ አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡ የንብረት ህግ ዜጎች ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አውጥተው ያፈሩትን ንብረት በነፃነት እንዲጠቀሙ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ የዚህ መርህ መስፈርቶች ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ ስለመንግስት አሰራር ግልፅነት እና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆን በተመለከተ በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 12(1) እና 25 እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል፡፡

ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል


ነጻ የሆነ ፍ/ቤት የሕግ በላይነት መሰረታዊ ገፅታና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መኖር ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዋነኛው ባሕሪ ደግሞ የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መረጋገጥ ነው፡፡ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግስት ወይም በሌላ ሕግ መደንገጋቸው ብቻ በራሱ ለመብቶች መረጋገጥ ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ መብቶች እውን ይሆኑ ዘንድ ነፃ ፍ/ቤት መኖር አለበት፡፡ ነፃነት የሌለው ፍ/ቤት የሰዎችን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እንዲረጋገጥ ሊያደርግ አይችልም፡፡
በዜጎችና በመንግስት እንዲሁም በሰዎች መካከል ባሉ ግንኙነቶች ሳቢያ የሚነሱ የፍትሐብሔር ወይም ወንጀል ክርክሮችን ገለልተኛና ነፃ ሆኖ እልባት ሊሰጥ የሚችል ፍ/ቤት በሌለበት የሕግ በላይነት ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ የሕግ በላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና መልካም አስተዳደር እውን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰላምና ዘለቄታ ያለው ልማትም ዋስትና አይኖረውም፡፡ የዳኝነት ነፃነት ለኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ እድገት መሰረት ነው፡፡ ባለሃብቱ በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት እንዲኖረው በአንድ ሀገር ውሰጥ የዳኝነት ነፃነት መስፈንና መረጋገት ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ ስለዳኝነት ነፃነት አስፈላጊነት ላይ ምንም ክርክር የለውም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 78 እና 79 ነፃ የዳኝነት አካል እንደተቋቋመ እና በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት አካል፣ ከማንኛውም ባለስልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተፅእኖ ነፃ መሆናቸው እና ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት በህግ በመመራት እንደሚያከናውኑ ተደንግጓል፡፡ ጥያቄው ያለው የዳኝነት ነፃነት ስፋትና እና ተግባራዊ አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡
ሠላም፣ ስርዓትና ደህንነት
የአንድ ሃገር መንግስት፣ ህዝብና ነዋሪዎች ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት መብትና ጥቅም መከበረ እና መረጋገጥ የህግ የባለይነት ዋነኛ ገፅታ ነው፡፡ ዘላቂ ዋስትና ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻቻለው በአገራዊ ደህንነት፣ በመንግስትና በህዝብ ጥቅም፣ በግለሰቦች ደህንነትና መብት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊት ዝግጅቶችንና ሴራዎችን አስቀድሞ ለመከላከል ሲቻልና ወንጀሎቹ ከተፈፀሙ አጥፊዎችን በህግ ስርዓት ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብና ለማስቀጣት ሲቻል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፓለቲካ ድርጅቶች፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራትና ማንኛውም ሰው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በህገ መንግስቱና ሌሎች የህግ ማዕቀፎችና ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የማከናውን የዳበረ ባህል ሲዳብሩ የምርጫ ውድድሮች ጨምሮ ሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካውና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ መሆን ይገባቸዋል፡፡ መንግስት ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልበትን የመጠቀም(monopoly ofcoercive power) ብቸኛ መብት አለው፡፡ በመሆኑም ከህግ ከተፈቀደው ውጭ ዜጎች ወይም ሌሎች አካላት መብታቸውን ለማስከበር ሃይል የመጠቀም መብት የላቸውም፡፡ መንግሰት ሃገረ መንግስቱ የቆመበትን ሥርዓና ደህንነት ማስከበር አለበት ሲባል ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት የመከላከል ስራ መሰራት፣ ፓለቲካዊ ግጭቶችን(ሽብርተኝነት፣ አለመረጋጋትን፣ በታጠቁ ሃይሎች መካከል የሚደረግ ግጭትን) ውጤታማ በሆነ መልኩ መቀነስ እና የግል ችግርን ወይም በደልን ለመወጣት መደበኛውን የህግ ማስከበር ሥርዓት ከመከተል ይልቅ ሃይልን መጠቀም ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው አድርጎ አለመፈፀም(ለምሳሌ የደቦ ፍትህ) በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሰብዓዊ መብትና ነፃነቶች መከበር


ሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የመነጩ የማጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡ ሃገራችን ህገ መንግስት የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩ ስለመሆኑ በመሰረታዊ መርህነት የተደነገገ ከመሆኑም በላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ የፌደራል መንግስት የክልል ህግ አውጭ፣ አስፈፃሚና የዳኝነት አካል በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት በተካተቱ የሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ በአንቀጽ 13(1) ተደንግጓል፡፡ መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ግዴታ የሚወጣው አስፈላጊውን የህግ፣ የአስተዳደርና ሌሎች እርምጃዎች በመዉሰድ ነው፡፡ መንግስት ከዜጎቹ ጋር ባለው የቀጥታ ግንኙነት እንዲሁም ዜጎች ባላቸው የእርስ በርስ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብት የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ በመሆኑም የመንግስት ባለስልጣናትና ሰራተኞች ስልጣንና ሃላፊነታቸውን አላግባብና ከህግ ውጭ በመጠቀም የሚፈፀሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቶችን እንዲሁም ሰዎች ባላቸው የጎንዮሽ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብትና ነፃነት የሚጥሱ ድርጊቶች የወንጀል ተጠያቂነትና ሃላፊነት የሚያስከትሉ ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ፣ በመከላከል እና ጥሰቱ ተፈፅሞ ሲገኝ በተሟላ ሁኔታ በወንጀል ፍትህ ስርዓቱ እንዲፈፀም በማድረግ መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበርና የማስከበር ግዴታውን በመወጣት የህግ የባለይነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡

የሕግ የባለይነትን ለማረጋገጥ ምን ይደረግ ?


በአንድ ሃገር ውስጥ የህግ የበላይነት መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በአንፃራዊነት ካልሆነ በስተቀረ ከላይ የተመለከቱት የህግ የበላይነት መገለጫዎች ሙሉ በሙሉ የተከበረበት ሃገር የለም፡፡ የህግ የበላይነት በጊዜ ሂደት የሚገነባ እና የጋራ ባሕል መገለጫ ይሆናል፡፡ መንግስት እና ዜጎች ሕጎች የእሴቶቻቸው መገለጫ እና ጥቅማቸውን ለማስከበር የወጡ መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ህጎች በማክበርም ሆነ በማስከበር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!