የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች
ከስነ ስርዓት አካሄድ አንጻር ውሳኔ ሰጪ የሆነ የመንግስት አካል በቅን ልቦና ተመርቶ አድሎአዊ ያልሆነ ውሳኔ መስጠትና ከሁሉም በላይ በውሳኔው መብቱ ወይም ጥቅሙ ሊነካ ለሚችል ለማንኛውም ግለሰብ ከውሳኔው በፊት የመሰማት መብቱን ሊጠብቅለት ይገባል፡፡የአስተዳደር ውሳኔ ፍትሐዊነት በዋነኛነት ሁለት መሰረታዊ መርሆዎችን ያቅፋል፡፡ አንደኛው የመሰማት መብት ሲሆን (The right to fair hearing) በላቲን audi alteram partem ተብሎ ሲጠራ አንዳንዴ ‘ተቃራኒውን ወገን ሰማው’ ወይም ‘ማንም ሰው መከላከያው ሳይሰማ እርምጃ ሊወሰድበት አይገባም’ (no one should be condemned unheard) በሚል ይገለጻል፡፡




















































































































































































































