መስቀለኛ መዘዝ
የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ ምንም ላይፈይድለት ምስክሯን “እማማ እኔን ያውቁኛል?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ምስክር — “እንዴት አላውቅህም አንተ ሞላጫ! አውቅሃለው እንጂ! ከልጅነትህ ጀምሮ አሳምሬ አውቅሃለው፡፡ የሌባ ዐይነ ደረቅ! ደሞ አፍህን ሞልተህ ‘ያውቁኛል?’ ትላለህ?”ጠበቃው በመቀጠል “ዐቃቤ ህጉንስ ያውቁታል?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ምስክር — “እንዴት አላውቀው?! ይሄ ወስላታ! አተራማሽ! ሚስትና ልጆቹን ቤት ጎልቶ ሴት ሲያሳድድ ነው እኮ የሚውለው፡፡ እሱንማ እኔ ብቻ ሳልሆን አገሩ በሙሉ ያውቀዋል፡፡”በመቀጠል የነገሩ አካሄድ ያሰጋቸው ክቡር ዳኛ በፍጥነት በምስክርነቱ መሃል ጣልቃ በመግባት ጠበቃውና ዐቃቤ ህጉን ወደሳቸው ዘንድ እንዲመጡ በእጃቸው ምልክት ከሰጡ በኋላ “ሁለታችሁም ወደዚህ ቅረቡ’” በማለት ጠንከር ያለ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ሁለቱም እንደተባሉት የተከበሩት ዳኛ ፊት ተጠግተው ቆሙ፡፡ዳኛው ሁለቱንም ገልመጥ ገልመጥ አድርገው ተመለከቱና “አንተም ሆንክ አንተ! አንድሽም የኔን ስም ታነሺና! ወዮልሽ! በችሎት መድፈር ልክሽን ነው የማከናንብሽ”
\



















































































































































































































