SUBSCRIBE

Search This Blog

Jun 8, 2020

ህጋዊነት



ህጋዊነት
የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ 

 

ህጋዊነት


የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡ የንብረት ህግ ዜጎች ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አውጥተው ያፈሩትን ንብረት በነፃነት እንዲጠቀሙ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ የዚህ መርህ መስፈርቶች ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ 

ስለመንግስት አሰራር ግልፅነት እና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆን በተመለከተ በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 12(1) እና 25 እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል፡፡

የሕግ የበላይነት ትርጉም

“የሕግ የበላይነት ማለት የመንግስት አካላት፣ ባለስልጣናት(ሰራተኛውን ጭምሮ) እና ዜጎች በሕግ ጥላ ስር ሲወሰኑና ሲያክብሩ ነው “ የሚል ነው፡፡
በአንድ ማህበረሰብ የመንግስት ባለስልጣናትና ዜጎች የእለት- ተለት ስራቸውን የሚፈፅሙት በህግ ጥላ ስር ሆነው ህግን በማክበር ከሆነ በህግ የበላይነት የሚመራ ማህበረሰብ ይባላል፡፡ በዚህ ትርጉም ውስጥ የተገለፀው ህግ ለውጥን ሊያስተናግድ በሚችል መልኩ በጠቅላላ አገላለፅ የተረቀቀና በቀላሉ የሚረዱት፣ ተደራሽ የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ ሁሉም በህግ ፊት እኩል የሆነበት እንዲሁም ህጉ በማይከበርበት ወቅት የማስፈፀሚያ ስርዓትና ተቋማት ሊኖረው ይገባል ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሕግ የበላይነት ሊኖር አይችልም ይላል ዊሊያም፡፡ ለምሳሌ ህጉን የማስፈፀሚያ ስርዓት እና ተቋማት ከሌሉ ወይም ስራቸውን በአግባቡ ካልተወጡ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ይቆጠራል፤ ባለስልጣኑም ሆነ ዜጋው ልጓም እንደሌለው ፈረስ እንዳሻው ይፈነጫል ማለት ነው፡፡



WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!