SUBSCRIBE

Search This Blog

Jun 9, 2020

በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ።

በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ።

ህጋዊነት

ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል

ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር

ሰላምና ደህነት

በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን
የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የህግ የበላይነት መለኪያ መስፈርት ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅኑት የነበረ ሲሆን ዋና አላማውም መንግስት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋጭና አምባገነነ ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግስት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን

መንግስት በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በሚፈፅምበት ወቅት በህግ በተቀመጡ አሰራሮች አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ከተቃረነ በህግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም ህጉን ለመቀየር ወይም ለማሻሻል ፍላጎት ቢያድርባቸው ህግ የማውጣት ስልጣንን የሚገድቡ ወሰኖችን(constraints) በመጣስ ሊሆን አይገባም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 ማንኛም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው ህግ አውጪው የሚያወጣው ህግ ወይም ሕግ አስፈፃሚው የሚወስነው ውሳኔ ወይም ህግ ተርጓሚው አካል ህግ ሲተረጉም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ማክበር እንዳለበት በስልጣናቸው ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ይህን ገደብ የጣሰ ህግ፣ ውሳኔ እና የህግ ትርጉም ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የመንግስት አካላት በህግ በተሰጣቸው ስልጣን( separation of power) ብቻ እየሰሩ ስለመሆኑ ግልፅነትና ተያቂነት የሚያሰፍን የቁጥጥር ማድረጊያ መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 12 ማንኛውም ሃላፊና የህዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ቁጥጥርና ተጠያቂ ከሚደረግባቸው መንገዶች መካከል የሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር መኖር( ለምሳሌ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(17-18) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚውን አካል የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ደንግጓል) ፣ ለሲቨል ማህበራትና ለሚዲያ ተጠያቂ በመሆን፣ የመንግስት ስልጣን በህግ አግባብ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ(ህገ መንግስት አንቀጽ 9(3) ይመለከቷል) ወ.ዘተረፈ ይገኝበታል፡፡

ህጋዊነት

የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡ አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡ የንብረት ህግ ዜጎች ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አውጥተው ያፈሩትን ንብረት በነፃነት እንዲጠቀሙ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ የዚህ መርህ መስፈርቶች ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ ስለመንግስት አሰራር ግልፅነት እና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆን በተመለከተ በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 12(1) እና 25 እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል፡፡
የሕግ የበላይነት ትርጉም
“የሕግ የበላይነት ማለት የመንግስት አካላት፣ ባለስልጣናት(ሰራተኛውን ጭምሮ) እና ዜጎች በሕግ ጥላ ስር ሲወሰኑና ሲያክብሩ ነው “ የሚል ነው፡፡
በአንድ ማህበረሰብ የመንግስት ባለስልጣናትና ዜጎች የእለት- ተለት ስራቸውን የሚፈፅሙት በህግ ጥላ ስር ሆነው ህግን በማክበር ከሆነ በህግ የበላይነት የሚመራ ማህበረሰብ ይባላል፡፡ በዚህ ትርጉም ውስጥ የተገለፀው ህግ ለውጥን ሊያስተናግድ በሚችል መልኩ በጠቅላላ አገላለፅ የተረቀቀና በቀላሉ የሚረዱት፣ ተደራሽ የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ ሁሉም በህግ ፊት እኩል የሆነበት እንዲሁም ህጉ በማይከበርበት ወቅት የማስፈፀሚያ ስርዓትና ተቋማት ሊኖረው ይገባል ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሕግ የበላይነት ሊኖር አይችልም ይላል ዊሊያም፡፡ ለምሳሌ ህጉን የማስፈፀሚያ ስርዓት እና ተቋማት ከሌሉ ወይም ስራቸውን በአግባቡ ካልተወጡ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ይቆጠራል፤ ባለስልጣኑም ሆነ ዜጋው ልጓም እንደሌለው ፈረስ እንዳሻው ይፈነጫል ማለት ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም በሰፋ መልኩ እንደሚከተለው ይተረጉመዋል:-
“ የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ሁሉም ሰው፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በግልፅ በፀደቀ፣ ያለአድሎ በእኩል በሚፈፀም፣ በገለልተኛ ፍርድ ቤት በሚተረጎም እና ከአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች የቃል ኪዳን ሰነዶች ጋር በተጣጣመ ህግ ተጠያቂ መሆንን የሚያመለክት ሲሆን ተጠያቂነትን፣ ርትዕን፣ ተገማችነትን፣ የስልጣን ክፍፍልን፣ በውሳኔ ሰጪነት ተሳታፊነትን፣ የዘፈቀደ አሰራርን ለማስወገድ እና የህግና የሥነ ስርዓት ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሂደትና ጥረት ይጨምራል” በማለት ይተረጉመዋል፡፡
ፅንሰ ሃሳቡን የሚያጠኑ የሕግ ሊሂቃኖች ከላይ ከተመለከቱት ትርጉሞች አንፃር እይታቸው በሁለት የሚከፈል ሲሆን ሕጋዊነትን መሰረት ያደረገ ዝቀተኛው (formal or procedural conception) እይታ እና መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያካተተ (substantive conception) የህግ የበላይነት በሚል ይከፈላል፡፡ ህጋዊነትን መሰረት ያደረገው ዝቅተኛው የሕግ የበላይነት እይታ ዊሊያም ከሰጠው ትርጉም ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ህግ መሰረታዊ የአስተዳደር መሳሪያ ሲሆን አግባብ ባለው ባለስልጣን ይመነጫል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ፣ ተገማች፣ የረጋ እና ወደ ፊት የሚፈፀም መሆን እንደሚገባው ይገልፃሉ፡፡ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረገው የህግ የበላይነት እይታ አንድ ህግ ቅቡል ለመሆን ከሥነ ስርዓታዊ መስፈርቶች በተጨማሪ የሞራል ቅቡልነት ያለው፣ ርትዕንና ሰብዓዊ መብቶችን እና ሌሎች ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ያከበረ መሆን ይገባዋል የሚል ነው፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደሌለው በመደንገግ በመንግስት ስልጣን ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው መንግስት ምንም እንኳ ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟላ ህግ ቢያወጣም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ካላከበረ ህጉ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ መንግስት አላማውን ለማስፈፀም ወይም ለአገዛዝ እንዲመቸው መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ያላከበረና መደበኛ የሕግ አወጣጥ ሥነ ስርዓትን የተከተለ ህግ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ስርዓት በህግ የተደገፈ ነበር፡፡ በሃገራችንም ፀረ ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራት አዋጅ እና የምርጫ አዋጅ የገዥውን መንግስት ስልጣን ለማራዘም ሲባል የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚገድቡ በመሆናቸው መንግስት የህግ የባላይነትን በሚያስከብር መልኩ እያሻሻላቸው ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህግ የበላይነት ሲባል በህግ አውጪው አካል መደበኛ የህግ አወጣጥ ስነ ስርዓትን ተከትሎ በወጣ ህግ መተዳደር ብቻ ሳይሆን ህጉ ባስገዳጅ ሁኔታ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ባከበረ መልኩ ስለመፅደቁ ትኩረት ይሻል ማለት ነው።
የህግ የባላይነት ፋይዳ እና አላባውያን
የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ለሰላም ግንባታ፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲሁም ውጤታማና ተአማኒነት ያለው የፍትህ አስተዳደር ተቋማት ለመገንባት በመሰረታዊነት የሚወሰድ ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡ በዋነኛነት ግን ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሳካት የተወጠነ ሃሳብ ነው፡፡
እነሱም፡-
የመንግስትን የዘፈቀደ የስልጣን አጠቃቀምን ለመገደብ፣
የዜጎችን የንብረት፣ የነፃነት እና የሕይወት መብት በሌሎች እንዳይጣስ ጥበቃ ማድረግ ነው፡፡
በአንድ ሀገር መንግስት ውስጥ የህግ የበላይነት ስለመኖሩ ማረጋገጭ የሚሆኑ መገለጫ አላባውያን የተለያየ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነትን የሚያከብሩ ሃገራትን ደረጃ(rule of law index) የሚያወጣው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፕሮጅክት(world justice project) የሚጠቀምባቸውን መለኪያዎች ከህገ መንግስታችን አኳያ የሚከተሉትን አምስት አላባውያን እናያለን፡፡
በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ

ህጋዊነት

ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል

ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር
ሰላምና ደህነት
በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን
የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የህግ የበላይነት መለኪያ መስፈርት ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅኑት የነበረ ሲሆን ዋና አላማውም መንግስት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋጭና አምባገነነ ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግስት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን እና የዜጎችን ሰላም፣ ደህንነት እና መብት አክብሮ ለማስከበር በሚያስችል መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ መንግስት በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በሚፈፅምበት ወቅት በህግ በተቀመጡ አሰራሮች አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ከተቃረነ በህግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም ህጉን ለመቀየር ወይም ለማሻሻል ፍላጎት ቢያድርባቸው ህግ የማውጣት ስልጣንን የሚገድቡ ወሰኖችን(constraints) በመጣስ ሊሆን አይገባም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 ማንኛም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው ህግ አውጪው የሚያወጣው ህግ ወይም ሕግ አስፈፃሚው የሚወስነው ውሳኔ ወይም ህግ ተርጓሚው አካል ህግ ሲተረጉም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ማክበር እንዳለበት በስልጣናቸው ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ይህን ገደብ የጣሰ ህግ፣ ውሳኔ እና የህግ ትርጉም ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የመንግስት አካላት በህግ በተሰጣቸው ስልጣን( separation of power) ብቻ እየሰሩ ስለመሆኑ ግልፅነትና ተያቂነት የሚያሰፍን የቁጥጥር ማድረጊያ መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 12 ማንኛውም ሃላፊና የህዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ቁጥጥርና ተጠያቂ ከሚደረግባቸው መንገዶች መካከል የሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር መኖር( ለምሳሌ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(17-18) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚውን አካል የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ደንግጓል) ፣ ለሲቨል ማህበራትና ለሚዲያ ተጠያቂ በመሆን፣ የመንግስት ስልጣን በህግ አግባብ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ(ህገ መንግስት አንቀጽ 9(3) ይመለከቷል) ወ.ዘተረፈ ይገኝበታል፡፡
ህጋዊነት
የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡ አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡ የንብረት ህግ ዜጎች ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አውጥተው ያፈሩትን ንብረት በነፃነት እንዲጠቀሙ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ የዚህ መርህ መስፈርቶች ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ ስለመንግስት አሰራር ግልፅነት እና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆን በተመለከተ በሕገ መንግስቱን አንቀጽ 12(1) እና 25 እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል፡፡
ገለልተኛና ነፃ የዳኝነት አካል
ነጻ የሆነ ፍ/ቤት የሕግ በላይነት መሰረታዊ ገፅታና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መኖር ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዋነኛው ባሕሪ ደግሞ የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መረጋገጥ ነው፡፡ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግስት ወይም በሌላ ሕግ መደንገጋቸው ብቻ በራሱ ለመብቶች መረጋገጥ ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ መብቶች እውን ይሆኑ ዘንድ ነፃ ፍ/ቤት መኖር አለበት፡፡ ነፃነት የሌለው ፍ/ቤት የሰዎችን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እንዲረጋገጥ ሊያደርግ አይችልም፡፡
በዜጎችና በመንግስት እንዲሁም በሰዎች መካከል ባሉ ግንኙነቶች ሳቢያ የሚነሱ የፍትሐብሔር ወይም ወንጀል ክርክሮችን ገለልተኛና ነፃ ሆኖ እልባት ሊሰጥ የሚችል ፍ/ቤት በሌለበት የሕግ በላይነት ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ የሕግ በላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና መልካም አስተዳደር እውን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰላምና ዘለቄታ ያለው ልማትም ዋስትና አይኖረውም፡፡ የዳኝነት ነፃነት ለኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ እድገት መሰረት ነው፡፡ ባለሃብቱ በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት እንዲኖረው በአንድ ሀገር ውሰጥ የዳኝነት ነፃነት መስፈንና መረጋገት ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ ስለዳኝነት ነፃነት አስፈላጊነት ላይ ምንም ክርክር የለውም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 78 እና 79 ነፃ የዳኝነት አካል እንደተቋቋመ እና በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት አካል፣ ከማንኛውም ባለስልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተፅእኖ ነፃ መሆናቸው እና ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት በህግ በመመራት እንደሚያከናውኑ ተደንግጓል፡፡ ጥያቄው ያለው የዳኝነት ነፃነት ስፋትና እና ተግባራዊ አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡
ሠላም፣ ስርዓትና ደህንነት
የአንድ ሃገር መንግስት፣ ህዝብና ነዋሪዎች ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት መብትና ጥቅም መከበረ እና መረጋገጥ የህግ የባለይነት ዋነኛ ገፅታ ነው፡፡ ዘላቂ ዋስትና ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻቻለው በአገራዊ ደህንነት፣ በመንግስትና በህዝብ ጥቅም፣ በግለሰቦች ደህንነትና መብት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊት ዝግጅቶችንና ሴራዎችን አስቀድሞ ለመከላከል ሲቻልና ወንጀሎቹ ከተፈፀሙ አጥፊዎችን በህግ ስርዓት ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብና ለማስቀጣት ሲቻል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፓለቲካ ድርጅቶች፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራትና ማንኛውም ሰው የዕለት 
ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በህገ መንግስቱና ሌሎች የህግ ማዕቀፎችና ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የማከናውን የዳበረ ባህል ሲዳብሩ የምርጫ ውድድሮች ጨምሮ ሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካውና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ መሆን ይገባቸዋል፡፡ መንግስት ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልበትን የመጠቀም(monopoly ofcoercive power) ብቸኛ መብት አለው፡፡ በመሆኑም ከህግ ከተፈቀደው ውጭ ዜጎች ወይም ሌሎች አካላት መብታቸውን ለማስከበር ሃይል የመጠቀም መብት የላቸውም፡፡ መንግሰት ሃገረ መንግስቱ የቆመበትን ሥርዓና ደህንነት ማስከበር አለበት ሲባል ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት የመከላከል ስራ መሰራት፣ ፓለቲካዊ ግጭቶችን(ሽብርተኝነት፣ አለመረጋጋትን፣ በታጠቁ ሃይሎች መካከል የሚደረግ ግጭትን) ውጤታማ በሆነ መልኩ መቀነስ እና የግል ችግርን ወይም በደልን ለመወጣት መደበኛውን የህግ ማስከበር ሥርዓት ከመከተል ይልቅ ሃይልን መጠቀም ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው አድርጎ አለመፈፀም(ለምሳሌ የደቦ ፍትህ) በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ሰብዓዊ መብትና ነፃነቶች መከበር
ሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የመነጩ የማጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡ ሃገራችን ህገ መንግስት የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩ ስለመሆኑ በመሰረታዊ መርህነት የተደነገገ ከመሆኑም በላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ የፌደራል መንግስት የክልል ህግ አውጭ፣ አስፈፃሚና የዳኝነት አካል በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት በተካተቱ የሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ በአንቀጽ 13(1) ተደንግጓል፡፡ መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ግዴታ የሚወጣው አስፈላጊውን የህግ፣ የአስተዳደርና ሌሎች እርምጃዎች በመዉሰድ ነው፡፡ መንግስት ከዜጎቹ ጋር ባለው የቀጥታ ግንኙነት እንዲሁም ዜጎች ባላቸው የእርስ በርስ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብት የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ በመሆኑም የመንግስት ባለስልጣናትና ሰራተኞች ስልጣንና ሃላፊነታቸውን አላግባብና ከህግ ውጭ በመጠቀም የሚፈፀሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቶችን እንዲሁም ሰዎች ባላቸው የጎንዮሽ ግንኙነት አንዱ የሌላውን መብትና ነፃነት የሚጥሱ ድርጊቶች የወንጀል ተጠያቂነትና ሃላፊነት የሚያስከትሉ ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ፣ በመከላከል እና ጥሰቱ ተፈፅሞ ሲገኝ በተሟላ ሁኔታ በወንጀል ፍትህ ስርዓቱ እንዲፈፀም በማድረግ መንግስት ሰብዓዊ መብት የማክበርና የማስከበር ግዴታውን በመወጣት የህግ የባለይነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡
የሕግ የባለይነትን ለማረጋገጥ ምን ይደረግ ?
በአንድ ሃገር ውስጥ የህግ የበላይነት መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በአንፃራዊነት ካልሆነ በስተቀረ ከላይ የተመለከቱት የህግ የበላይነት መገለጫዎች ሙሉ በሙሉ የተከበረበት ሃገር የለም፡፡ የህግ የበላይነት በጊዜ ሂደት የሚገነባ እና የጋራ ባሕል መገለጫ ይሆናል፡፡ መንግስት እና ዜጎች ሕጎች የእሴቶቻቸው መገለጫ እና ጥቅማቸውን ለማስከበር የወጡ መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ህጎች በማክበርም ሆነ በማስከበር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡

በፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሕብረተሰቡ ድርሻ ምን መሆን አለበት?
መንኛውም ሰው በመንግስት እውቅና በተሰጠው በህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ  ባልሆነ መልኩ ተሳትፎ የማድረግ መብት ሃገራችን ካፀደቀቻቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት የቃል ኪዳን ሰነዶችና በሃገራችን ህገ-መንግስት በአንቀፅ 38 ንዑስ አንቀፅ 1(ሀ) ላይ በግልፅ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ የህብረተሰቡ በፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ የዚሁ መብት መገለጫ ነው፡፡

ለፍትህ አስተዳደሩ የሚደረገው ድጋፍ በበጎ ፈቃደኝነት ከሚደረጉ ተግባራት አንስቶ በህግ የታዘዙ ግዴታዎችን መፈፀም የሚያጠቃልል ሲሆን በህግ የተቀመጡ ግዴታዎችን ሣይፈፅሙ ሲቀሩ ግለሰቦችን በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጉ የወንጀል ድንጋጌዎች በወንጀል ህጉ ተደንግገዋል፡፡

በሃገራችን ህጎች መሰረት ህብረተሰቡ በ 3 መንገዶች በፍትህ አስተዳደሩ ተሳትፎ ወይም ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ

        ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ በመስጠት

        ለ) ምስክር በመሆን

        ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት

 ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ መስጠት

በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ አንቀፅ 11 መሰረት ማንም ሰው ማንኛውንም ወንጀል ሲሰራ ያየ ወይም ያላየም ቢሆን የወንጀል ክስ እንዲቀርብ ወንጀሉን ለማስታወቅ መብት አለው በማለት ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ግን ወንጀል የተፈጸመ መሆኑን ማሳወቅ ግዴታ የሚሆንበት ሁኔታዎች እንዳሉ በወንጀል ህጋችን በዝርዝር ተቀምጧል እነዚህም፡-

ከአንቀጽ 241-246 እና ከአንቀፅ 252-258 የተደነገጉትን ወንጀሎች ማለትም በአገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት፣ የፓለቲካና የግዛት ሉአላዊነት ፣የመከላከያ ሃይል ወይም የውስጥና የውጭ ደህንነት ላይ ወንጀል ሲፈጽም፣ ለመፈጸም ሲሞክር ወይም ሲዘጋጅ ያያ እንደሆነ ለሚመለከተው ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት
በመከላከያ ሰራዊት እና በወታደራዊ ግዴታዎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን( ወታደራዊ ኩብላ ወይም ወታደራዊ አመፅ) የማሳወቅ ግዴታ
በሞት ወይም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀሙን ወይም የወንጀለኛውን ማንነት የማሳወቅ፣
እነዚህ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ለሚመለከተው አካል አለማሳዎቅ የወንጀል ተጠያቂነት ወይም ቅጣት አለው፡፡
በሌላ በኩል ወንጀል ያጠቃላይ ህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር እንደመሆኑ መጠን ወንጀልን መከላከልና ተፈፅሞ ሲገኝ ተጠርጣሪውን ወደ ፍትህ አደባበይ እንዲቀርብ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ወንጀል መፈጸሙን ጥቆማ ለፓሊስ ከማቅረብ በተጨማሪ ማንኛውም ሰው የእጅ ከፈንጅ ወንጀል እየተፈጸመ ወይም ተፈፅሞ ካየ ተጠርጣሪውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችል በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀፅ 50 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች መሟላት አለበት እነሱም፡-

ወንጀሉ እጅ ከፈንጅ የተፈፀመ መሆን አለበት
ወንጀሉ በግል አቤቱታ የሚያስቀጣ የወንጀል ዓይነት መሆን የለበትም
የተፈፀመው ወንጀል ከ3 ወር በላይ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆን አለበት
ይህ ስልጣን ለግለሰቦች የተሰጠው ፓሊስ ወንጀል የተፈፀመበት ቦታ እስከሚደርስ ድረስ ወንጀለኞች ከአካባቢው እንዳይሰወሩ ለመከላከል ሲሆን ይህም በጊዜያዊነት የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የተጠርጣሪውን ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ለፓሊስ ማስረከብ ይገባል፡፡

ለ) ምስክር በመሆን ድጋፍ ማድረግ

በወንጀልም ሆነ በፍትሃብሄር ጉዳይ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገበት ያለን ጉዳይ እልባት ለመስጠት በተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ከሚገባቸው ነገሮች ውስጥ ጉዳዮን ያስረዱልኛል የሚሉዋቸውን የምስክሮች ስም ዝርዝር እና የሰነድ ማስረጃዎችን ከክሱ ወይም ከመልሳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡

ምስክርነት ማለት ግለሰቦች በፍርድ ቤት በተያዘ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ የሚያውቁትን ነገር ፍርድ ቤት በአካል በመቅረብ የአስረጅነት ቃላቸውን የሚሰጡበት አግባብ ነው፡፡

አንድ ሰው ፍርድ ቤት በመቅረብ የሚሰጠው ምስክርነት በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን፡-

መስክርነት መብት የሚሆንበት
ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት
ምስክርነት መብት የሚሆንበት አግባብ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ የጉዳዮ ባለቤቶች( ከሳሽ ወይም ተከሳሽ) ጉዳያቸውን ለማስረዳት እራሳቸው ምስክር ሆነው ሲቀርቡ ነው፡፡

በሌላ በኩል ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት አግባብ ሲሆን ይህም ማለት በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ምስክር ሆኖ የተጠራው ግለሰብ ፍርድ ቤት ለመገኘት ፈቃደኛ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በተያዘው ጉዳይ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት ስለሚቸገር ግለሰቡ በፓሊስ ተገዶ እንዲቀርብ በማድረግ የምስክርነት ቃሉን የሚሰጥበት አግባብ በህግ ተደንግጓል፡፡

የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመመስከር ፍቃደኛ ያልሆነ ግለሰብ በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 448 መሰረት የፍትህ እርዳታ መስጠትን እምቢ በማለት በሚል ርዕስ ሥር የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል፡፡

“ፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ነክ ሥልጣን ያለው አካል በያዘው ጉዳይ ላይ በምስክርነት ወይም በልዮ አዋቂ ምስክርነት ወይም በአስተርጓሚነት እንዲረዳ በህግ መሰረት የተጠራ ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሳይቀርብ የቀረ ወይም ለመቅረብ እምቢተኛ እንደሆነ ከሁለት ወር በማይበልጥቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡”

ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤት አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሚያውቀውን ጉዳይ እንዲመሰክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ሲደርሰው በመጥሪያው በተገለፀው ቀን እና ፍርድ ቤት በመቅረብ የምስክርነት ቃሉን በመስጥት የፍትህ አስተዳደሩን መደገፍ ይችላል፡፡

    ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት

በህገ-መንግስታችን የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነት መርህ ከማስከበር አንፃር ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የፍትህ ተቋም በመሆኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ክብር በመስጠት ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡ ተገቢውን ክብር ለፍርድ ቤቶች መስጠት ይገባል ሲባል ፍርድ ቤቶች በህግ የተጣለባቸውን  ሃላፊነት 

በሚወጡበት ወቅት ችሎት ማስቻያ ቦታዎች የዳኝነት ስራ መልካም አካሄድን ከሚያደናቀፍ፣ ከሚያውክ፣ ወይም የፍርድ ቤቱን ስልጣንና ክብር ዝቅ ከሚያደርጉ ተግባራት ነፃ መሆን ይገባቸዋል፡፡

አዲሱ የወንጀል ህጋችን በአንቀፅ 449 ማንም ሰው በፍ/ቤት ምርመራ ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ የሰደበ፣ ያወከ ወይም በነዚህ ላይ የዛተ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከሦስት ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ካመነ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያዉኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ሕብረተሰባችን በወንጀል ወይም በፍትሃብሄር ፍትህ አስተዳደር ውስጥ በንቁ ሁኔታ በመሳተፍ የፍትህ አካላት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያሳኩ መርዳት ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ፍርድ ቤት ምስክር በመሆን፣ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ ለሚመለከተው አካል በመስጠት ወይም በህግ በተደነገገው አግባብ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና ለፍርድ ቤቶች ተገቢውን ክብር በመስጠት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ በፍትህ አስተዳደሪ መሳተፍ ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፤
“የአስተዳደር ተቋም” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አስፈጻሚ አካል ሆኖ በሕግ የተደራጀ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሲሆን ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ የከተማ አስተዳደርንም ይጨምራል፤ ሆኖም የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞችን አይጨምርም፤
“መመሪያ” ማለት ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ውጤት የሚያስከትል የሕግ ሰነድ ሲሆን በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር የሕግ ሰነድንም ይጨምራል፤
“የአስተዳደር ውሳኔ” ማለት መመሪያ ማውጣትን ሳይጨምር የአስተዳደር ተቋም በዕለት ተዕለት ተግባሩ በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ነው፤
"ሰው" ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
በዚህ አዋጅ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትን ጾታ ይጨምራል፡፡
ክፍል ሁለት
የአስተዳደር መመሪያዎች
ንዑስ ክፍል አንድ
መርህ
አንቀጽ 3 - መመሪያ ስለማውጣት
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መመሪያ ያወጣል፡፡
የአስተዳደር ተቋም መመሪያ የሚያወጣው በዚህ አዋጅ በተደነገገው ሥነ-ሥርዓት መሠረት ብቻ ነው፡፡
አንቀጽ 4 - መመሪያ ስለሚወጣበት ጊዜ
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ማዉጣት አለበት፡፡
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን መመሪያ አለማውጣቱ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት ሊሰጥ የሚገባዉን አገልግሎት ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ላለመስጠት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡
ማንኛውም ሰዉ መብቱን ወይም ጥቅሙን በሚመለከት የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ያላወጣ ቢሆንም የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት አለው፡፡
አንቀጽ 5 - መመሪያ እንዲወጣ ጥያቄ ስለማቅረብ
ማንኛውም ሰው አንድ የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣው የሚገባዉን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ሳያወጣ ቢቀር መመሪያውን እንዲያወጣ በጽሁፍ ሊጠይቀው ይችላል፤
ጥያቄው የቀረበለት የአስተዳደር ተቋም በሠላሳ የሥራ ቀናት ውስጥ መመሪያውን የማውጣት ሂደት መጀመር ወይም ምክንያቱን በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ አለበት፡፡
ንዑስ ክፍል ሁለት
የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት
አንቀጽ 6 - የመመሪያ አወጣጥን የሚመለከት መዝገብ ስለማደራጀት
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም የሚያወጣውን መመሪያ በተመለከተ የሚከተሉትን የያዘ መዝገብ ማደራጀት አለበት፤
ሀ. በተቋሙ በመታየት ላይ ያለ ረቂቅ መመሪያ ርዕሰ ጉዳይ እና የመመሪያውን አወጣጥ መርሃ ግብር፤
ለ. የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚያመለክት መረጃ፤
ሐ. ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ የታተሙ ማስታወቂያዎች፤
መ. በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ስለሚቀርብበት ጊዜ፤
ሠ. ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 መሠረት የተሰበሰቡ አስተያየቶችንና በአስተዳደር ተቋሙ በአስተያየቶቹ ላይ የተወሰዱ አቋሞችን፡፡
ማንኛውም ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የሚደራጀውን መዝገብ መመልከት ወይም አስፈላጊውን ወጪ ሸፍኖ ቅጂውን መውሰድ ይችላል፡፡
አንቀጽ 7 - ማስታወቂያ ስለማዉጣት
የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት ስለሚያወጣው ረቂቅ መመሪያ በጋዜጣ እና የተቋሙን ድረ ገጽ ጨምሮ በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማስታወቂያ ማውጣት አለበት፤
የመመሪያውን ረቂቅ ለማዘጋጀት መሰረት የሆነውን ሕጋዊ ስልጣን እና በመመሪያው ስለሚካተቱት ርዕሰ ጉዳዮች፤
የረቂቅ መመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚቻል ስለመሆኑና የሚገኝበትን ሁኔታ፤
በረቂቅ መመሪያው ላይ ሰዎች አስተያያታቸውን መቼ እና እንዴት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ፤
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 በተመለከተው መዝገብ የሰፈሩ መረጃዎችን የትና መቼ ማግኘት እንደሚቻል የሚገልፅ መረጃ፡፡
አንቀጽ 8 - ረቂቅ መመሪያን ለአስተያየት ስለመላክ
የአስተዳደር ተቋም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 በተደነገገው መሰረት ለሕዝብ ያሳወቀውን ረቂቅ መመሪያ ለሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአስተያየት መላክ አለበት፡፡
የሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ካላቸው አስተያየታቸውን ተቋሙ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሁፍ መላክ አለባቸው፡፡ ተቋሙ የሚወስነው የጊዜ ገደብ በማናቸውም ሁኔታ ከ15 የሥራ ቀናት ማነስ የለበትም።
አንቀጽ 9 - የውይይት መድረክ ስለማዘጋጀት
የአስተዳደር ተቋሙ በመመሪያው ረቂቅ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መቀበያ ጊዜ ካበቃበት ጊዜ አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀት አለበት፡፡
ማንኛውም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 መሠረት ያልተስተናገደ በመድረኩ የሚሳተፍ ሰው አስተያየቱን በጽሑፍ ጭምር ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ በሚያዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ አስተያየቶችን ማስተናገድ የሚያስችል በቂ ጊዜ መመደብ አለበት፡፡
አንቀጽ 10 - ከመመሪያ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ነጻ ስለመሆን
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አዋጅ ከአንቀጽ 6 እስከ 9 ባሉት ድንጋጌዎች ከተመለከቱት ግዴታዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች ነጻ ይሆናል፤
ሀ. የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በመኖሩ በግዴታዎቹ ሥርዓት ውስጥ ለማለፍ ጊዜ የማይፈቅድ ሲሆን፤
ለ. ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ፤ ወይም
ሐ. ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የመመሪያውን ተፈጻሚነት ፋይዳ ቢስ የሚያደርግ ሲሆን፡፡
የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ከግዴታ ነጻ እንዲሆን ያደረገውን ምክንያት የያዘ ዝርዝር መግለጫ ማዘጋጀት አለበት፡፡
ንዑስ ክፍል ሦስት
መመሪያ ስለማጽደቅና ስለተፈፃሚነቱ
አንቀጽ 11 - መመሪያ ስለሚጸድቅበት ጊዜና ሁኔታ
የአስተዳደር ተቋሙ በተዘጋጀው መመሪያ ረቂቅ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 መሠረት የተወሰነው የጽሑፍ አስተያየት ማቅረቢያና የውይይት መድረክ ማካሄጃ ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ መመሪያውን ማጽደቅ አይችልም፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ መመሪያውን ከማጽደቁ በፊት በረቂቁ ላይ የቀረበ ማናቸውንም አስተያየት ከግምት ወስጥ ማስገባት አለበት።
የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተመለከተውን ግዴታ ለመወጣት በአስተያየቱ መሠረት ማስተካከያ ማድረግ ወይም አስተያየቱን የማይቀበል ከሆነ፣ የማይቀበልበትን ምክንያት የሚያብራራ ጽሑፍ ማዘጋጀት አለበት።
የአስተዳደር ተቋሙ ረቂቅ መመሪያውን ከማጽደቁ በፊት ለአስተያየት ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መላክ አለበት፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የረቂቅ መመሪያውን ሕጋዊነት አስመልክቶ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ አስተያየቱን ለአስተዳደር ተቋሙ መላክ አለበት፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ አስተያየቱን ከአልላከ አስተያየት እንደሌለው ተቆጥሮ መመሪያውን የማጽደቁ ሂደት ይቀጥላል፡፡
አንቀጽ 12 - በመመሪያው ረቂቅና በሚወጣው መመሪያ መካከል ልዩነት ስለመኖር
የአስተዳደር ተቋሙ በማስታወቂያ ከተመለከተው ረቂቅ መመሪያ ጋር መሠረታዊ ልዩነት ያለው መመሪያ ማዉጣት አይችልም፤ ሆኖም መሠረታዊ ልዩነት ያለው መመሪያ ለማውጣት ከፈለገ የተጀመረውን የመመሪያ አወጣጥ ሂደት በማቋረጥ አዲስ የመመሪያ አወጣጥ ሂደት ከመጀመር አይከለከልም፡፡
አንድ በመጨረሻ መልክ የተዘጋጀ መመሪያ በማስታወቂያ ከተመለከተው የመመሪያው ረቂቅ መሠረታዊ ልዩነት አለው ሊባል የሚችለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፤
ሀ. የረቂቅ መመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን በጉልህ የተለወጠ ከሆነ፤ ወይም
ለ. ረቂቅ መመሪያው አዳዲስ ግዴታዎችን አካትቶ የተገኘ ከሆነ፡፡
አንቀጽ 13 - የማብራሪያ ጽሑፍ
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ በሚያወጣበት ጊዜ የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማብራሪያ ማዘጋጀት አለበት፤
መመሪያው የወጣበት የሕግ መሠረትና ዓላማ፤
በማስታወቂያው የተሰራጨው ረቂቅና የመጨረሻ ሆኖ በወጣው መመሪያ መካከል የይዘት ልዩነት ካለ የተደረጉትን ለውጦች ከነምክንያቶቹ የሚገልጽ ማስታወሻ፤
በረቂቅ መመሪያው ላይ የቀረቡ አስተያየቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች ማጠቃለያ፡፡
አንቀጽ 14 - የመመሪያ ይዘትና ቅርጽ
በአስተዳደር ተቋም የሚወጣ ማንኛዉም መመሪያ ከመመሪያው ዋና ይዘት በተጨማሪ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፤
ሀ. መመሪያው እንዲወጣ የሥልጣን ምንጭ የሆነውን ሕግ፤
ለ. የመመሪያውን አጭር ርእስ፤
ሐ. የተሻሩ ወይም ተፈጻሚነታቸው የታገዱ መመሪያዎች ካሉ ይህንኑ የሚመለከት ድንጋጌ፤
መ. የዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መመሪያው የወጣበትንና ተፈጻሚ የሚሆንበትን ቀን፡፡
ማንኛውም መመሪያ በአጭርና በግልጽ ቋንቋ መጻፍ አለበት፡፡
የአስተዳደር ተቋም ሌላ አካል ያወጣቸውን በሥልጣኑ ክልል የሚወድቁ መመሪያዎች ወይም የሥነ-ምግባር ደንቦች በሙሉ ወይም በከፊል በማጣቀስ የራሱ መመሪያ አካል ማድረግ ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ የመመሪያው አካል ያደረጋቸውን ሰነዶች ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ አለበት፡፡
አንቀጽ 15 - የመመሪያዎች ምዝገባ
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ እንዳወጣ ወዲያውኑ መመሪያውን ከነማብራሪያው ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት፡፡
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሥራ ላይ የነበረ መመሪያን ይህ አዋጅ በወጣ ከ90 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመዘገበውን መመሪያ ከነማብራሪያው ለሕዝብ ክፍት ማድረግ አለበት፡፡ መመሪያው ስለመመዝገቡም ለአስተዳደር ተቋሙ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡
አንቀጽ 16 - መመሪያውን ተደራሽ ስለማድረግ
የፌድራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 መሠረት የመዘገበውን መመሪያ በድረ ገጹ ላይ መጫን አለበት፡፡
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ፣
ሀ. አሳትሞ ለሚመለከታቸው መንግስታዊና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ማሠራጨት፣ እና
ለ. በተቋሙ ድረ ገጽ ላይ መጫን፣
አለበት፡፡
ማንኛዉም የመመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚፈልግ ሰው ወጪውን ሸፍኖ ከአስተዳደር ተቋሙ መውሰድ ይችላል፡፡
አንቀጽ 17 - የመመሪያ ተፈጻሚነት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 መሠረት ያለተመዘገበና በአንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) መሠረት በአስተዳደር ተቋሙ ድረ ገጽ ላይ ያልተጫነ መመሪያ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ተፈጻሚነቱን ያጣ ነባር መመሪያ በዚህ ክፍል ንዑስ ክፍል ሁለት የተደነገገውን የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተከትሎ እንደ አዲስ እንዲወጣ ሊደረግ ይችላል፡፡
አንቀጽ 18 - ስለመመሪያ ክለሳ
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ አፈጻጸም በተመለከተ በየጊዜው እየገመገመ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡
ክፍል ሦስት
የአስተዳደር ውሳኔዎች
ንዑስ ክፍል አንድ
የአስተዳደር ውሳኔ አጀማመር
አንቀጽ 19 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ስለማቅረብ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ጉዳዩ በሚመለከተዉ ሰዉ ወይም በወኪሉ ሊቀርብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 20 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የሚቀርብበት ሁኔታ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ በጽሑፍ ሆኖ እንደሁኔታዉ በአካል፣ በተመዘገበ ፖስታ ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ሊቀርብ ይችላል፡፡
የአስተዳደር ተቋም የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የሚቀርብበትን ቅጽ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
አንቀጽ 21 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄን ስለመመዝገብ እና ለውሳኔ ስለማቅረብ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ወዲያውኑ ለጥያቄ አቅራቢዉ ደረሰኝ መስጠት እና ጥያቄው በተገቢዉ ጊዜ እንዲመዘገብና ለውሳኔ እንዲቀርብ ማድረግ አለበት፡፡
አንቀጽ 22 - የአስተዳደር ውሳኔን በአስተዳደር ተቋም አነሳሽነት ስለመጀመር
የአስተዳደር ውሳኔ በሚመለከተዉ የአስተዳደር ተቋም አነሳሽነት ሊጀመር ይችላል፡፡
ንዑስ ክፍል ሁለት
የአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች
አንቀጽ 23 - የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠው ሰው
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም ሥልጣን የተሰጠዉ የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ብቻ መሆን አለበት፡፡
አንቀጽ 24 - በሕግ የተሰጠ ሥልጣን ወሰንን አለማለፍ
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለአስተዳደር ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ወሰን ማለፍ የለበትም፡፡
አንቀጽ 25 - የግል እና የሕዝብ ጥቅምን ማመዛዘን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ተቋሙን ተገልጋይ የግል ጥቅም እና በአስተዳደር ተቋሙ ዓላማ የተመለከተውን የሕዝብ ጥቅም ማመዛዘን አለበት፡፡
አንቀጽ 26 - አግባብነት በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት አለመመራት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለጉዳዩ አግባብነት በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት መመራት የለበትም፡፡
አንቀጽ 27 - ሙያዊ ውሳኔ መሥጠት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሙያዉ የሚጠይቀዉን ሥነ-ምግባር፣ ትጋት እና ጥንቃቄ ማክበር አለበት፡፡
አንቀጽ 28 - ተገልጋይን፣ ተቃዋሚን እና ሕዝብን ማድመጥ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 20 ወይም 22 መሠረት የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔ ከመሥጠቱ በፊት የሚመለተዉን ሰው ፍሬ ነገር እና ማስረጃ በሚገባ ማድመጥ እና መመርመር እንዲሁም እንደነገሩ ሁኔታ የሦስተኛ ወገን ተቃዋሚን እና የሕዝብን አስተያዬት ማድመጥ አለበት፡፡
አንቀጽ 29 - በቅን ልቦና መወሰን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በቅን ልቦና መወሰን አለበት፡፡
አንቀጽ 30 - በቂ ምክንያት መስጠት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለአስተዳዳር ውሳኔው በቂ ምክንያት መስጠት አለበት፡፡
አንቀጽ 31 - የጥቅም ግጭትን ማስቀረት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ከተገልጋዩ ጋር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ከሆነ ወይም በማናቸውም ሁኔታ የጥቅም ግጭት የሚያስከትልበት ከሆነ ጉዳዩን ከማየት እራሱን ማግለል አለበት፡፡
አንቀጽ 32 - የተገልጋዮችን እኩልነት ማክበር
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሁሉንም ተገልጋዮች በዘር፣ በብሄር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት መጠን፣ በትውልድ ሁኔታ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ ማስተናገድ አለበት፡፡
አንቀጽ 33 - በተገቢዉ ጊዜ መወሰን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔዉን ሳይዘገይ በተገቢዉ ጊዜ መስጠት እና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ጥቅሞች በውሳኔው መዘግየት ምክንያት ለጉዳት እንዳይጋለጡ ማድረግ አለበት፡፡
የአስተዳደር ውሳኔ በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ መቅረት የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ እንደተሰጠ ውሳኔ ይቆጠራል፡፡
አንቀጽ 34 - ተገማች መሆን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በፍሬ ነገር ተመሳሳይ የሆኑ ጉዳዮችን በተመሳሳይ ሁኔታ መወሰን አለበት፡፡
አንቀጽ 35 - ግልጽ መሆን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ግልጽነትን የተከተለ እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ንዑስ ክፍል ሦስት
የአስተዳደር ውሳኔ አፈፃፀም
አንቀጽ 36 - የአስተዳደር ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለመስጠት
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ ወዲያዉኑ ለተገልጋዩ በጽሑፍ መሠጠት አለበት፡፡
አንቀጽ 37 - የአስተዳደር ውሳኔን የሚፈጽመው ሰው
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ የሚፈጸመው ውሳኔውን በሰጠው ሰዉ ወይም በሚመለከተዉ አካል ይሆናል፡፡
ንዑስ ክፍል አራት
በአስተዳደር ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ ቅሬታ
አንቀጽ 38 - ቅሬታ የማቅረብ መብት
ማንኛውም ሰዉ በተላለፈበት የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ለአስተዳደር ተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
አንቀጽ 39 - የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋም
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋም እና ይህንኑ ለተገልጋዮች ይፋ ማድረግ አለበት፡፡
አንቀጽ 40 - የአስተዳደር ውሳኔው አፈፃፀም መታገድ
ማንኛውም ቅሬታ የቀረበበት የአስተዳደር ውሳኔ ቅሬታው ተመርምሮ እስኪወሰን ድረስ አይፈጸምም፡፡ ሆኖም የውሳኔው ሳይፈጸም መቆየት በሕዝብ ላይ የማይመለስ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ዉሳኔዉ እንዲፈጸም ሊያዝ ይችላል፡፡
አንቀጽ 41 - ቅሬታውን ስለመመርመርና ስለመወሰን
የአስተዳደር ተቋሙ የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ቅሬታውን በሚገባ መመርመር እና የዉሳኔ ሀሳብ ለአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ ለወከለዉ የሥራ ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ የወከለዉ የሥራ ኃላፊ በቅሬታ ማስተናገጃ አካል የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክቶ የሰጠው ውሳኔ የተቋሙ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 42 - የቅሬታ ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለመስጠት
የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 41 መሠረት የተሰጠውን ውሳኔ ወዲያዉኑ ለቅሬታ አቅራቢው በጽሑፍ መስጠት አለበት፡፡
ክፍል አራት
በፍርድ ቤት የሚደረግ የአስተዳደር መመሪያዎችና ውሳኔዎች ክለሳ
ንዑስ ክፍል አንድ
የክለሳ አጀማመር
አንቀጽ 43 - የክለሳ አቤቱታ ስለማቅረብ
የዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣
ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፤
ማንኛውም በአስተዳደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው ውሳኔው በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 44 - የክለሳ አቤቱታ ስለሚቀርብበት ፍርድ ቤት
የአስተዳደር መመሪያ ወይም ዉሳኔ እንዲከለስ አቤቱታ የሚቀርበው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታዎችን የሚያስተናግድ የአስተዳደር ጉዳይ ችሎት ያደራጃል፡፡
ንዑስ ክፍል ሁለት
የክለሳ መርሆዎች
አንቀጽ 45 - የክለሳ ምክንያት
የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት የሚከለሰው፣
ሀ. በዚህ አዋጅ ክፍል ሁለት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ሳይከተል የወጣ፣
ለ. ከአስተዳደር ተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ፣ ወይም
ሐ. ሕግን የጣሰ፣
ሲሆን ነው፡፡
የአስተዳደር ውሳኔ በፍርድ ቤት የሚከለሰው በዚህ አዋጅ ክፍል ሦስት የተደነገጉትን መርሆዎች የጣሰ ሲሆን ነው፡፡
አንቀጽ 46 - የክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው በመጨረሻ ውሳኔ ላይ ስለመሆኑ
ማንኛውም የፍርድ ቤት ክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው የመጨረሻ በሆነ የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ብቻ ነው፡፡
አንቀጽ 47 - አስተዳደራዊ መፍትሄዎችን አሟጦ ስለመጨረስ
በሕግ በሌላ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር ማንኛውም ለፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታ የሚያቀርብ ባለጉዳይ አቤቱታውን ከማቅረቡ በፊት በአስተዳደር ተቋሙ ውስጥ ያሉትን አስተዳደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ መጨረስ አለበት፡፡
የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ቢኖርም የአስተዳደር ተቋሙ አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠቱን ሂደት ከሚገባው ጊዜ በላይ ያራዘመ እንደሆነ አስተዳደራዊ መፍትሄ አሟጦ መጨረስ ግዴታ አይሆንም፡፡
ንዑስ ክፍል ሦስት
የክለሳ ሥርዓት
አንቀጽ 48 - የክለሳ አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1(ሀ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ መመሪያው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ90 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1(ለ) ወይም (ሐ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 47(2) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የአስተዳደር ውሳኔ በፍርደ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ ባለጉዳዩ ውሳኔውን እንዲያውቀው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡
አንቀጽ 49 - የጽሑፍ መልስ ስለማቅረብ
የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት የአስተዳደር ተቋም በ15 የሥራ ቀናት ዉስጥ የጽሑፍ መልስ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ይችላል፡፡
አንቀጽ 50 - ሰነዶችን ስለማቅረብ
የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት የአስተዳደር ተቋም አቤቱታ የቀረበበትን መመሪያ ወይም ዉሳኔ በተመለከተ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ይችላል፡፡
ንዑስ ክፍል አራት
የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ እና አፈፃፀም
አንቀጽ 51 - የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታውን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ መርምሮ ዉሳኔ መስጠት አለበት፡፡
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር መመሪያ ወይም ዉሳኔ ሊያፀና ወይም በሙሉ ወይም በከፊል ሊሽር ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር መመሪያ ወይም ውሳኔ በሙሉ ወይም በከፊል ሲሽር የአስተዳደር ተቋሙ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተጠቆሙ ግድፈቶችን አስተካክሎ መመሪያውን እንደገና እንዲያወጣ ወይም እንዲያሻሽል፣ ወይም ውሳኔ ሰጥቶበት የነበረውን ጉዳይ እንደገና መርምሮ እንዲወስን ሊያዘው ይችላል፡፡
አንቀጽ 52 - የክለሳ ዉሳኔ አፈፃፀም
በፍርድ ቤት የተሰጠ የአስተዳደር መመሪያን ወይም ዉሳኔን የማፅናት ወይም የመሻር ዉሳኔ ወዲያዉኑ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር መመሪያው ወይም ዉሳኔው እንዲሻሻል ካዘዘ የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ ክፍል ሁለት እና ሦስት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች እና መርሆዎች አክብሮ መመሪያውን ወይም የአስተዳደር ውሳኔውን በተገቢዉ ጊዜ ማሻሻል አለበት፡፡
በፍርድ ቤቱ የተሰጠ የአስተዳር መመሪያን ወይም ዉሳኔን በሙሉ ወይም በከፊል የመሻር ዉሳኔ ወይም የማሻሻል ትዕዛዝ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን መመሪያ ወይም ውሳኔ ሕጋዊ ኃይል በሙሉ ወይም በከፊል ያስቀራል፡
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 53 - የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ተፈፃሚ ስለመሆኑ
በዚህ አዋጅ ክፍል አራት ባልተመለከቱ የክለሳ ሥነ-ሥርዓት ጉዳዮች ላይ አግባብነት ያላቸዉ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
አንቀጽ 54 - የጉዳት ካሳ ስለመጠየቅ
ከአስተዳደር መመሪያ ውይም ውሳኔ ጋር በተያያዘ ጥፋት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ተገልጋይ መመሪያውን ያወጣው ወይም ውሳኔውን የሰጠው የአስተዳደር ተቋም አግባብ ባለዉ ሕግ መሠረት ካሳ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡
አንቀጽ 55 - መረጃ የመስጠት ግዴታ
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ከመመሪያ ማውጣት ወይም ከአስተዳደር ውሳኔ መስጠት እና እነዚህን ከመፈጸም ጋር በተያያዘ በሌላ የአስተዳደር ተቋም ሲጠየቅ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበትፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሕብረተሰቡ ድርሻ ምን መሆን አለበት?

መንኛውም ሰው በመንግስት እውቅና በተሰጠው በህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ  ባልሆነ መልኩ ተሳትፎ የማድረግ መብት ሃገራችን ካፀደቀቻቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት የቃል ኪዳን ሰነዶችና በሃገራችን ህገ-መንግስት በአንቀፅ 38 ንዑስ አንቀፅ 1(ሀ) ላይ በግልፅ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ የህብረተሰቡ በፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ የዚሁ መብት መገለጫ ነው፡፡፡፡

በሃገራችን ህጎች መሰረት ህብረተሰቡ በ 3 መንገዶች በፍትህ አስተዳደሩ ተሳትፎ ወይም ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ

        ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ በመስጠት

        ለ) ምስክር በመሆን

        ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት

 ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ መስጠት

በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ አንቀፅ 11 መሰረት ማንም ሰው ማንኛውንም ወንጀል ሲሰራ ያየ ወይም ያላየም ቢሆን የወንጀል ክስ እንዲቀርብ ወንጀሉን ለማስታወቅ መብት አለው በማለት ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ግን ወንጀል የተፈጸመ መሆኑን ማሳወቅ ግዴታ የሚሆንበት ሁኔታዎች እንዳሉ በወንጀል ህጋችን በዝርዝር ተቀምጧል እነዚህም፡-

ከአንቀጽ 241-246 እና ከአንቀፅ 252-258 የተደነገጉትን ወንጀሎች ማለትም በአገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት፣ የፓለቲካና የግዛት ሉአላዊነት ፣የመከላከያ ሃይል ወይም የውስጥና የውጭ ደህንነት ላይ ወንጀል ሲፈጽም፣ ለመፈጸም ሲሞክር ወይም ሲዘጋጅ ያያ እንደሆነ ለሚመለከተው ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት
በመከላከያ ሰራዊት እና በወታደራዊ ግዴታዎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን( ወታደራዊ ኩብላ ወይም ወታደራዊ አመፅ) የማሳወቅ ግዴታ
በሞት ወይም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀሙን ወይም የወንጀለኛውን ማንነት የማሳወቅ፣
እነዚህ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ለሚመለከተው አካል አለማሳዎቅ የወንጀል ተጠያቂነት ወይም ቅጣት አለው፡፡

በሌላ በኩል ወንጀል ያጠቃላይ ህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር እንደመሆኑ መጠን ወንጀልን መከላከልና ተፈፅሞ ሲገኝ ተጠርጣሪውን ወደ ፍትህ አደባበይ እንዲቀርብ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ወንጀል መፈጸሙን ጥቆማ ለፓሊስ ከማቅረብ በተጨማሪ ማንኛውም ሰው የእጅ ከፈንጅ ወንጀል እየተፈጸመ ወይም ተፈፅሞ ካየ ተጠርጣሪውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችል በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀፅ 50 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች መሟላት አለበት እነሱም፡-

ወንጀሉ እጅ ከፈንጅ የተፈፀመ መሆን አለበት
ወንጀሉ በግል አቤቱታ የሚያስቀጣ የወንጀል ዓይነት መሆን የለበትም
የተፈፀመው ወንጀል ከ3 ወር በላይ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆን አለበት
ይህ ስልጣን ለግለሰቦች የተሰጠው ፓሊስ ወንጀል የተፈፀመበት ቦታ እስከሚደርስ ድረስ ወንጀለኞች ከአካባቢው እንዳይሰወሩ ለመከላከል ሲሆን ይህም በጊዜያዊነት የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የተጠርጣሪውን ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ለፓሊስ ማስረከብ ይገባል፡፡

ለ) ምስክር በመሆን ድጋፍ ማድረግ

በወንጀልም ሆነ በፍትሃብሄር ጉዳይ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገበት ያለን ጉዳይ እልባት ለመስጠት በተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ከሚገባቸው ነገሮች ውስጥ ጉዳዮን ያስረዱልኛል የሚሉዋቸውን የምስክሮች ስም ዝርዝር እና የሰነድ ማስረጃዎችን ከክሱ ወይም ከመልሳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡

ምስክርነት ማለት ግለሰቦች በፍርድ ቤት በተያዘ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ የሚያውቁትን ነገር ፍርድ ቤት በአካል በመቅረብ የአስረጅነት ቃላቸውን የሚሰጡበት አግባብ ነው፡፡

አንድ ሰው ፍርድ ቤት በመቅረብ የሚሰጠው ምስክርነት በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን፡-

መስክርነት መብት የሚሆንበት
ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት
ምስክርነት መብት የሚሆንበት አግባብ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ የጉዳዮ ባለቤቶች( ከሳሽ ወይም ተከሳሽ) ጉዳያቸውን ለማስረዳት እራሳቸው ምስክር ሆነው ሲቀርቡ ነው፡፡

በሌላ በኩል ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት አግባብ ሲሆን ይህም ማለት በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ምስክር ሆኖ የተጠራው ግለሰብ ፍርድ ቤት ለመገኘት ፈቃደኛ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በተያዘው ጉዳይ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት ስለሚቸገር ግለሰቡ በፓሊስ ተገዶ እንዲቀርብ በማድረግ የምስክርነት ቃሉን የሚሰጥበት አግባብ በህግ ተደንግጓል፡፡

የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመመስከር ፍቃደኛ ያልሆነ ግለሰብ በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 448 መሰረት የፍትህ እርዳታ መስጠትን እምቢ በማለት በሚል ርዕስ ሥር የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል፡፡

“ፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ነክ ሥልጣን ያለው አካል በያዘው ጉዳይ ላይ በምስክርነት ወይም በልዮ አዋቂ ምስክርነት ወይም በአስተርጓሚነት እንዲረዳ በህግ መሰረት የተጠራ ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሳይቀርብ የቀረ ወይም ለመቅረብ እምቢተኛ እንደሆነ ከሁለት ወር በማይበልጥቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡”

ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤት አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሚያውቀውን ጉዳይ እንዲመሰክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ሲደርሰው በመጥሪያው በተገለፀው ቀን እና ፍርድ ቤት በመቅረብ የምስክርነት ቃሉን በመስጥት የፍትህ አስተዳደሩን መደገፍ ይችላል፡፡

    ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት
በህገ-መንግስታችን የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነት መርህ ከማስከበር አንፃር ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የፍትህ ተቋም በመሆኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ክብር በመስጠት ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡ ተገቢውን ክብር ለፍርድ ቤቶች መስጠት ይገባል ሲባል ፍርድ ቤቶች በህግ የተጣለባቸውን  ሃላፊነት በሚወጡበት ወቅት ችሎት ማስቻያ ቦታዎች የዳኝነት ስራ መልካም አካሄድን ከሚያደናቀፍ፣ ከሚያውክ፣ ወይም የፍርድ ቤቱን ስልጣንና ክብር ዝቅ ከሚያደርጉ ተግባራት ነፃ መሆን ይገባቸዋል፡፡

አዲሱ የወንጀል ህጋችን በአንቀፅ 449 ማንም ሰው በፍ/ቤት ምርመራ ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ የሰደበ፣ ያወከ ወይም በነዚህ ላይ የዛተ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከሦስት ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡
ፍርድ ቤቱም የፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ካመነ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያዉኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ሕብረተሰባችን በወንጀል ወይም በፍትሃብሄር ፍትህ አስተዳደር ውስጥ በንቁ ሁኔታ በመሳተፍ የፍትህ አካላት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያሳኩ መርዳት ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ፍርድ ቤት ምስክር በመሆን፣ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ ለሚመለከተው አካል በመስጠት ወይም በህግ በተደነገገው አግባብ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና ለፍርድ ቤቶች ተገቢውን ክብር በመስጠት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ በፍትህ አስተዳደሪ መሳተፍ ይችላል፡፡

የአስተዳደር ተቋሞች የውሳኔ አሰጣጥና የመመሪያ አወጣጥ መርሆዎችና ሥነ-ሥርዓት  እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰዉ የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ የግልጽነትና የተጠያቂነት ባህል በማዳበር አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎ

አንቀጽ 1 - አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ "የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር ……/2012" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀጽ 2 - ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፤

“የአስተዳደር ተቋም” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አስፈጻሚ አካል ሆኖ በሕግ የተደራጀ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሲሆን ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ የከተማ አስተዳደርንም ይጨምራል፤ ሆኖም የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞችን አይጨምርም፤
“መመሪያ” ማለት ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ውጤት የሚያስከትል የሕግ ሰነድ ሲሆን በስራ ላይ ያለ መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር የሕግ ሰነድንም ይጨምራል፤
“የአስተዳደር ውሳኔ” ማለት መመሪያ ማውጣትን ሳይጨምር የአስተዳደር ተቋም በዕለት ተዕለት ተግባሩ በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ነው፤
"ሰው" ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
በዚህ አዋጅ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትን ጾታ ይጨምራል፡፡
 
ክፍል ሁለት

የአስተዳደር መመሪያዎች

ንዑስ ክፍል አንድ

መርህ

አንቀጽ 3 - መመሪያ ስለማውጣት

ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መመሪያ ያወጣል፡፡

የአስተዳደር ተቋም መመሪያ የሚያወጣው በዚህ አዋጅ በተደነገገው ሥነ-ሥርዓት መሠረት ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ 4 - መመሪያ ስለሚወጣበት ጊዜ
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ማዉጣት አለበት፡፡
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን መመሪያ አለማውጣቱ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት ሊሰጥ የሚገባዉን አገልግሎት ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ላለመስጠት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡
ማንኛውም ሰዉ መብቱን ወይም ጥቅሙን በሚመለከት የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ያላወጣ ቢሆንም የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት አለው፡፡
 
አንቀጽ 5 - መመሪያ እንዲወጣ ጥያቄ ስለማቅረብ
ማንኛውም ሰው አንድ የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣው የሚገባዉን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ሳያወጣ ቢቀር መመሪያውን እንዲያወጣ በጽሁፍ ሊጠይቀው ይችላል፤
ጥያቄው የቀረበለት የአስተዳደር ተቋም በሠላሳ የሥራ ቀናት ውስጥ መመሪያውን የማውጣት ሂደት መጀመር ወይም ምክንያቱን በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ አለበት፡፡
 
ንዑስ ክፍል ሁለት

የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት

 አንቀጽ 6 - የመመሪያ አወጣጥን የሚመለከት መዝገብ ስለማደራጀት
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም የሚያወጣውን መመሪያ በተመለከተ የሚከተሉትን የያዘ መዝገብ ማደራጀት አለበት፤
ሀ. በተቋሙ በመታየት ላይ ያለ ረቂቅ መመሪያ ርዕሰ ጉዳይ እና የመመሪያውን አወጣጥ መርሃ ግብር፤

ለ. የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚያመለክት መረጃ፤

ሐ. ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ የታተሙ ማስታወቂያዎች፤

መ. በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ስለሚቀርብበት ጊዜ፤

ሠ. ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 መሠረት የተሰበሰቡ አስተያየቶችንና በአስተዳደር ተቋሙ በአስተያየቶቹ ላይ የተወሰዱ አቋሞችን፡፡

ማንኛውም ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የሚደራጀውን መዝገብ መመልከት ወይም አስፈላጊውን ወጪ ሸፍኖ ቅጂውን መውሰድ ይችላል፡፡
 
አንቀጽ 7 - ማስታወቂያ ስለማዉጣት
የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት ስለሚያወጣው ረቂቅ መመሪያ በጋዜጣ እና የተቋሙን ድረ ገጽ ጨምሮ በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማስታወቂያ ማውጣት አለበት፤
የመመሪያውን ረቂቅ ለማዘጋጀት መሰረት የሆነውን ሕጋዊ ስልጣን እና በመመሪያው ስለሚካተቱት ርዕሰ ጉዳዮች፤
የረቂቅ መመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚቻል ስለመሆኑና የሚገኝበትን ሁኔታ፤
በረቂቅ መመሪያው ላይ ሰዎች አስተያያታቸውን መቼ እና እንዴት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ፤
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 በተመለከተው መዝገብ የሰፈሩ መረጃዎችን የትና መቼ ማግኘት እንደሚቻል የሚገልፅ መረጃ፡፡
 
አንቀጽ 8 - ረቂቅ መመሪያን ለአስተያየት ስለመላክ
የአስተዳደር ተቋም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 በተደነገገው መሰረት ለሕዝብ ያሳወቀውን ረቂቅ መመሪያ ለሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአስተያየት መላክ አለበት፡፡
የሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ካላቸው አስተያየታቸውን ተቋሙ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሁፍ መላክ አለባቸው፡፡ ተቋሙ የሚወስነው የጊዜ ገደብ በማናቸውም ሁኔታ ከ15 የሥራ ቀናት ማነስ የለበትም።
 አንቀጽ 9 - የውይይት መድረክ ስለማዘጋጀት
የአስተዳደር ተቋሙ በመመሪያው ረቂቅ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መቀበያ ጊዜ ካበቃበት ጊዜ አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀት አለበት፡፡
ማንኛውም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 መሠረት ያልተስተናገደ በመድረኩ የሚሳተፍ ሰው አስተያየቱን በጽሑፍ ጭምር ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ በሚያዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ አስተያየቶችን ማስተናገድ የሚያስችል በቂ ጊዜ መመደብ አለበት፡፡
 አንቀጽ 10 - ከመመሪያ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ነጻ ስለመሆን
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አዋጅ ከአንቀጽ 6 እስከ 9 ባሉት ድንጋጌዎች ከተመለከቱት ግዴታዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች ነጻ ይሆናል፤
ሀ. የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በመኖሩ በግዴታዎቹ ሥርዓት ውስጥ ለማለፍ ጊዜ የማይፈቅድ ሲሆን፤

ለ. ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ፤ ወይም

ሐ. ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የመመሪያውን ተፈጻሚነት ፋይዳ ቢስ የሚያደርግ ሲሆን፡፡

የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ከግዴታ ነጻ እንዲሆን ያደረገውን ምክንያት የያዘ ዝርዝር መግለጫ ማዘጋጀት አለበት፡፡
 
ንዑስ ክፍል ሦስት

መመሪያ ስለማጽደቅና ስለተፈፃሚነቱ

አንቀጽ 11 - መመሪያ ስለሚጸድቅበት ጊዜና ሁኔታ
 
የአስተዳደር ተቋሙ በተዘጋጀው መመሪያ ረቂቅ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 መሠረት የተወሰነው የጽሑፍ አስተያየት ማቅረቢያና የውይይት መድረክ ማካሄጃ ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ መመሪያውን ማጽደቅ አይችልም፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ መመሪያውን ከማጽደቁ በፊት በረቂቁ ላይ የቀረበ ማናቸውንም አስተያየት ከግምት ወስጥ ማስገባት አለበት።
የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተመለከተውን ግዴታ ለመወጣት በአስተያየቱ መሠረት ማስተካከያ ማድረግ ወይም አስተያየቱን የማይቀበል ከሆነ፣ የማይቀበልበትን ምክንያት የሚያብራራ ጽሑፍ ማዘጋጀት አለበት።
የአስተዳደር ተቋሙ ረቂቅ መመሪያውን ከማጽደቁ በፊት ለአስተያየት ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መላክ አለበት፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የረቂቅ መመሪያውን ሕጋዊነት አስመልክቶ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ አስተያየቱን ለአስተዳደር ተቋሙ መላክ አለበት፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ አስተያየቱን ከአልላከ አስተያየት እንደሌለው ተቆጥሮ መመሪያውን የማጽደቁ ሂደት ይቀጥላል፡፡
አንቀጽ 12 - በመመሪያው ረቂቅና በሚወጣው መመሪያ መካከል ልዩነት ስለመኖር
የአስተዳደር ተቋሙ በማስታወቂያ ከተመለከተው ረቂቅ መመሪያ ጋር መሠረታዊ ልዩነት ያለው መመሪያ ማዉጣት አይችልም፤ ሆኖም መሠረታዊ ልዩነት ያለው መመሪያ ለማውጣት ከፈለገ የተጀመረውን የመመሪያ አወጣጥ ሂደት በማቋረጥ አዲስ የመመሪያ አወጣጥ ሂደት ከመጀመር አይከለከልም፡፡
አንድ በመጨረሻ መልክ የተዘጋጀ መመሪያ በማስታወቂያ ከተመለከተው የመመሪያው ረቂቅ መሠረታዊ ልዩነት አለው ሊባል የሚችለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፤
  ሀ. የረቂቅ መመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን በጉልህ የተለወጠ ከሆነ፤ ወይም

     ለ. ረቂቅ መመሪያው አዳዲስ ግዴታዎችን አካትቶ የተገኘ ከሆነ፡፡
አንቀጽ 13 - የማብራሪያ ጽሑፍ
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ በሚያወጣበት ጊዜ የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማብራሪያ ማዘጋጀት አለበት፤

መመሪያው የወጣበት የሕግ መሠረትና ዓላማ፤
በማስታወቂያው የተሰራጨው ረቂቅና የመጨረሻ ሆኖ በወጣው መመሪያ መካከል የይዘት ልዩነት ካለ የተደረጉትን ለውጦች ከነምክንያቶቹ የሚገልጽ ማስታወሻ፤
በረቂቅ መመሪያው ላይ የቀረቡ አስተያየቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች ማጠቃለያ፡፡
 አንቀጽ 14 - የመመሪያ ይዘትና ቅርጽ
በአስተዳደር ተቋም የሚወጣ ማንኛዉም መመሪያ ከመመሪያው ዋና ይዘት በተጨማሪ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፤
ሀ. መመሪያው እንዲወጣ የሥልጣን ምንጭ የሆነውን ሕግ፤

ለ. የመመሪያውን አጭር ርእስ፤

ሐ. የተሻሩ ወይም ተፈጻሚነታቸው የታገዱ መመሪያዎች ካሉ ይህንኑ የሚመለከት ድንጋጌ፤

መ. የዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መመሪያው የወጣበትንና ተፈጻሚ የሚሆንበትን ቀን፡፡

ማንኛውም መመሪያ በአጭርና በግልጽ ቋንቋ መጻፍ አለበት፡፡
የአስተዳደር ተቋም ሌላ አካል ያወጣቸውን በሥልጣኑ ክልል የሚወድቁ መመሪያዎች ወይም የሥነ-ምግባር ደንቦች በሙሉ ወይም በከፊል በማጣቀስ የራሱ መመሪያ አካል ማድረግ ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ የመመሪያው አካል ያደረጋቸውን ሰነዶች ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ አለበት፡፡
አንቀጽ 15 - የመመሪያዎች ምዝገባ
 
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ እንዳወጣ ወዲያውኑ መመሪያውን ከነማብራሪያው ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት፡፡
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሥራ ላይ የነበረ መመሪያን ይህ አዋጅ በወጣ ከ90 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመዘገበውን መመሪያ ከነማብራሪያው ለሕዝብ ክፍት ማድረግ አለበት፡፡ መመሪያው ስለመመዝገቡም ለአስተዳደር ተቋሙ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡
አንቀጽ 16 - መመሪያውን ተደራሽ ስለማድረግ
የፌድራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 መሠረት የመዘገበውን መመሪያ በድረ ገጹ ላይ መጫን አለበት፡፡
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ፣
ሀ.  አሳትሞ ለሚመለከታቸው መንግስታዊና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ማሠራጨት፣ እና

ለ.  በተቋሙ ድረ ገጽ ላይ መጫን፣

አለበት፡፡

ማንኛዉም የመመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚፈልግ ሰው ወጪውን ሸፍኖ ከአስተዳደር ተቋሙ መውሰድ ይችላል፡፡
አንቀጽ 17 - የመመሪያ ተፈጻሚነት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 መሠረት ያለተመዘገበና በአንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) መሠረት በአስተዳደር ተቋሙ ድረ ገጽ ላይ ያልተጫነ መመሪያ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ተፈጻሚነቱን ያጣ ነባር መመሪያ በዚህ ክፍል ንዑስ ክፍል ሁለት የተደነገገውን የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተከትሎ እንደ አዲስ እንዲወጣ ሊደረግ ይችላል፡፡
 አንቀጽ 18 - ስለመመሪያ ክለሳ
ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ አፈጻጸም በተመለከተ በየጊዜው እየገመገመ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡
ክፍል ሦስት

የአስተዳደር ውሳኔዎች

ንዑስ ክፍል አንድ

የአስተዳደር ውሳኔ አጀማመር

 አንቀጽ 19 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ስለማቅረብ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ጉዳዩ በሚመለከተዉ ሰዉ ወይም በወኪሉ ሊቀርብ ይችላል፡፡

አንቀጽ 20 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የሚቀርብበት ሁኔታ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ በጽሑፍ ሆኖ እንደሁኔታዉ በአካል፣ በተመዘገበ ፖስታ ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ሊቀርብ ይችላል፡፡
የአስተዳደር ተቋም የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የሚቀርብበትን ቅጽ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
አንቀጽ 21 - የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄን ስለመመዝገብ እና ለውሳኔ ስለማቅረብ
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ወዲያውኑ ለጥያቄ አቅራቢዉ ደረሰኝ መስጠት እና ጥያቄው በተገቢዉ ጊዜ እንዲመዘገብና ለውሳኔ እንዲቀርብ ማድረግ አለበት፡፡

አንቀጽ 22 - የአስተዳደር ውሳኔን በአስተዳደር ተቋም አነሳሽነት ስለመጀመር
የአስተዳደር ውሳኔ በሚመለከተዉ የአስተዳደር ተቋም አነሳሽነት ሊጀመር ይችላል፡፡
ንዑስ ክፍል ሁለት

የአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች

 አንቀጽ 23 - የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠው ሰው
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም ሥልጣን የተሰጠዉ የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ብቻ መሆን አለበት፡፡

 አንቀጽ 24 - በሕግ የተሰጠ ሥልጣን ወሰንን አለማለፍ
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለአስተዳደር ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ወሰን ማለፍ የለበትም፡፡

አንቀጽ 25 - የግል እና የሕዝብ ጥቅምን ማመዛዘን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ተቋሙን ተገልጋይ የግል ጥቅም እና በአስተዳደር ተቋሙ ዓላማ የተመለከተውን የሕዝብ ጥቅም ማመዛዘን አለበት፡፡

አንቀጽ 26 - አግባብነት በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት አለመመራት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለጉዳዩ አግባብነት በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት መመራት የለበትም፡፡

አንቀጽ 27 - ሙያዊ ውሳኔ መሥጠት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሙያዉ የሚጠይቀዉን ሥነ-ምግባር፣ ትጋት እና ጥንቃቄ ማክበር አለበት፡፡

 አንቀጽ 28 - ተገልጋይን፣ ተቃዋሚን እና ሕዝብን ማድመጥ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 20 ወይም 22 መሠረት የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔ ከመሥጠቱ በፊት የሚመለተዉን ሰው ፍሬ ነገር እና ማስረጃ በሚገባ ማድመጥ እና መመርመር እንዲሁም እንደነገሩ ሁኔታ የሦስተኛ ወገን ተቃዋሚን እና የሕዝብን አስተያዬት ማድመጥ አለበት፡፡

 አንቀጽ 29 - በቅን ልቦና መወሰን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በቅን ልቦና መወሰን አለበት፡፡

 አንቀጽ 30 - በቂ ምክንያት መስጠት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለአስተዳዳር ውሳኔው በቂ ምክንያት መስጠት አለበት፡፡

 አንቀጽ 31 - የጥቅም ግጭትን ማስቀረት
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ከተገልጋዩ ጋር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ከሆነ ወይም በማናቸውም ሁኔታ የጥቅም ግጭት የሚያስከትልበት ከሆነ ጉዳዩን ከማየት እራሱን ማግለል አለበት፡፡

 አንቀጽ 32 - የተገልጋዮችን እኩልነት ማክበር
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሁሉንም ተገልጋዮች በዘር፣ በብሄር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት መጠን፣ በትውልድ ሁኔታ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ ማስተናገድ አለበት፡፡

 አንቀጽ 33 - በተገቢዉ ጊዜ መወሰን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔዉን ሳይዘገይ በተገቢዉ ጊዜ መስጠት እና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ጥቅሞች በውሳኔው መዘግየት ምክንያት ለጉዳት እንዳይጋለጡ ማድረግ አለበት፡፡
የአስተዳደር ውሳኔ በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ መቅረት የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ እንደተሰጠ ውሳኔ ይቆጠራል፡፡
 አንቀጽ 34 - ተገማች መሆን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በፍሬ ነገር ተመሳሳይ የሆኑ ጉዳዮችን በተመሳሳይ ሁኔታ መወሰን አለበት፡፡

 አንቀጽ 35 - ግልጽ መሆን
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ግልጽነትን የተከተለ እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ንዑስ ክፍል ሦስት

የአስተዳደር ውሳኔ አፈፃፀም

 አንቀጽ 36 - የአስተዳደር ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለመስጠት
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ ወዲያዉኑ ለተገልጋዩ በጽሑፍ መሠጠት አለበት፡፡

 አንቀጽ 37 - የአስተዳደር ውሳኔን የሚፈጽመው ሰው
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ የሚፈጸመው ውሳኔውን በሰጠው ሰዉ ወይም በሚመለከተዉ አካል ይሆናል፡፡
ንዑስ ክፍል አራት

በአስተዳደር ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ ቅሬታ

 አንቀጽ 38 - ቅሬታ የማቅረብ መብት
ማንኛውም ሰዉ በተላለፈበት የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ለአስተዳደር ተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡

 አንቀጽ 39 - የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋም
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋም እና ይህንኑ ለተገልጋዮች ይፋ ማድረግ አለበት፡፡

አንቀጽ 40 - የአስተዳደር ውሳኔው አፈፃፀም መታገድ
ማንኛውም ቅሬታ የቀረበበት የአስተዳደር ውሳኔ ቅሬታው ተመርምሮ እስኪወሰን ድረስ አይፈጸምም፡፡ ሆኖም የውሳኔው ሳይፈጸም መቆየት በሕዝብ ላይ የማይመለስ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ዉሳኔዉ እንዲፈጸም ሊያዝ ይችላል፡፡

 አንቀጽ 41 - ቅሬታውን ስለመመርመርና ስለመወሰን
 
የአስተዳደር ተቋሙ የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ቅሬታውን በሚገባ መመርመር እና የዉሳኔ ሀሳብ ለአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ ለወከለዉ የሥራ ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡
የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ የወከለዉ የሥራ ኃላፊ በቅሬታ ማስተናገጃ አካል የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክቶ የሰጠው ውሳኔ የተቋሙ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡
 አንቀጽ 42 - የቅሬታ ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለመስጠት
የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 41 መሠረት የተሰጠውን ውሳኔ ወዲያዉኑ ለቅሬታ አቅራቢው በጽሑፍ መስጠት አለበት፡፡
ክፍል አራት

በፍርድ ቤት የሚደረግ የአስተዳደር መመሪያዎችና ውሳኔዎች ክለሳ

ንዑስ ክፍል አንድ

የክለሳ አጀማመር

 አንቀጽ 43 - የክለሳ አቤቱታ ስለማቅረብ
የዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣

ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፤
ማንኛውም በአስተዳደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው ውሳኔው በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
  አንቀጽ 44 - የክለሳ አቤቱታ ስለሚቀርብበት ፍርድ ቤት
የአስተዳደር መመሪያ ወይም ዉሳኔ እንዲከለስ አቤቱታ የሚቀርበው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታዎችን የሚያስተናግድ የአስተዳደር ጉዳይ ችሎት ያደራጃል፡፡
 
ንዑስ ክፍል ሁለት

የክለሳ መርሆዎች

 አንቀጽ 45 - የክለሳ ምክንያት
የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት የሚከለሰው፣
ሀ.  በዚህ አዋጅ ክፍል ሁለት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ሳይከተል የወጣ፣

ለ.  ከአስተዳደር ተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ፣ ወይም

ሐ. ሕግን የጣሰ፣

ሲሆን ነው፡፡

የአስተዳደር ውሳኔ በፍርድ ቤት የሚከለሰው በዚህ አዋጅ ክፍል ሦስት የተደነገጉትን መርሆዎች የጣሰ ሲሆን ነው፡፡
 አንቀጽ 46 - የክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው በመጨረሻ ውሳኔ ላይ ስለመሆኑ
ማንኛውም የፍርድ ቤት ክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው የመጨረሻ በሆነ የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ብቻ ነው፡፡

 አንቀጽ 47 - አስተዳደራዊ መፍትሄዎችን አሟጦ ስለመጨረስ
በሕግ በሌላ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር ማንኛውም ለፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታ የሚያቀርብ ባለጉዳይ አቤቱታውን ከማቅረቡ በፊት በአስተዳደር ተቋሙ ውስጥ ያሉትን አስተዳደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ መጨረስ አለበት፡፡
የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ቢኖርም የአስተዳደር ተቋሙ አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠቱን ሂደት ከሚገባው ጊዜ በላይ ያራዘመ እንደሆነ አስተዳደራዊ መፍትሄ አሟጦ መጨረስ ግዴታ አይሆንም፡፡
 
ንዑስ ክፍል ሦስት

የክለሳ ሥርዓት
  አንቀጽ 48 - የክለሳ አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1(ሀ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ መመሪያው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ90 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1(ለ) ወይም (ሐ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 47(2) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የአስተዳደር ውሳኔ በፍርደ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ ባለጉዳዩ ውሳኔውን እንዲያውቀው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡
  አንቀጽ 49 - የጽሑፍ መልስ ስለማቅረብ
የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት የአስተዳደር ተቋም በ15 የሥራ ቀናት ዉስጥ የጽሑፍ መልስ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ይችላል፡፡

  አንቀጽ 50 - ሰነዶችን ስለማቅረብ
የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት የአስተዳደር ተቋም አቤቱታ የቀረበበትን መመሪያ ወይም ዉሳኔ በተመለከተ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ  ሊያዝ ይችላል፡፡

ንዑስ ክፍል አራት

የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ እና አፈፃፀም

 አንቀጽ 51 - የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ
 
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታውን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ መርምሮ ዉሳኔ መስጠት አለበት፡፡
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር መመሪያ ወይም ዉሳኔ ሊያፀና ወይም በሙሉ ወይም በከፊል ሊሽር ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር መመሪያ ወይም ውሳኔ በሙሉ ወይም በከፊል ሲሽር የአስተዳደር ተቋሙ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተጠቆሙ ግድፈቶችን አስተካክሎ መመሪያውን እንደገና እንዲያወጣ ወይም እንዲያሻሽል፣ ወይም ውሳኔ ሰጥቶበት የነበረውን ጉዳይ እንደገና መርምሮ እንዲወስን ሊያዘው ይችላል፡፡
  አንቀጽ 52 - የክለሳ ዉሳኔ አፈፃፀም
 
በፍርድ ቤት የተሰጠ የአስተዳደር መመሪያን ወይም ዉሳኔን የማፅናት ወይም የመሻር ዉሳኔ ወዲያዉኑ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር መመሪያው ወይም ዉሳኔው እንዲሻሻል ካዘዘ የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ ክፍል ሁለት እና ሦስት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች እና መርሆዎች አክብሮ መመሪያውን ወይም የአስተዳደር ውሳኔውን በተገቢዉ ጊዜ ማሻሻል አለበት፡፡
በፍርድ ቤቱ የተሰጠ የአስተዳር መመሪያን ወይም ዉሳኔን በሙሉ ወይም በከፊል የመሻር ዉሳኔ ወይም የማሻሻል ትዕዛዝ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን መመሪያ ወይም ውሳኔ ሕጋዊ ኃይል በሙሉ ወይም በከፊል ያስቀራል፡

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

  አንቀጽ 53 - የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ተፈፃሚ ስለመሆኑ
በዚህ አዋጅ ክፍል አራት ባልተመለከቱ የክለሳ ሥነ-ሥርዓት ጉዳዮች ላይ አግባብነት ያላቸዉ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

 አንቀጽ 54 - የጉዳት ካሳ ስለመጠየቅ
ከአስተዳደር መመሪያ ውይም ውሳኔ ጋር በተያያዘ ጥፋት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ተገልጋይ መመሪያውን ያወጣው ወይም ውሳኔውን የሰጠው የአስተዳደር ተቋም አግባብ ባለዉ ሕግ መሠረት ካሳ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡

 አንቀጽ 55 - መረጃ የመስጠት ግዴታ
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ከመመሪያ ማውጣት ወይም ከአስተዳደር ውሳኔ መስጠት እና እነዚህን ከመፈጸም ጋር በተያያዘ በሌላ የአስተዳደር ተቋም ሲጠየቅ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

 አንቀጽ 56 - ደንብ የማውጣት ሥልጣን
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልግ ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡

ወደኋላ ሄዶ ተግባራዊ የሚያደርጉ የታክስና ጉምሩክ ሕግ ድንጋጌዎች ሕገ መንግሥታዊነት
   ሀ. ወደኋላ ሄዶ ተግባራዊ የሚያደርጉ የታክስና ጉምሩክ ሕግ ድንጋጌዎች ሕገ መንግሥታዊነት 
የታክስና የጉምሩክ ሕጎች ስንል ምን ማለታችን ነው? ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያላቸው ዝምድናስ ምን ይመስላል ?

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 2(36) መሠረት የታክስ ሕግ ማለት የጉምሩክ ሕግን ሳይጨምር የታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ፣ የቴምብርና የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣ ታክስ/ቀረጥ/ክፍያ ለመጣል የሚወጣ ሕግ እንድሁም እነዚህን አዋጆች መሠረት በማድረግ የሚወጡ ደንብና መመሪያዎችን ያካትታል፡፡ የጉምሩክ ሕግ ማለት ደግሞ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 2(39) መሠረት የጉምሩክ አዋጁን፣ አዋጁን ተከትለው የሚወጡ የጉምሩክ ደንብና መመሪያዎችን እንድሁም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን /የአሁኑ ገቢዎች ሚኒሰቴር/ የሚያስፈፀማቸውን ሌሎች ሕጎች ያካትታል፡፡

ለዚህ ፅሁፍ ዓላማ ትኩረት የምናደርግባቸው በግብር ከፋዩ እንድሁም በአስመጭና ላኪዎች ዘንድ ሕጉ ወደኋላ ሄዶ ተግባራዊ ሊደረግ አይገባም፤ ሕጉ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት በግብር ይግባኝ ኮሚሽን እና ፍ/ቤቶች ክርክር የሚነሳባቸው ሕጎች ላይ ነው፡፡

 ለ. የታክስና የጉምሩክ ሕጎች የፍትሐብሔር ሕግ ናቸው ወይስ የወንጀል ሕግ ወይስ ሁለቱንም? Are they civil laws or criminal laws or both?

ይህን ፅንሰ ሀሳብ በተመለከተ በአንዳንድ የሕግ ባለሙያዎችና በግብር ይግባኝ ኮሚሽን ዘንድ እነዚህን ሕጎች እንደ ፍትሐ ብሄር ሕግ /civil and administrative laws/ የማየት ዝንባሌ አለ፡፡ ይህም በ1996 ዓ.ም እንደወጣው የወንጀል ሕግ በግልፅ የወንጀል ሕግ የሚል ስያሜ ስለሌለውና በአብዛኛው ስለ ፍትሐብሔራዊ /ገንዘብ ነክ/ ጉዳይ የሚዳስስ ሕግ ነው ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ይሁን እንጅ እነዚህ ሕጎች የፍ/ብሄር ወይም የወንጀል ሕግ ናቸው የሚለውን ለመለየት ህጎቹን በዝርዝር ማንበብና መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 በተመለከተ ከአንቀጽ 166-174 ያሉት ድንጋጌዎች ስለ ጉምሩክ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው በዝርዝር የሚደነግጉ ሲሆን ከዚህ ውጭ ያሉት ድንጋጌዎች ደግሞ ስለ ፍትሐብሔራዊ ወይም ገንዘብ ነክ ጉዳይ ወይም ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ የሚደነግጉ ናቸው፡፡ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/08ን ለማስፈፀም የወጣው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 ስንመለከትም በአዋጁ ከአንቀጽ 106-133 ያሉት ድንጋጌዎች ስለ ታክስ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው በዝርዝር የሚደነግግ ሲሆን ሌሎቹ ድንጋጌዎች ደግሞ ስለ ፍትሐብሔራዊ ወይም ገንዘብ ነክ ጉዳይ ወይም ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ ይደነግጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው የታክስና የጉምሩክ ሕጎች የፍትሐብሔር ሕግና የወንጀል ሕግ ድምር ወጤት መሆናቸውን ነው፡፡ እነዚህ ሕጎች የፍትሐብሔር እና የወንጀል ሕግ ከመሆናቸው በተጨማሪ የስነ ስርዓት ሕጎችም /procedural laws/ ጭምር ናቸው፡፡ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር ከአንቀጽ 152-155 ያሉት ድንጋጌዎች አዋጁ የሚፈፀምበትን ስነ ስርዓት ያስቀምጣሉ፡፡ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 ከአንቀጽ 52-60 እንድሁም ከአንቀጽ 86-94 ያሉት ድንጋጌዎች የገቢ ግብር አዋጁ የሚፈፀምበትን ስነ ስርዓት /መቼ፣የት፣እንደት፣ለማን…..ወዘተ/ የሚለውን ጉዳይ ይደነግጋሉ፡፡ የፌደራል የታክስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 407/09 ከአንቀጽ 9-18 ያሉት ድንጋጌዎችም የገቢ ግብር አዋጁ የሚፈፀምበትን ዝርዝር ስነ ስርዓት የሚደነግጉ ናቸው፡፡  ስለዚህ እነዚህን ሕጎች ስንተረጉም ያላቸውን የፍትሐብሔር፣ የወንጀል እና የስነ ስርዓት ሕግ ባህሪነት ከግምት ባስገባ በሆነ መንገድ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ሕጎች ዘርፈ ብዙ ዘርፎች ያላቸው ሕጎች ናቸው የሚለውን ከተረዳን ይህን ዘርፋቸውን መነሻ በማድረግ የሚነሳውን ትችት /critics/ በቀጣይ እንመለከተዋለን፡፡

ሐ. የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08፣ የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/08 እና የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/09 እንድሁም የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 ሕገ መንግሥታዊነት

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 137 (1) ላይ በግልፅ እንደተደነገገው አዋጁ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት/retroactively/ በተፈፀመ ድርጊት ወይም አለማድረግ ምክንያት በተሰጠ የታክስ ውሳኔ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣውና ስራ ላይ የዋለው ነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ነው፡፡ ይህም የአዋጁ አንቀጽ 139 (2) እና (3) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው አዋጁ ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያሳያል፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዳት የሚቻለው የታክስ ውሳኔው ከነሀሴ 14/2008 ዓ.ም በፊት በማናቸውም ጊዜ የተሰጠ ቢሆንም አዋጁ ወደኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የሚሆን መሆኑን ነው፡፡ ይሁን እንጅ የታክስ ውሳኔው ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት የተሰጠ ቢሆንም አዋጁ ወደኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ልዩ ምክንያቶች አሉ፡፡
1.1 ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት ሊከፈል ሲገባ ባልተከፈለ ታክስ ላይ የሚጣል አስተዳደራዊ ቅጣት በስራ ላይ በነበሩት የታክስ ሕጎች ፍፃሜ መሠረት ያገኛል፡፡

የዚህ ልዩ ሁኔታ ተፈፃሚነት እስከምን ድረስ ነው? What was the scope of application of this exception? አስተዳደራዊ ቅጣት ስንል ምን ማለታችን ነው? ወለድ ወይስ ቅጣት ወይስ ሁለቱንም ያጠቃልላል ?

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 2(24) መሠረት ቅጣት ማለት የታክስ ሕግ በመጣሱ ምክንያት በአዋጁ ክፍል 15 ምዕራፍ 2 ወይም በሌላ ሕግ የሚጣል አስተዳደራዊ ቅጣት ነው፡፡ ይህን አንቀጽ ከአዋጁ አንቀጽ 2(16) ጋር ስንመረምረው አስተዳደራዊ ቅጣት ማለት ቅጣትን ብቻ የሚያመለክት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ምክንያቱም ሕጉ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚል ትርጉም የሰጠው ለቅጣት እንጅ ለወለድ ስላልሆነ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አስተዳደራዊ ቅጣቶችን በዝርዝር የሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 101-115 አስተዳደራዊ ቅጣት የሚል ርዕስ በመስጠት የሚያወራው ስለ ቅጣት እንጅ ስለወለድ አለመሆኑ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ቅጣትን ብቻ ያመላክታል የሚለውን ክርክር ያጠናክርልናል፡፡ ይህም ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት ሊከፈል ሲገባ ባልተከፈለ ታክስ ላይ የሚጣል አስተዳደራዊ ቅጣት በስራ ላይ በነበሩት የታክስ ሕጎች መሠረት ፍፃሜ የሚያገኘው ባልተከፈለው ታክስ ላይ የሚጣለው ቅጣት ብቻ መሆኑን ያሳያል፡፡ ባልተከፈለው ታክስ ላይ የሚጣለውን ፍሬ ግብር እና ወለድ አያካትትም፡፡ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የሚጣለው የቅጣት መጠን፣ የቅጣቱ መጠን ከፍሬ ግብሩ መጠን ጋር ያለው ግንኙነት …ወዘተ በቀድሞው የታክስ ሕግ መሠረት ይዳኛል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ሚኒስቴሩ ቅጣት ከፍሬ ግብሩ በበለጠ ሁኔታ መጣል ይችላል፡፡ ምክንያቱም የቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 ቅጣት ከፍሬ ግብር መብለጥ የለበትም በማለት እንደ ታክስ አስተዳደር አዋጁ ገደብ ስለማያስቀምጥ ነው፡፡ ስለዚህ ልዩ ሁኔታው እነዚህን ጉዳዮች ለመዳኘት የምንጠቅሰው ድንጋጌ ይሆናል ማለት ነው፡፡

1.2 ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት ተጀምሮ ከዚህ ቀን በኋላ በጉባኤ በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ በቀድሞው የታክስ ስነ ስርዓት ሕጎች መሠረት ይዳኛል፡፡ በጉዳዩ ላይ የታክስ ውሳኔ ከዚህ ቀን በፊት ተሰጥቶ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ቀርቦ በጉባኤ በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ /pending cases/ በተጀመረበት ጉዳይ ይቀጥላል፡፡ ይሁን እንጅ የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ነገር ቅሬታው ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት ለጉባኤው መቅረብ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት በኋላ እንደ አድስ የቀረበ ከሆነ ግን አዋጁ ወደኋላ ሄዶ ይሰራል ማለት ነው፡፡ የልዩ ሁኔታው ተፈፃሚነት እስከዚህ ድረስ ነው፡፡

1.3 ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም በፊት በወቅቱ መቅረብ እየነበረበት የአቤቱታው እና የይግባኝ ማቅረቢያው ጊዜ ካለፈ የታክስ አስተዳደር አዋጁ ረጅም የአቤቱታ እና የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጥ ቢሆንም ለይግባኝ ባዩ ጥቅም ሲባል አዋጁ ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም፡፡ ይህም አዋጁ ቸልተኛ ቅሬታ አቅራቢዎችን /negligent complaints/ የማያበረታታ መሆኑን ያሳያል፡፡

በአጠቃላይ የታክስ አስተዳደር አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ስንመለከተው በመርህ ደረጃ ወደኋላ ሄዶ የሚሰራ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰራ መሆኑን ከድንጋጌወቹ መረዳት ይቻላል፡፡ ሕጉ በዚህ ሁኔታ መውጣቱ የህጋዊነት መርህን ይቃረናል አይቃረንም የሚለውን እና ሌሎች ትችቶችን /critics/ ከታች በዝርዝር እንመለከተዋለን፡፡

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/08 አንቀጽ 102 መሠረት አዋጁ ከሀምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተገኘ ገቢ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ይሁን አንጅ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው ነሀሴ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ነው፡፡ ይህም አዋጁ የወጣው ነሀሴ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ሆኖ እያለ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን ሲገባው ወደ ኋላ በመሄድ ከሀምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያሳያል፡፡ በዚህ ላይ የሚነሳውን ትችት/critics/ ከታች እንመለከተዋለን፡፡
ይህ በእንድህ እንዳለ የሚኒስትሮች የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/09 አንቀጽ 71 ደንቡ ከሀምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተገኘ ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጅ ደንቡ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የወጣው ነሀሴ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡ ይህም ደንቡ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን ሲገባው ወደ ኋላ በመሄድ ተፈፃሚ እንድሆን የተደነገገ መሆኑን በግልፅ ያሣያል፡፡
በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 1 እና 183 መሠረት አዋጁ 859/2006 ዓ.ም ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው ግን ህዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም ነው፡፡ የአዋጁ ስያሜ መሰጠት ያለበት አዋጁ በወጣበት ዓመተ ምህረት መሆን ሲገባው አዋጁ ወደኋላ ሄዶ እንደሚሰራ በማስመሰል አዋጅ ቁጥር 859/06 ብሎ ስያሜ መስጠት ዓላማው ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም፡፡ አዋጁ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ይሰራል የሚል ክርክር ለማንሳት ይሁን ወይም ከስያሜ ስህተት የመጣ ይሁን ግልፅ አይደለም፡፡ ይሁን እንጅ አዋጁ በወቅቱ ሲወጣ ምንም ዓላማ ይኑረው የአዋጁ ስያሜ እና የወጣበት ጊዜ መለያየቱ ከሕግ አወጣጥ መርህ ውጭ በቸልተኝነት የወጣ ሕግ መሆኑን ያሳያል፡፡
ከእነዚህ የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች በመነሳት አዋጁና ደንቡ ወደ ኋላ ሄዶ የሚሰራበት አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ነው አይደለም የሚለውን እናያለን፡፡ የህጎቹን ሕገ መንግሥታዊነት በተመለከተ የሕግ ባለሙያዎች ሁለት አይነት ክርክር ያነሳሉ፡፡

አንደኛው የመከራከሪያ ሀሳብ እነዚህ ሕጎች ሕገ መንግሥቱን አይቃረኑም ከሚሉ ባለሙያዎች የሚነሳ ነው፡፡ የሚያነሱትም ምክንያት ሕገ መንግሥቱ የፍትሐብሔር ሕግ (የታክስና የጉምሩክ ሕግን ጨምሮ ) ወደኋላ ሄዶ አይሰራም በሚል በግልፅ አልከለከለም፡፡ ሕገ መንግሥቱ የከለከለው የወንጀል ሕግ ወደኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የማይሆን መሆኑን ነው፡፡ የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 22 በግልፅ የሚደነግገው የወንጀል ሕግ ወደኋላ ሄዶ የማይሰራ መሆኑን ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሕግ ወደኋላ ሄዶ አይሰራም በሚል እንደ ወንጀል ሕጉ አልከለከለም፡፡ ስለዚህ ዝምታው የፍትሐብሔር ሕግ ወደኋላ ሄዶ እንዲሰራ ሕገ መንግሥቱ ይፈቅዳል፤ ባይፈቅድ ኖሮ እንደ ወንጀል ሕጉ ይከለክል ነበር የሚል ክርክር ያነሳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የታክስና የጉምሩክ ሕጎች ወደኋላ ሄደው መስራታቸው ሕገ መንግሥቱን አይቃረንም በሚል ሀሳባቸውን ይደመድማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሀሳብ የሚተችበት ምክንያት አለ፡፡ የትችቱ አንደኛው ምክንያትም ይህ የክርክር ሀሳብ የታክስና የጉምሩክ ሕጎችን የወንጀል ሕግ ይዘት ያላቸው ሕጎች መሆናቸውን ካለመገንዘብ የቀረበ በመሆኑ ነው፡፡ ይሄውም የታክስና የጉምሩክ ሕጎች የፍትሐብሔርና የወንጀል ሕግ ድምር ውጤት መሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ሕጎች የሚደነግጉት የፍትሐብሔር ተጠያቂነትን ብቻ ሳይሆን የወንጀል ተጠያቂነትን ጭምር ነው፡፡ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 106-133 ስለ ታክስ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው በዝርዝር ይደነግጋሉ፡፡ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 166-174 ስለ ጉምሩክ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው በዝርዝር ይደነግጋሉ፡፡ ይህ የሚያሳየው ሕገ መንግሥቱ የፍትሐብሔር ሕግ (ታክስና ጉምሩክ ሕግ) ወደኋላ ሄዶ አይሰራም በሚል እንደ ወንጀል ሕጉ ያልከለከለ በመሆኑ ሕገ መንግሥቱን አይቃረኑም የሚል ክርክር የምናነሳ ከሆነ እነዚህ ሕጎች በውስጣቸው የወንጀል ድንጋጌዎችንም ስለያዙ የወንጀል ጉዳዩም ወደኋላ ሄዶ ይሰራል የሚል ድምዳሜ ላይ የምንደርስ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ደግሞ በግልፅ ሕገ መንግሥቱን ይቃረናል፡፡ ምክንያቱም ሕገ መንግሥቱ በግልፅ የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም በሚል ስለሚደነግግ ነው፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት የታክስና የጉምሩክ ሕጎች የፍትሐብሔር፣ የወንጀልና የስነ ስርዓት ሕግም ጭምር ስለሆኑ ህጎቹ ወደኋላ ሄደው መስራታቸው ሕገ መንግሥቱን አይቃረንም የሚለው መከራከሪያ ውሀ የሚቋጥር አይደለም፡፡ ምክንያቱም በኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 22(1) መሠረት የወንጀል ሕግ ወደኋላ ሄዶ አይሰራም ስለሚልና ይሄ ክልከላም ከወንጀሉ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በአንድ ኮድ ለተደነገገው የፍትሐብሔር ሕግም ስለሚሰራ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አንደኛ በታክስና በጉምሩክ ሕጎች ውስጥ የፍትሐ ብሄሩም ሆነ የወንጀል ጉዳዩ አብረው በአንድ ኮድ ነው የተቀመጡት ፤ ሁለተኛ የህዝብን ጥቅም /public interest/ የሚጠብቀው የወንጀል ሕግ ወደኋላ ሄዶ አይሰራም ከተባለ የግል ጥቅምን /private interest/ የሚጠብቀው በታክስና ጉምሩክ ሕጉ ውስጥ የተቀመጠው የፍትሐብሔር ሕግ ወደኋላ ሄዶ የሚሰራበት አመክንዮ /logic/ የለም፡፡

ሁለተኛው የክርክር ሀሳብ ደግሞ ከላይ የጠቀስናቸው የታክስና የጉምሩክ ሕጎች ሕገ መንግሥቱን ይቃረናሉ፤ሕገ መንግሰታዊ አይደሉም ከሚሉ ባለሙያዎች የሚቀርብ ነው፡፡ እኔም ይህንን ሀሳብ ከሚጋሩ ባለሙያዎች አንዱ ስሆን ከላይ የጠቀስናቸው ወደኋላ ሄደው ተፈፃሚ የሚሆኑ የታክስና የጉምሩክ ሕጎች ሕገ መንግሥቱን ያቃረናሉ፡፡ ምክንያቱም፡-

1ኛ. የሕገ መንግሥቱ መግቢያ እኛ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች "በሀገራችን ውስጥ ዘላቂ ሰላም፣ ዋስትና ያለው ድሞክራሲ ለማምጣት……..ወዘተ " ከዚህ ቀን ጀምሮ በተወካዮቻችን አማካኝነት ይህን ሕገ መንግሥት አውጥተናል ማለቱ በራሱ የህጋዊነት መርህን /principle of legality/ ያሳያል፡፡ ሕገ መንግሥቱ በመግቢያው ላይ ከዚህ ቀን ጀምሮ ሕገ መንግሥት አፀደቅን ይላል እንጅ ወደኋላ ሄዶ ይሰራል አይልም፡፡ እንዴውም ከዚህ በፊት የተዛባ ታሪካችንን / የኋላ ታሪካችንን/ ለማረም ከነሀሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሕገ መንግሥት ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም አፀደቅን ይላል እንጅ የኋላ ታሪካችንን ለማረም ሕገ መንግሥቱ ወደኋላ ሄዶ ይሰራል አይልም፡፡ የሕገ መንግሥቱ መግቢያ በቁጥር 1 እና 3 ላይ ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ከነሀሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የሚውል መሆኑን መደንገጉ ሕገ መንግሥቱ ወደ ፊት እንጅ ወደኋላ ሄዶ የማይሰራ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህም የሀገሪቱ ሕግ ቁንጮ የሆነው ሕገ መንግሥት ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚሰራ መሆኑን ያሳያል፡፡ የሕገ መንግሥቱ አውጭዎች ፍላጎትም /intention of the legislator/ ሕገ መንግሥቱ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ወደፊት እንድሰራ ማድረግ መሆኑን ከመግቢያው መረዳት ይቻላል፡፡  የሕገ መንግሥቱ መግቢያ ሁለት አንድምታ /two ways of interpretation in one expression/ አለው፡፡

ሀ. ሕገ መንግሥቱ በራሱ ወደ ፊት እንጅ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም የሕገ መንግሥቱ ባለቤትና አውጭዎች ከዚህ ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሕግ አወጣን እንጅ ከመውጣቱ በፊት ለተፈፀሙ ድርጊቶች ወደኋላ ሄዶ ተፈፃሚ የሚሆን ሕግ አወጣን ብለው አላስቀመጡም፡፡

ለ. ሌሎች ከሕገ መንግሥቱ በታች ያሉ ሕጎችም የሕገ መንግሥቱን ፈለግ በመከተል ሕጉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆን ወይም /proactive/ በሆነ መንገድ መውጣት እንዳለበት የሚጠቁም ነው፡፡ ምክንያቱም የሀገሪቱ የበላይ ሕግ የሆነው ሕገ መንግሥት ከወጣሁበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ እሆናለሁ ካለ ሌሎች ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርገው የሚወጡና ሕገ መንግሰቱን መጣስ /መቃረን/ የማይችሉ ሕጎችም በዚሁ መልክ መውጣት አለባቸው የሚል መልዕክት እያስተላለፈ ነው ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ የታክና የጉምሩክ ሕጎች ወደኋላ ሄደው ተፈፃሚ እንድሆኑ በአዋጅና በደንብ መደንገጉ ሕገ መንገስቱን ይጥሳል ፤መጣስ ብቻ ሳይሆን ሕገ መንግሥቱ አታድርግ ያለውን ነገር ሕግ አውጭው አካል ያደረገ መሆኑን ያሳያል፡፡

2ኛ. ሕገ መንግሥቱ ከመግቢያው በተጨማሪ በአንቀጽ 22 (1) ላይ ማንኛውም የወንጀል ሕግ ተፈፃሚ የሚሆነው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው በሚል ይደነግጋል፡፡ የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም በማለት በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ሕጉ ከመውጣቱ በፊት ለተፈፀመው ድርጊት ወደኋላ ሄዶ አይሰራም በማለት በመግቢያው ላይ የተገለፀውን የህጋዊነት መርህ ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው ሕግ ተፈፃሚ የሚሆነው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን የወንጀል ሕጉ ወደኋላ ሄዶ መስራት ተጠርጣሪውን የሚጠቅመው ከሆነ ግን ሕጉ ወደኋላ ሄዶ ይሰራል፡፡ ይህ ድንጋጌ የሚያሳው የህጋዊነት መርህ ልዩ ሁኔታ /exception/ ያለው መሆኑን ነው፡፡ ይሄውም ልዩ ሁኔታው ተፈፃሚ የሚሆነው፡-

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!