SUBSCRIBE

Search This Blog

Jun 30, 2020

በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን


    በህግ የተገደበ የመንግስት ስልጣ።
         ህጋዊነት
                 በሕግ የተገደበ የመንግስት ስልጣን

የመንግስት፣ የባለስልጣናቱና እንደራሴዎቹ ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የህግ የበላይነት መለኪያ መስፈርት ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያቀነቅኑት የነበረ ሲሆን ዋና አላማውም መንግስት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋጭና አምባገነነ ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግስት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን እና የዜጎችን ሰላም፣ ደህንነት እና መብት አክብሮ ለማስከበር
መንግስት በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በሚፈፅምበት ወቅት በህግ በተቀመጡ አሰራሮች አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ከተቃረነ በህግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም ህጉን ለመቀየር ወይም ለማሻሻል ፍላጎት ቢያድርባቸው ህግ የማውጣት ስልጣንን የሚገድቡ ወሰኖችን(constraints) በመጣስ ሊሆን አይገባም፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 ማንኛም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ የምንረዳው ህግ አውጪው የሚያወጣው ህግ ወይም ሕግ አስፈፃሚው የሚወስነው ውሳኔ ወይም ህግ ተርጓሚው አካል ህግ ሲተረጉም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ማክበር እንዳለበት በስልጣናቸው ላይ ገደብ አስቀምጧል፡፡ ይህን ገደብ የጣሰ ህግ፣ ውሳኔ እና የህግ ትርጉም ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የመንግስት አካላት በህግ በተሰጣቸው ስልጣን( separation of power) ብቻ እየሰሩ ስለመሆኑ ግልፅነትና ተያቂነት የሚያሰፍን የቁጥጥር ማድረጊያ መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡ የኢፌድሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 12 ማንኛውም ሃላፊና የህዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ቁጥጥርና ተጠያቂ ከሚደረግባቸው መንገዶች መካከል የሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር መኖር( ለምሳሌ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(17-18) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚውን አካል የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ደንግጓል) ፣ ለሲቨል ማህበራትና ለሚዲያ ተጠያቂ በመሆን፣ የመንግስት ስልጣን በህግ አግባብ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ(ህገ መንግስት አንቀጽ 9(3) ይመለከቷል) ወ.ዘተረፈ ይገኝበታል፡፡
ህጋዊነት
የህግ የባላይነት ማረጋገጫ ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕጋዊነት መርህ መኖር ሲሆን አንድ ህግ ከረቂቅ ጀምሮ ፀድቆ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት ተደራሽ መሆኑ፣ ህጉ ግልፅና በቀላሉ የሚረዱት መሆኑ፣ ለውጥን የሚያስተናግድ፣ ተገማች የሆነ፣ ሊፈፀም የሚችል፣ በሁሉም ላይ በእኩል ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ እና ማስፈፀሚ ስርዓትና ተቋም ሊኖር ይገባል የሚል ነው፡፡ አንድ የህግ ስርዓት እነዚህን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ መንግስት እና ዜጎች ለህጉ ይገዛሉ ተብሎ አይጠበቀም፡፡ ይህ መርህ መከበሩ ዜጎች ባልወጣ ህግ እንዳይቀጡና የወጡትንም ህጎች አክብረው የእለተ ተለት ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡ ህጉም ተገማች በመሆኑ ግብይት እንዲሳለጥ ይደርጋል፡፡ ምክንያቱም ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የውል ህግ በመኖሩ ዜጎች ያለ ስጋት በነፃነት እንዲገበያዮ ዋስትና ይሰጣቸዋል፤ ዉሉን ያላከበረ ተገዶ እንዲፈፅም ወይም ካሳ እንዲከፍል ስለሚደርግ ለሌላኛው ወገን ዋስትና ይሆናል፡፡

WordPress

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITES HOME ON WORDPRESS

This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution

BLOG CATEGORIE'S

ABOUT CONTACT & MAPS

Share This It!